Zegerami Job

Zegerami Job

Share

Photos from Zegerami Job's post 03/01/2026

🇺🇸🇺🇸🇺🇸 VS 🇻🇪🇻🇪🇻🇪
አሜሪካ ለሊቱን ሉዓላዊ ሀገር ወደሆነችው ቬንዝዌላ ገብታ ከፍተኛ ጥቃት ፈጽማ የሀገሪቱን ፕሬዚዳንት ኒኮላስ ማዱሮን እና ባለቤታቸውን ይዛ ከሀገሪቱ ወጥታለች።

አሁን ላይ ማዱሮና ባለቤታቸው ሕግ ፊት ሊቀርቡ በአሜሪካ መርከብ ወደ ኒውዮርክ እየተወሰዱ ነው ተብሏል።

ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ለፎክስ ኒውስ በሰጡት ቃል ፤ " የለሊቱን የፕሬዚዳንት ኒኮላስ ማዱሮን መያዝ ልክ እንደ ቴሌቪዥን ሾው ነበር ያየሁት " ብለዋል።

" ፍጥነቱን ብታዩ ኖሮ አስደናቂ ነበር " ሲሉ ገልጸዋል።

ዶናልድ ትራምፕ ቡድናቸው እጅግ አስደናቂ ስራ እንደሰራ አወድሰው " ከአሜሪካ ውጪ እንዲህ አይነት ኦፕሬሽን/ተግባር መፈጸም የሚችል ሌላ ሀገር ምድር ላይ የለም " ብለዋል።

Via ቲክቫህ ኢትዮጵያ

09/12/2025

👉👉👉 አሻም ሚዲያ ከጋዜጠኛ ሶፎንያስ ዋሲሁን ጋር የነበረውን የሥራ ውል አቋረጠ

አሻም ሚዲያ ትሬዲንግ አክሲዮን ማህበር ጋዜጠኛ ሶፎንያስ ዋሲሁንን ከሥራ ማገዱን ዛሬ ሕዳር 30 ቀን 2018 ዓ.ም. በሰጠው መግለጫ አስታወቀ። ውሳኔው የተላለፈው በጋዜጠኛው ላይ በማህበራዊ ሚዲያ የተሰራጨውን "ከኢትዮጵያዊነት ባሕል፣ ወግ እንዲሁም ሃይማኖት ያፈነገጠ ተግባር" የሚያሳይ መረጃ ተከትሎ ነው።

ድርጅቱ ጋዜጠኛ ሶፎንያስ ዋሲሁን በኮንትራት ውል የዜና አቅራቢና የ"ሶፊ ሾው" የመዝናኛ ዝግጅት አዘጋጅና አቅራቢ እንደነበረ ገልጿል። ይሁን እንጂ፣ ከሕዳር 29 ቀን 2018 ዓ.ም. ጀምሮ በተለያዩ የማህበራዊ ሚዲያ መድረኮች ላይ በድምጽ፣ በጽሁፍና በተንቀሳቃሽ ምስል ጭምር የተደገፈ መረጃ ሲዘዋወር መታየቱን አረጋግጧል።

አሻም ሚዲያ ይህንን መረጃ ተከትሎ ሶፎንያስን ማብራሪያ ቢጠይቀውም፣ ጋዜጠኛው "አሁን ራሴን ለማስተካከል፤ ለማከም ፀበል ገብቻለሁ" ከሚል አጭር ምላሽ ውጪ ሌላ ተጨማሪ ማብራሪያ ለመስጠት ፈቃደኛ አልሆነም።

ድርጅቱ በመግለጫው የኢትዮጵያን ባህል፣ ወግ፣ የህብረተሰቡን እሴትና ሃይማኖት የሚያከብር ኤዲቶሪያል መርህ እንደሚከተል አጽንኦት ሰጥቷል።

በመሆኑም፣ ጋዜጠኛው የተሰራጨበት ድርጊት የሚዲያውን ኤዲቶሪያልም ሆነ የማህበረሰቡን እምነትና እሴት የሚጻረር በመሆኑ፣ ድርጊቱን በጽኑ እንደሚያወግዝ እና ተቋሙን እንደማይወክል አስታውቋል።

በመጨረሻም፣ አሻም ሚዲያ ትሬዲንግ አክሲዮን ማህበር ጋዜጠኛ ሶፎንያስ ዋሲሁን በፈጸመው "ከባድ የማህበረሰባዊ እሴት እና ኤዲቶሪያል ጥሰት" ምክንያት የነበረው የስራ ውል ከዛሬ ሕዳር 30 ቀን 2018 ዓ.ም ጀምሮ መቋረጡን አሳውቋል።

Via አሻም ሚዲያ

05/12/2025

የ2026 አለም ዋንጫ የምድብ ድልድል ታወቀ።

የውድድሩ መክፈቻ ጨዋታ ሜክሲኮን ከደቡብ አፍሪካ አገናኝቷል፡፡

ሜክሲኮ ፣ ካናዳ እና አሜሪካ በጥምረት በሚያዘጋጁት 23ተኛ የፊፋ አለም ዋንጫ ውድድር ለመጀመሪያ ጊዜ 48 ሀገራትን ያሳተፈ ይሆናል፡፡

የ2026 ዓለም ዋንጫ በኢትዮጵያ አቆጣጠር ሰኔ 4 2018 ይጀምራል።

Want your business to be the top-listed Recruitment Company in Addis Ababa?
Click here to claim your Sponsored Listing.

Telephone

Website

Address


United States
Addis Ababa
85017