Kallu press
11/14/2019
!
አሁን ከምሽቱ 7:10
-----------
በተማሪዎች መካከል የተፈጠረ የዘርም ይሁን የሃይማኖት ግጭት የለም። የወንዶች ዶርም አከባቢ ተማሪዎች ባሰሙት የረብሻ ድምጽ የተደናገጡ ተማሪዎች ሲሮጡ የወደቁና መኖራቸውን አውቀናል።
ይሄንን መደናገጥ እንደ ግብዓት በመጠቀም አላስፈላጊ የሂወትና ሃብት ኪሳራ እንዲፈጠር የሚደረገው ፕሮፓጋንዳ መቆም አለበት።
በተማሪዎች መካከል የተፈጠረ አንዳች ግጭትም ይሁን አለመግባባብት አለመኖሩን በቦታው የሚገኙ ተማሪዎች ምስክሮች ናቸው።
ተማሪዎች ያልተለመደ የረብሻም ይሁን መሰል ድምጽ ሲሰሙ ወይም ሲያጋጥማቸው መረጋጋትና እራሳቸውን መጠበቅ አለባቸው። በሚሰሙት ጩኸት ወይም ረብሻ ተደናግጠው በቡድንም ይሁን በተናጠል በጨለማ ከግቢ መውጣት፣ በጨለማ መሮጥ፣ ከህንጻ ላይ መዝለል ፈጽሞ የለባቸውም። ያልተለመደና ለደህንነታቸው ስጋት የሚሆን ጉዳይ ከገጠማቸው በዶርሞቻቸው ዙሪያ ያሉ የጸጥታ አካላትንና ሰራተኞችን እርዳታቸውን ይጠይቁ።
--------
ወሎ ዩኒቨርሲቲ በተማሪዎች መካከል የተፈጠረ የዘርም ይሁን ሌላ አይነት ግጭት የለም። ተማሪዎች በአይናቸው ባላዩት ጉዳይ በማህበራዊ ሚዲያ የሚለቀቅን አጥፊ መልዕክት፣ ድብቅ አላማ ያላቸውን ተማሪዎች ጥሪ ወይም መረጃ ተከትለው ያልተገባ ውሳኔ እንዳይወስኑ ይጠንቀቁ።
Click here to claim your Sponsored Listing.
Category
Telephone
Website
Address
Atlanta, GA
92