T KDM

T KDM

Share

Photos from T KDM's post 15/12/2020
05/11/2020

ግፍ እና ጎርፍ
ሰሚ ካጡ የሶማሌ ተረቶች አንዱ እንዲህ ይላል፡፡
አንድ ሰው የጠፋች የአካባቢውን ግመል ፍለጋ ጫካ ይገባል፡፡ ከብዙ መከራ
በኋላ ያቺን ግመል አግኝቶ ከተማ ገባና ግመሏን ለባለቤቱ ሳይመልስ ሐሳቡን
ቀይሮ ራሱ ያልባትና ይጋልባት ጀመር፡፡ ግመሏን ከአውሬ ለማዳን ጫካ ገብቶ
የነበረው ሰውዬ እርሱ ራሱ ግመሏን መውሰዱ ብዙዎችን አስገረማቸው፡፡ ትንሽ
ቆየና ከዚያች ከአንዷ ግመል ወተት እያለበ በግመሏ ላይ ተቀምጦ እየዞረ
ለአካባቢው ሰው ወተት መሸጥ ጀመረ፡፡ ነገር ግን የግመሏ ወተት በአንድ ጊዜ
ሀብታም ሊያደርገው አልቻለምና ሌላ ነገር አሰበ፡፡ በወተቱ ውስጥ ውኃ
እየጨመረ ቀላቅሎ መሸጥ፡፡ ‹‹ሰውም ምነው የሰውየው አመሉም ወተቱም
ተቀየረሳ›› እያለ ዝም ብሎ ይገዛ ጀመር፡፡ (ይገዛ የሚለው ቃል ጠብቆ
እንዳይነበብ አሳስባለሁ)
ሰውዬውም በግመል ወተቱ ላይ ውኃን እያበዛው፤ የግመሉም ቁጥር እየጨመረ
ሄደ፡፡ እየቆየም በግመልና በግመል ወተት ከሚታወቁት የሀገሩ ነጋዎች በላይ እኔ
ነኝ ያለ፣ ቢጠሩት የማይሰማ ሀብታም ሆነ፡፡ የአካባቢው ሰዎችም ‹‹ይኼ ሰው
ትናንት ምንም አልነበረውም፡፡ የጠፋ ግመል ሊፈልግ ጫካ ገባ፤ ተመልሶ መጣ፤
ከተማ ገባ፤ በአንድ ጊዜ ተመነደገ›› እያሉ ይገረሙ ነበር፡፡ ወተት ብቻ ተሽጦ
እንዴት በሁለት ዓመት ሦስት መቶ ግመል ሊገዛ ቻለ፡፡ የሚለው የሕዝቡ ሁሉ
ወሬ ሆነ፡፡
ሰውዬው ግን ምንም አልመሰለው፤ በወተቱ ውስጥ ውኃውን እየጨመረ ቀጠለ፤
እንዲያውም እበላ ባይ ቱልቱላዎችን ቀጠረና የእርሱ ወተት ሰው ጠጥቶት
የማያውቅ መሆኑን እንዲለፍፉ አደረ፡፡ አንዳንድ ጊዜ እንዲያውም ወተቱን
ለመልኩ ብቻ ይጨምርበትና የቀረው ውኃ ያደርገው ነበር፡፡ ‹‹ኧረ ሕዝቡ
እያማረረ ነው፤ በአንድ በኩል በድንገት ተነሥህ፤ ከተማ ገብተህ ቢጠሩህ
የማትሰማ ሀብታም ሆንክ፤ ይኼንን ስንታገሥህ ደግሞ ወተቱን ቀንሰህ ውኃውን
እያበዛህ መሸጥ ጀመርክ፡፡›› ሲሉት ‹‹ተውት ባካችሁ፣
ለመሆኑ የእኔን ወተት ከመግዛት ውጭ ሕዝቡ ምን አማራጭ አለው፤›› ይል
ነበር፡፡ በወተቱ ውስጥ የሚጨመረው ውኃም እየበዛ፣ ግመሎቹም እየበዙ ሄዱ፡፡
ግመሎቹም ሀገሩን ሞሉት፡፡ የሚያድሩበትና የሚግጡበት ልዩ የከተማ መሬት ተሰጣቸው፡፡ ወንዝ ዳር የሚገኝ ለም መሬት፡፡
አንድ ቀን ሸበሌ ወንዝ አጠገብ ግመሎቹን አሠማርቶ እርሱ አንድ ዛፍ ጥላ ሥር ሻሂ ከልጁ ጋር ይጠጣ ነበር፡፡ በዚህ መሐል ከደጋ የዘነበ ዝናብ ወንዙን ሞላውና በግራ በቀኝ ሲግጡ የነበሩትን ግመሎች ጠራርጎ ወሰዳቸው፡፡ የጎርፉን ድምጽ ሰምተው አባትና ልጅ ከጥሻው ሲወጡ ግመሎቻቸው ሁሉም ተወስደዋል፡፡
እሪታውን ሰምተው የተሰበሰቡ የሀገሩ ሰዎችም በአግራሞት የሆነውን ነገር ይመለከቱ ነበር፡፡
‹‹አየህ›› አሉት አንድ አዛውንት ‹‹ያ በወተቱ ላይ እየጨመርክ የሸጥከው ውኃ ተጠራቅሞ፣ ተጠራቅሞ ጎርፍ ሆኖ ግመሎቹን ወሰዳቸው፡፡ ግፍ እንደዚህ ነው፡፡ ሲሠራ ቀላል ይመስላል የተጠራቀመ ዕለት ግን ጎርፍ ሆኖ ይወስዳል፡፡ ተው ብንልህ አልሰማ ብለህ ነበር፤ አንተ በግፍ ግመል ስትሰበስብ የግፉ ውኃ ሌላ ቦታ እየተሰበሰበ መሆኑን ረስተህዋል፡፡ ቀን ጠብቆ ግን ይሄው ጎርፍ ሆኖ መጣ››
አሉት፡፡

