Visit Woliso

Visit Woliso

Share

Photos from Wonchi Tube's post 12/10/2025
11/09/2025

የኢፌዴሪ አየር ኃይል አዛዥ ሌተናል ጄኔራል ይልማ መርዳሳ የአዲስ ዓመት መልዕክት

የተከበራችሁ የኢትዮጵያ ህዝቦች የመከላከያ ሠራዊት አባላት እንዲሁም መላው የተቋሙ ሲቪል ሰራተኞች
በቅድሚያ እንኳን ለ2018 አዲስ ዓመት በሰላም አደረሳችሁ።

በተጠናቀቀው 2017 ዓመት ሀገራችን በሰላም በልማት በኢኮኖሚ ዕድገትና በማህበራዊ መስኮች ታላላቅ ስኬቶችን ያስመዘገበችበት የድል ዓመት መሆኑ ይታወሳል። በተለይም መላው ኢትዮጵያዊ እና ጀግናው ሰራዊታችን ደሙን ላቡን ጉልበቱንና እውቀቱን ከማፍሰስ ባሻገር ቦንድ በመግዛት የራሱን ታሪካዊ አሻራ ያሳረፈበት ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ በታላቅ ድምቀት ተመርቆ በይፋ ስራ የጀመረበት እና አየር ኃይላችንም ከተቋማዊ ሪፎርሙ ወዲህ የጀመራቸውን የለውጥ ጉዞዎች አጠናክሮ የቀጠለበት ነው።

የተቋሙን የዝግጁነት አቅም ለማሳደግ ያከናወናቸው ተግባራት ከዓመቱ አመርቂ ድሎቻችን ውስጥ የሚጠቀሱ ሲሆን ሰራዊታችንም የአስተሳሰብ ለውጥ በማምጣት የአመራሩንም ሆነ የአባላቱ ስነ ልቦና በማሳደግ የሚሰጠውን ተልዕኮ ለመወጣት የሚያስችል ቁመና እንዲይዝ ተደርጓል።

የኢትዮጵያ አየር ኃይል የተመሰረተበትን 90ኛውን አመት በተለያዩ ዝግጅቶች በድምቀት ለማክበር በዝግጅት ላይ ይገኛል።

በመጨረሻም አዲሱ ዓመት የተጣለብንን ሀገራዊ ኃላፊነት ከመቼውም ጊዜ በላቀ ወትሮ ዝግጁነት የምንወጣበት እንደሚሆን በመተማመን ለመላው የሀገራችን ህዝቦች ለጀግናው የሀገር መከላከያ ሰራዊታችንና ለአየር ኃይል አባላት የሰላም የዕድገትና የብልፅግና ዘመን እንዲሆንልን እመኛለሁ አመሰግናለሁ።

Photos from Addisu Arega Kitessa's post 06/07/2025
08/09/2024
Want your business to be the top-listed Travel Agency in Woliso?
Click here to claim your Sponsored Listing.

Telephone

Website

Address


Woliso
Woliso