Awramba Times
"የፕሪቶሪያውን ስምምነት የፈረምን ሰዎች 'ክህደት ፈጽማችኋል' በሚል እንድንረሸን በህወሓት ስራ አስፈጻሚ ሐሳብ ቀርቦ ነበር። የፈረምነው ሰነድም ተቀዳዶ ይጣል ተብሎ ነበር"
ሌ/ጄነራል ጻድቃን ገብረተንሳይ
11/06/2026
ህወሓት በሚቀጥሉት ቀናት በፌዴራል መንግሥት ላይ ጥቃት ለመሰንዘር ወስኗል ሲሉ አቶ ጌታቸው ረዳ እና አምባሳደር ሬድዋን ሁሴን ገለጹ
-------
አውራምባ ታይምስ [መቐለ] - በደቡብ አፍሪካ ፕሪቶሪያ፣ በኢትዮጵያ ፌዴራል መንግሥት እና በህዝባዊ ወያነ ሓርነት ትግራይ (ህወሓት) መካከል እ.ኤ.አ በኖቬምበር 3/2022 የተፈረመውን የሰላም ስምምነት፣ "ጽንፈኛ" ያሉትን የህወሓት ቡድን በይፋ መሻሩንና በሚቀጥሉት ጥቂት ቀናት ከፌዴራል መንግስት ጋር ቀጥተኛ ወደሆነ ወታደራዊ ግጭት ለመግባት መወሰኑን ሁለቱንም ተደራዳሪ አካላትን ወክለው በደቡብ አፍሪካ ሰነዱን የፈረሙት ኃላፊዎች ገለጹ።
የጠ/ሚ አብይ የምስራቅ አፍሪካ ጉዳዮች አማካሪ ሚኒስትር አቶ ጌታቸው ረዳ እና የብሄራዊ መረጃና ደህንነት አገልግሎት ዋና ዳይሬክተር የሆኑት አምባሳደር ሬድዋን ሁሴን በዛሬው እለት አልጀዚራ ላይ ባሳተሙት የጋራ ፅሑፍ እንዳመለከቱት፤ በትግራይ ክልል የሚገኘውና "በሻዕቢያ የሚደገፍ ጽንፈኛ" ሲሉ የገለጹትን የህወሓት ስብስብ፣ ሕጋዊውን የክልል ጊዜያዊ አስተዳደር በመበተን የራሱን መዋቅር ዘርግቷል ሲሉ ከሰዋል። ይህ የህወሓት ክንፍ የፕሪቶሪያውን የሰላም ስምምነት ወደ ጎን በመተው፣ በትግራይ ወጣቶች ላይ አስገዳጅ የውትድርና ምልመላ እያካሄደ እንደሚገኝና ክልሉን ወደለየለት የእልቂት አውድማ እያሸጋገረው መሆኑን አስታውቀዋል።
ይህ ቡድን በአስመራው አገዛዝ ቀጥተኛ ድጋፍ እየተመራ እንደሚገኝ ደጋግመው የጠቀሱት ጸሐፊዎቹ፤ ሁለቱም አካላት የፕሪቶሪያውን ስምምነት ለማፍረስ “ጽምዶ” የተሰኘ ስውር ጥምረት መመስረታቸውንም አብራርተዋል። "ይህ ጽንፈኛ የህወሓት ክንፍ በአስመራ አጋዥነት በቅርብ ቀናት ውስጥ በፌዴራል መንግሥቱ ላይ አዲስ ወታደራዊ ጥቃት ለመሰንዘር ዝግጅት እያጠናቀቀ ነው" ሲሉም ኃላፊዎቹ አብራርተዋል።
በመሆኑም ይላሉ ጸሐፊዎቹ፣ በመሆኑሞ ዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ በህወሓት እና በአይዞህ ባይ ደጋፊዎቹ ላይ ጠንካራ ዲፕሎማሲያዊ ጫና ሊያደርግ እንደሚገባ በማሳሰብ፣ ላለፉት ጥቂት አመታት ለህዝቡ እፎይታ የሰጠውን የፕሪቶሪያውን ስምምነት በኃይል ለመለወጥ የሚደረገው አደገኛ አካሄድ ቀጣናውን ወደ ከፋ የፖለቲካ ቀውስ እንዳይከተው በዚሁ ጽሁፋቸው ስጋታቸውን ገልጸዋል።
Click here to claim your Sponsored Listing.
Category
Contact the business
Telephone
Website
Address
700 Bellevue Way NE
Addis Ababa
98004