Sidama Media Network-SMN
Nearby non profit organizations
1620 Elton Road #204
03/23/2026
በቶሮንቶ የሚኖሩ የሲዳማ ኮሚዩኒቲ አባላት የፊቼ ጫምባላላ በአልን አከበሩ።
**************//**************
ማርች 23, 2026
SMN ዲሲ
በቶሮንቶ የሚገኙ የሲዳማ ኮሚዩኒቲ አባላት የሲዳማ አዲሱን አመት የፊቼ ጫምባላላ በአል በተለያዩ ዝግጂቶች አክብረው መዋላቸውን ከስፍራው የደረሰን መረጃ ያመለክታል።
እ.ኤ.አ ማርቻ 21 , 2026 በተከበረው በዚሁ በአል የሲዳማን ህዝብ ባህል እና ታሪክ የተመለከተ ጽሁፍ በታዳጊዎች የቀረበ ሲሆን፣ በውጭ አገር ተወልደው በማደግ የሚገኙ እነዚሁ የማህበረሰቡ ልጆች ባህላቸውን በራሳቸው ተነሳሽነት በቀጣይነት እያከበሩ እንዲዘልቁም ምክክር ተደርጎል።
በእለቱ በስፍራው ለነበሩ ለሁሉም ታዳጊዎች እና ህፃናት ልዩ የፊቼ ጫምባላላ ስጦታ ከኮሚኒቲውም ተበርክቶላቸዋል።
በአሉን በየአመቱ በጋራ ሰብሰብ ብሎ ማክበር ለኮሚኒቲው ያለው ጠቀመታ የአንድ ቀን ጉዳይ ብቻ አለመሆኑና በተለይ የማህበሩን አንድነት ለማጠናከር ፋይዳው የጎላ መሆኑን ታዳሚዎች ገልፀዋል።
03/17/2026
ሲዳማ አዲስ እና ባለራዕይ መሪ ያስፈልጋታል ተባለ።
************//************
ማርች 17, 2026
SMN, ዲሲ
ሰሞኑን የፍቼ ጫንባላላ በዓል አከባበር ላይ ተገኝተው የክልሉ ፕሬዝዳንት አቶ ደስታ ሌዳሞ ያደረጉትን ንግግር ተከትሎ በርካቶች ሀሳባቸውን እየሰጡ ይገኛሉ። ሀሳባቸው ከሰጡት መሀከል በሰሜን አሜሪካ የሚኖሩ፣ ለሲዳማ ህዝብ ትግል ከፍተኛ አስተዋጽኦ ያበረከቱ የአስተውሎተ-ሰውሰራሽ ሳይንቲስት ዶክተር በኃይሉ ቤላሞ ይጠቀሳሉ።
ዶክተር በኃይሉ ቤላሞ የሲዳማ ክልል ርዕሰ-መስተዳድሩ በፍቼ ጫንባላላ በዓል አከባበር ላይ፣ በመድረክ ያደረጉትን ንግግር በተመለከተ የሚከተለውን ዘለግ ያለ ሀሳብ በግላቸው ፌስቡክ ገፅ አስፍረዋል።
«በዘንድሮው በዓል ላይ የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር በሕዝብ ፊት ቀርበው ብዙዎች ሲሰማቸው የነበረውን እውነት ተናግረዋል፤ ይኸውም አንድነቱ መላላቱን ነው።
ይህ ድፍረትን ይጠይቃል። ንግግሩ ከልብ የመነጨ ከሆነ፣ እንዲሁም ስህተትን አምኖ በተሻለ መንገድ ለመሥራት እውነተኛ ቁርጠኝነት የታየበት ከሆነ፣ የሚደነቅ ብቻ ሳይሆን ፊቼ ጫንባባላላ የሚጠይቀውም ይሄኑ ነው።
ነገር ግን፣ ፊቼ ጫንባላላ የሚያስተምረን ፈውስ እውነተኛነትን እንደሚሻ ነው። ያለ እውነተኛ ለውጥ የሚደረግ እርቅ ባዶ ነው።
ሲዳማ በለም መሬት፣ በባህል፣ እንዲሁም በሕዝቡ ብሩህ አእምሮና ጉልበት የታደለች እጅግ ሰፊ አቅም ያላት ክልል ናት። የሲዳማ ሕዝብ ታግሎ ያገኘው የክልልነት ጥያቄ ችግሩ አልነበረም። የክልልነት መብት ትክክለኛ መሠረት ነበረ፣ አሁንም ነው። የሚያመው እውነት ግን ትርጉም ያለው ኢኮኖሚያዊ ልማት ጨርሶ አለመኖሩ ነው፤ ይህ ደግሞ የሲዳማ ሕዝብ ወይም የክልልነት ጥያቄው ውድቀት አይደለም። ይልቁንም የአመራር ውድቀት ነው። በቃ፣ ግልጽና ቀላል እውነት ይሄው ነው።
