Yeney Tube

Yeney Tube

Share

Nearby schools & colleges

POPs Games
POPs Games
Dairy Flat,

Photos from Yeney Tube's post 05/12/2023

++ ባለ አህያው ሰው ++

(በሊቀ ሊቃውንት ስምዐኮነ መልአክ)
( ከተማራችሁበት ሼር አድርጉት )

ደግነት ላልተሰጠው ሰው የአሚናዳብ ሠረገላ ቢኖረውም ምንም ታሪክ አይኖረውም። ባሕርዩን በደግነት ቅኝት ቃኝቶ ለሚኖር ሰው ደግሞ አህያም ቢሆን ባለው ነገር ያገለግላል እንጅ የአሚናዳብ ሠረገላ እስኪሰጠው ድረስ አይጠብቅም። እግዚአብሔር እንደ ፈርዖን በየዕለቱ የምንጠፈጥፈውን ጡብ ካልሞላችሁ ብሎ አስገባሪዎችን ልኮ አያስገርፈንም።

የምንችለውን ብንሠራ ደግሞ ከሠራነው በላይ ከፍ ከፍ ያደርገናል። ምንም እንኳን ያላገለገሉትን የማያስጨንቅ፤ የሠሩትን በጸጋ የሚያከብር አምላክ መሆኑን ብናውቅም የኛን መምጣት የሚጠብቁ አገልግሎቶች በመንገዳችን ላይ አሉ። ምናልባትም ከኛ ቀድመው በዚያ መንገድ ያለፉ ሰዎች አይተው ቸል ብለው ያለፏቸው አገልግሎቶች ሊሆኑ ይችላሉ። እኛም ቢሆን ለዚያ ብለን በዚያ መንገድ ላይ መራመድ አልጀመርንም ግን እግዚአብሔር በዚያ መንገድ ላይ እግረ መንገዳችንን ወደ መንግሥተ ሰማያት የምናቀናበትን ዕድል ፈጠረልን።

የያዝነው መሣሪያ፣ የጫንነው አህያ፣ የቋጠርነው ስንቅ፣ የመቀነታችን ወርቅ፣ የማሰሯችን ዘይት፣ የከረጢታችን ዱቄት ከኛ አልፎ ለሌላ አይተርፍም ብለን አስበን ይሆናል − ከቤታችን የወጣነው። ድንገት ግን፥ ፊታችን ላይ ካለን ነገር ልናካፍለው የሚገባን ሰው ያጋጥማል። ሽፍቶች የጨከኑበት፤ መንገዱን ያሰናከሉበት፤ ዓላማ የነበረው፤ ነገር ግን ለዓላማው መሳካት በሚያደርገው ትግል ላይ ሳለ ድንገት ላይነሣ የወደቀ ሰው ታገኙና የእናንተ እርዳታ ሊያስፈልገው ይችላል። ደግፋችሁ እንዳታቆሙት መቆም አይችልም። ወይም የያዛችሁት ሠረገላ እንደ ባኮስ ሠረገላ ለሱም ለእናንተም የሚበቃ ሆኖ ወጥቶ ከእናንተ ጋር እንዲቀመጥ አታደርጉት፤ አስቸጋሪ ነገር ነው ሥራ 8፥31።

ደጉ ሣምራዊ ይሄ ሁሉ አይፈትነውም፤ ከአህያው ወርዶ በቁስሉ ላይ ዘይቱን አፍስሶ ያነሣዋል እንጅ ከዚህ በፊት እንደመጡት ሰዎች አልፎት አይሄድም። ይህንን ሰው አይቶ ቸል ብሎ ማለፍ ከደበደቡት እና ካቆሰሉት ሽፍቶች በምን ይለያል?

ለማንኛውም ከኢየሩሳሌም ወደ ኢያሪኮ የሚወርደው ደጉ ሣምራዊ በሕይወት አጋጣሚ አንዳንድ ጊዜ የሚያጋጥም ነው እንጅ ሁልጊዜ በመካከላችን አይኖርም። በዝተው ዕለት ዕለት የምናገኛቸው፥ ከፍ ሲል፡− በገዛ የሕይወት መንገዳችን ደርሰው ራስ ራሳችንን የሚቀጠቅጡን ሽፍቶችን ነው። ዝቅ ሲል ደግሞ፡− መቀጥቀጣችንን መጎዳታችንን እያዩ ቸል ብለው የሚያልፉንን ሌዋዊውንና ካህኑን ነው። አንተ የምትጠቀምበትን መንገድ ለመዝጋት ሲያስቡ እጃቸው ላይ ያለውን ሕግ ጠቅሰው ያሰናክሉሃል፤ ማቴ 12፥2። በግል ሕይወታቸው ግን ሕጉን ያውቁታል እንጅ ሕጉን ስለማይኖሩበት “የሚጠላህን ሰው አህያ ከሸክሙ በታች ወድቆ ብታየው አትተወው ነገር ግን ከእርሱ ጋር አንሣው” ዘጸ 23፥5 የምትል ሕግ እያስተማሩ እንኳን ለአህያው ለሰው የማይራሩ ጨካኞች ናቸው።

