Maleda Media

Maleda  Media

Share

12/21/2025

ዉድ የማለዳ ሚዲያ ተከታታዮች ፦

ባለፉት አመታት ማለዳ ሚዲያ ጠቃሚና ሃቀኛ መረጃዎችንና ትንታኔዎችን ወደ እናንተ ሲያደርስ መክረሙ ይታወሳል።

ከዛሬ ጀምሮ ሚዲያችን ለተወሰነ ጊዜ መረጃዎችን ማድረስ የሚያቆም መሆኑን እያስታወቅን በአዲስ ትኩረት ፣ ይዘት እና አቀራረብ የምንመለስ መሆኑን እንገልፃለን።

እናንተ የገፃችን ተከታዮችም ያለ ማቋረጥ ለምታደርጉልን ድጋፍ እያማሰገንን መመለሳችንን እንድትጠብቁ በአክብሮት እንጠይቃለን።

መልካም የበዕላት ሰሞን ይሁንላቹ !

ማለዳ ሚዲያ

Photos from Maleda  Media's post 12/12/2025

በዩኒክ ስታር ኮሌጅ እህት ኩባንያ በሲዳማ ክልል ዳዬ ባንሳ እየተገነባ ያለ ሎጅ ተጠናቆ አገልግሎት መስጠት ባለመጀመሩ ቅር መሰኘታቸውን የአከባቢው ነዋሪዎች ገለፁ ።
******
በቦኖራ ወንዝ የአቦሬ ፏፏቴ አጠገብ እየተገነባ የነበረ ሎጅ ተጠናቆ ለጎብኚዎች አገልግሎት መስጠት ሳይጀምር ከአሥርት ዓመታት በላይ በማስቆጠሩ በአከባቢው ማህበረሰብ ቅሬታ አስነስቷል።

ቅሬታቸውን ለማለዳ ሚዲያ ያሰሙ አንዳንድ የዳዬ ከተማ ነዋሪዎች የአከባቢው ማህበረሰብ የወል ሃብት የሆኑትን ፏፏቴና የዉሃ ሃብት አጥሮ ሳያለሙ ለዓመታት ማቆየት ተገቢ እንዳልሆነ ይናገራሉ።

ጉዳዩ የሚመለከተው የመንግሥት አካላም ፕሮጀክተቶቹ ለምን በተያዘላቸው ጊዜ እንዳልተጠናቀቁ ለህዝቡ መረጃ የመስጠት ኃላፊነቱን ሊወጣ እንደሚገባ አሳስበዋል።

ቦኖራን የመሰለ ፏፏተቴ ለጎብኚዎች አገልግሎት እንዳይሰጥ በግለሰቦች ይዞታ ስም ታጥሮና ተቆልፎ መቀመጡ ለማህበረሰቡ ኪሣራ መሆኑን ያነሱት አስተተያየት ሰጪዎቹ ፕሮጀክቱ ቶሎ ተጠናቀው ለጎብኚዎች ክፍት እንዲሆንና የአከባቢው ማህበረሰብም ተጠቃሚ እንዲሆን ከመንግሥት ድጋፍና ብርቱ ክትትል እንደሚያስፈልግ ተጠቁሟል።

ማለዳ ሚዲያ

Photos from Maleda  Media's post 12/12/2025

‎”ዲሽታ ጊና “- የኣሪ ብሔረሰብ የዘመን መለወጫ ባህል እየተከበረ ነው።
****
የኣሪ ብሔረሰብ የሀገር ሽማግለዎች ከዞኑ አስተዳደር ጋር በመመካከር የዘንድሮ በዓል በማርበርግ ቫይረስ ምክንያት በአደባባይ እንደማይከበር ውሳኔ አስተላልፈዋል።

በኣሪ ብሔረሰቡ ዘንድ የአብሮነት ፣ የዕርቅና የሠላም፣ የመረዳዳትና የአዲስ ዘመን ብስራት ወቅት ተደርጎ የሚወሰደው የዲሽታ ጊና በዓል በየዓመቱ በታህሳስ ወር መግቢያ በታላቅ ድምቀት ይከበራል።

የብሔረሰቡ ተወላጆች በያሉበት ቦታ ሆነው በዓሉን እንዲያከብሩ የሚገኙ ሲሆን በሐዋሳና አከባቢው የሚገኙ የኣሪ ብሔረሰብ ተወላጆች በሱሙዳ አደባባይ ሰብሰብ አክብረውታል።

ማለዳ ሚዲያ

Want your business to be the top-listed Media Company in Seattle?
Click here to claim your Sponsored Listing.

Telephone

Website

Address


Seattle, WA
98134