ያለፈውን ስህተት ማመን ዋጋ የሚኖረው ለቀጣዩ እርምጃ መሰረት ሲሆን ብቻ ነው። የሚቀጥለው እርምጃ ደግሞ ግልጽ ነው፡ ሲዳማ አዲስና ባለራዕይ አመራር ያስፈልገዋል። ደፋር፣ ብቁና ሥራን ለመሥራት የሚተጋ አዲስ ትውልድ! በትላንትናው ታማኝነትና ዕዳ ያልተተበተበ አመራር! በየቀኑ ሲነቃ ስለ መንገድ፣ ስለ ሥራ ዕድል፣ ስለ ትምህርት ቤት፣ ስለ ኢንቨስትመንትና ስለ ተራው የሲዳማ ቤተሰብ ዕድል የሚያስብ—ያንን ለማሳካትም ተነሳሽነትና ራዕይ ያለው መሪ ያስፈልጋል። በአሮጌ መንገድ ላይ አዲስ ስም መለጠፍ ሳይሆን፣ እውነተኛና መሠረታዊ ለውጥ የሚያመጣ አዲስነት!
የሲዳማ ሕዝብ ብዙ የፊቼ በዓላትን አክብሯል፣ ብዙ ቃላትን ሰምቷል፣ እንዲሁም ረጅም ጊዜ ጠብቋል። ሕዝቡ በእውነተኛ ለውጥና በስም ብቻ በሚደረግ ለውጥ መካከል ያለውን ልዩነት ያውቃል። ይህ አዲስ ዓመት ይዞት በሚመጣው ተስፋና ግልጽነት፣ እውነተኛ ለውጥ ሲመጣ የማየት አለባቸው።
ፊቼ አንድ ሕዝብ በድፍረት መታደስን ሲመርጥ ምን ሊሳካ እንደሚችል የሚታይበት በዓል ነው። ይህ አዲስ ዓመት ለሲዳማ ሕዝብ ሁሌም የሚገባውን አዲስ፣ ደፋርና ባለራዕይ አመራር ይዞ ይምጣ—ሥራውን ዳር የሚያደርሱ መሪዎችን!»
03/14/2026
AYIDDE CAMBALAALLA!
**********//*************
The Sidama Diaspora Community in the Washington DC, Maryland and Virginia warmly invites all Ethiopia diaspora living in the area to join us in celebrating Fichee–Chambalaalla, the Sidama New Year. This cherished cultural tradition symbolizes renewal, unity, and the continuation of Sidama heritage across generations.
Please Join us for this joyful event as we celebrate the Sidama culture, strengthen community bonds, and welcome the New Year together.
📅 Date: March 29, 2026
⏰ Time: 1:00 PM EST
Venue: 3506 International Dr NW, Washington, DC 20008
Please share this invitation and send us your participation confirmation via (202)556-0899.
Click here to claim your Sponsored Listing.
Category
Contact the organization
Website
Address
DMV
Silver Spring, MD
20902