02/09/2020

❀━┅┉┈ያንተን ሪዝቅ ማንም አይበላውም┈┉┅━❀
አንድ ሰውዬ ነበር በአንድ ካንፓኒ ተቀጥሮ በሚሰራው
እናቱን ሚስቱን እና ልጆቹን ያስተዳድራል።
ዘውትር ስራውን በአግባብ እና በእምነት ለአለቃው
ይሰራ ነበር።
እናም አንድ ቀን ሙሉ ስራ ሳይገባ ይቀራል...
የካንፓኒው ባለቤትም፦"በርግጠኝነት ክፍያ አንሶት
ነው የቀረው ስለዚህ ነገ ሲመጣ ክፍያ
እጨምርለታለሁ።" ብሎ ይወስናል።
በነጋታው ይህ ሰው ስራ ቦታ ከመግባቱ ክፍያውን ከነ
ጭማሪው ሰጠው።ቆጥሮ ተቀበለው።
ግን ስለጭማሪው ምንም አልደነቀውም ለምን ክፍያ
እንደተጨነረለትም አለቃውን አልጠየቀም...ዝም ብሎ
ስራውን ቀጠለ።
ለተወሰኑ ቀናት እንደበፊቱ ስራውን በአግባብ ሰራ'ና
የሆነ ቀን ስራ ሳይገባ ቀረ።
አለቃው በቃ የለለ ተቆጣ የጨመረለትንም ደሞዝ
መልሶ ቀነሰበት።
እናም በማግስቱ መጣ ስራውን ጨርሶ ክፍያ
ሲቀበለው የጨመረለትን እንደቀነሰ አወቀ አሁንም
ምንም ሳይል ትቶ ወጣ።
በሰራተኛው ሁኔታ የተገረመውም አለቃው፦"ባለፈው
ክፍያ ስጨምርልህ ምንም አላልክም ዛሬም
ስቀንስብህ ምንም አይነት ጥያቄ አላቀረብክም
ለምንድነው?" ብሎ ጠየቀው።
እሱም፦"የመጀመሪያ ግዜ ስራ የቀረሁት የዛን ቀን
አላህ ልጅ ረዝቆኝ ነው(ምስቴ ወልዳ)።ያን ቀን ደሞዝ
ስትጨምርልኝ ስለጭማሪው ያልጠየቅኩህ የደሞዙ
ጭማሪ ያ አዲስ ለተወለደው ህፃን አላህ የመደበለት
ሪዝቅ እንደሆነ ስላወቅኩ ነው።
ትናንት ስራ የቀረሁት እናቴ ሞታ ነው።
አሁን ደሞ ደሞዝ ስትቀንስብኝ ዝም ያልኩት ያ ከዚህ
በፊት ትበላው የነበረው የእናቴ ሪዝቅ በሷ መሞት
ምክንያት አላህ አቋርጦት እንደሆነ ስላወቅኩ
ነው።"ብሎ መለሰለት።
❀━┅┉┈ሱብሀን አላህ┈┉┅━❀

Want your school to be the top-listed School/college in Jeddah?
Click here to claim your Sponsored Listing.

Category

Telephone

Website

Address


Jeddah