እኛ ግን እነሆ ባለ አህያውን ሰው አግኝተነዋል! ደጉ ሣምራዊ በዘመናችን ከዚህ ሌላ እንዴት ሆኖ ሊመጣ ይችላል? ሽፍቶች የቀጠቀጡትን ልባችንን በቁስሉ ላይ ከዘይቱ አፍስሶ ጥዝጣዜውን አራቀለት። ከአህያው ላይ ወርዶ በአህያው ላይ ጭኖ ወደ ባለምድኃኒት ያመጣቸው ብዙ ናቸው። መጀመሪያ በአሜሪካ ያየነውን ደግነቱን ይሄው ዛሬ ደግሞ በዐረቡ ምድር ደገመው። ተስፋ መቁረጥ የሚሉት ሽፍታ ላደቀቀው ሕዝብ እንዲህ ያለ ደግነት ከወዴት ይገኛል? ለዚህ ሕዝብ ከቤተ ክርስቲያን በላይ ዘይትና መድኃኒት ከየት ይገኝለታል? የቆሰሉ ሰዎች የሚጫኑባት ይህች donkey የተባረከች ትሁን።

ለካ ለአዲሱ ትውልድ እግዚአብሔር አዲስ የጽድቅ መንገድ ያዘጋጃል? በእውነት እኔ አዝን ነበር ይሄ የዘመናችን ሰው እንግዶችን በእግዚአብሔር ስም ተቀብሎ በቤቱ እንዳያስተናግድ ለራሱና ለእንግዶች የሚበቃ ቤት የለው፥ በዚያውም ላይ እንደ አባቶቻችን ዘመን እንግዶችን ወደ ቤታችን ወስደን ለማሳደር ብዙ አስቸጋሪ ነገሮች አሉብን፥ እንኳን የማናውቃቸውን ይቅርና የምናውቃቸውንም ወስደን ለማሳደር የምንቸገርባቸው ብዙ ዘመን ያመጣቸው ጉዳዮች መኖራቸው ግልጽ ነው። በዚህ ምክንያት ይሄ የኔ ዘመን ጎጆውን የተቀማ ትውልድ “እንግዳ ብሆን አልተቀበላችሁኝም” ተብሎ ይፈረድበት ይሆን? ብየ አዝን ነበር። እግዚአብሔር ለካ ሌላ የጽድቅ መንገድ አዘጋጅቷል። ሰይጣን የጽድቅ መንገዶችን ሲያጠብብን እግዚአብሔር በሌላ በኩል አሰፋልን።

አሁን ዓለም በወንበዴዎች እጅ ወድቋል፤ ምሕረት በሌላቸው ኃያላን በትር ተመትቶ ደቋል፤ ቀድመው የከፍታ ቦታውን የያዙ ኃያላን አዲሱን ትውልድ መውጫ መግቢያ አሳጥተውታል። ትምህርቱን፣ ጉርብትናውን፣ ትዳሩን፣ ንግዱን፣ ኑሮውን፣ መዝናናቱን እና ሌላውንም ሞራል አልባ አድርገውታል። ቤተ ክርስቲያን የምታስፈልገው ትውልድ ከቀድሞው ይልቅ ያሁኑ ይመስለኛል። ለቀደሙት ሰዎች የምታስፈልገው ለክርስቲያኑ ወይም የሚመጣውን ሕይወት ተስፋ ለሚያደርጉት ነበረ። አሁን ግን በምድር ለሚኖር ፍጥረት ሁሉ ታስፈልጋለች። የኖኅ መርከብ የምታስፈልገው ለኖኅና ቤተ ሰቡ ብቻ እንዳልሆነ ታውቃላችሁ።

ባሕርይዋ የማይለወጥ ቤተ ክርስቲያናችን ጠባዩን ለለወጠው ዓለም ታስፈልገዋለች። አንዳንድ ሰዎች አሜሪካ ውስጥ ገዳም መሥራት ምን ያደርግልናል ሲሉ እንሰማ ነበር እኛ ኢትዮጵያውያን አሜሪካን በሃይማኖት ነው እንጅ በሌላ በምን ልንረዳት እንችላለን? ያጣችው ሃይማኖት ነው እንጅ ሌላውማ አላት። ወረርሽኝ በበዛበት አካባቢ የጤና ኬላ አብዝቶ ማቋቋም የሚድኑትን ያበዛል እንጅ ጉዳት የለም። የሠለጠነውን ዐለም ያኽል በዲያብሎስ የጥርስ ንክሻ የገባ ያለ አይመስለኝም ስለዚህ ገዳማት አድባራትን በውስጣቸው ብንሠራ ኪዳኑ፣ ቅዳሴው፣ ዕጣኑ መሥዋዕቱ ከጠላት ንክሻ ሊታደጋቸው ይቻለዋል።

ቤተ ክርስቲያን ካልደረሰችለት ዓለም ለጥፋት እየተቃረበ ነው። ወንበዴዎች ቀጥቅጠው በጎዳና ጥለው ልብሱን ገፈው ጥለውት ሲሄዱ እያየን ነው። በዶንኪ ቲዩብ እየተሠራ ያለው መልካም ሥራ የደጉ ሣምራዊን ሥራ የሚመስል ነው። ባለቤቱም እንደ ደጉ ሣምራዊ ነው። ከአህያው ወርዶ ማለትም ራሱን ከመጥቀም ወጥቶ ምዕመናን መጽናኛ የሚያገኙበት ቤተ ክርስቲያን በኳታር እንዲሠራ ማድረጉ የሚደነቅ ሣምራዊነት ነው። በዓለም ሁሉ ያሉትን ሰዎች ለበጎ ነገር ማነቃቃት መታደል ነው። በዚህ ስፍራ እግዚአብሔርን አግኝተው ንስሐ ገብተው ኃዘንተኛ የነበሩት ተጽናንተው ስታይ እንዴት ልብህ ትደሰት ይሆን? አንተ ደግ ሣምራዊ ያንተ ደስታ ማንም የማይቀማህ ደስታ ነው።

አንተ የምትደሰተው ጠላቶቻቸውን በዘመናዊ መሣሪያ አጥፍተው እንደሚደሰቱ የዓለም ኃያላን መንግሥታት አይደለም ከምዕመናን ጠላቶቻቸው አጋንንት ጠፍተውላቸው በማየትህ ነው እንጅ። ዓለም ሕዝቦቿን ስደተኛ እያደረገች ባለችበት በዚህ ዘመን ለስደተኞቹ ምዕመናን መኖሪያ የሚሆን የእግዚአብሔር ቤት ነው ብሎ አስቦ መሥራት እንዴት ያለ መታደል ነው? አወ ከዚህ በኋላ መዕመናን ልባቸው በዚያ ያድራልና ማደሪያ አልባዎች አይሆኑም። ዓለም በራሷ እጅ የሠራቻቸውን ከተሞች በራሷ እጅ እያጠፋች ባለችበት ወቅት የሰዎችን ተስፋ መገንባት መታደል ነውና ለታደልኸው ላንተ በተቀደሰ ሰላምታ ሰላም ብያለሁ። የደረስህላቸው ገዳማት ስላንተ ቀኑን ሙሉ እጃቸውን ዘርግተው ጸሎት እንደሚያደርሱ አንዳንዶችን ከቦታው ሂጀ አይቻለሁ።

በወንጌል ታሪኩ የተጻፈውን ባለ አህያውን ሰው አግኝተነዋል፡− የ donkey tyube መሥራች እሸቱ መለሰ ነው። አብረውት የሚሠሩ መምህራንና መዘምራንም “ከዚህ በላይ የምታወጣውን ሁሉ እኔ ስመለስ እከፍልሃለሁ” የተባለውን የጌታን ቃል ተስፋ አድርገው የሚሠሩ ናቸው። ጌታ እስኪመጣ ድረስ የቆሰለውን ዓለም ለማዳን የተላኩ መልዕክተኞች ናቸው። ሉቃ 10፥25−37

(ሊቀ ሊቃውንት ስምዐ ኮነ መልአክ)

Photos from Yeney Tube's post 07/02/2023

ደቡብ tv
ቃና tv
አማራ tv
ናሁ tv

እናመሰግናለን ... ሌሎችንም እንጠብቃለን...

Want your school to be the top-listed School/college in Auckland?
Click here to claim your Sponsored Listing.

Category

Address


Auckland
1025