Apostolic generation
ማርቆስ 12
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
²⁹ ኢየሱስም መልሶ እንዲህ አለው፦ ከትእዛዛቱ ሁሉ ፊተኛይቱ፦ እስራኤል ሆይ፥ ስማ፤ ጌታ አምላካችን አንድ ጌታ ነው፥
³⁰ አንተም በፍጹም ልብህ በፍጹምም ነፍስህ በፍጹምም አሳብህ በፍጹምም ኃይልህ ጌታ አምላክህን ውደድ የምትል ናት። ፊተኛይቱ ትእዛዝ ይህች ናት።
15/03/2026
ከታች ያለውን የ Telegram channel join አድርጉ በየቀኑ single መዝሙሮች በኮንፈረንስ የተሰበኩ ስብከቶች እና የፅሁፍ ትምህርት ይለቀቃል
join አድርጉ
👉https://t.me/ApostolicchurchofAreka
👉https://t.me/ApostolicchurchofAreka
15/03/2026
የዓለም አቀፍ ጉባኤ
#ዋራ
በኢትዮጵያ ሐዋርያዊት ቤተክርስቲያን 35ኛው ዙር በስዳማ ክልል ዋራ በሚባል ቦታ ሐዋርያዊት ቤተክርስቲያን ታላቅ መንፈሳዊ ጉባኤ ከ ሐሙስ ጀምራ እያካሄደች ትገኛለች።
በጉባኤ ከተለያዩ ሀገራት ኢትዮጽያዊ ያልሆኑ ነገር ግን ሰማያዊ ዜጋ የሆኑት ኢትዮጵያን እግዚአብሔር እንደባረካት እና ይህ ድንቅ ሥራ ወደ እኛም ይደርስ እያሉ እየመሰከሩ ይገኛሉ።
ይህ ጉባኤ ነገ እሁድ ማለትም 6/07/2018 ዓ.ም የመጨረሻ ስለሆነ ሁላችሁም የበረከት ተካፋይ እንድትሆኑ በክርስቶስ ፍቅር ተጋብዛችኋል።
በሌላ በኩል በኮንፈረንሱ እየተከናወነ ያለው ተአምራት ይህን ያህል ነው ለማለት እና ለመገለፅ የሚከብድ ቢሆንም በእኛ ቤት አድራጊ ራሱ ኢየሱስ ነው የ ተአምራት ባለቤት ስሙ ይመስገን።
ስለሆነም አንዳንድ ትምህርት የያዙት ነገሮችን ለውስጥ የሚናገር እና ለውጭ የሚናገሩትን ታሳብ በማደረግ ያሉትን ትምህርትና ፕሮግራሙን መጨረሻ ወደ እናንተ እናደርሳለን።
በዚህ ቦታ በመኖሬ ዕድለኛ ነኝ🙏
International conference
In the 35th round of the Ethiopian Apostolic Church, the Apostolic Church is holding a great spiritual conference starting from Thursday at a place called Wara in Sadama region.
In the conference, non-Ethiopians from different countries, but who are heavenly citizens, are testifying saying that God has blessed Ethiopia and that this wonderful work will reach us.
This conference will end tomorrow, Sunday, 6/07/2018, so all of you are invited by the love of Christ to be part of the blessing.
On the other hand, the miracles that are happening at the conference are so much that it is difficult to say and explain, but it is Jesus himself, the maker of our house, praise be to the owner of miracles.
Therefore, we bring to you the end of the lesson and the program, which contains some things that speak inwardly and those that speak outwardly.
I am lucky to live in this place
ከታች ያለውን የ Telegram channel join አድርጉ በየቀኑ single መዝሙሮች በኮንፈረንስ የተሰበኩ ስብከቶች እና የፅሁፍ ትምህርት ይለቀቃል
join አድርጉ
👉https://t.me/ApostolicchurchofAreka
👉https://t.me/ApostolicchurchofAreka
27/02/2026
“እግዚአብሔር #ሙላቱ ሁሉ #በእርሱ እንዲኖር፥ በእርሱም በኩል በመስቀሉ ደም ሰላም አድርጎ በምድር ወይም በሰማያት ያሉትን ሁሉ ለራሱ እንዲያስታርቅ ፈቅዶአልና።”
— ቆላስይስ 1፥19-20
አንዱ እግዚአብሔር ሙልአቱን ሁሉ በእርሱ አድርጓል
ይህ እርሱ የተባለው ማነው ከተባለ ፤ በሁለተኛው ምዕራፍ ቁጥር 9 ላይ 👉ሰውነት ይለዋል
“For it pleased the that in him should all fulness dwell;”
— Colossians 1:19 (KJV)
father means 👉አብ
him የተባለው 👉ወልድ or bodily
“For in him dwelleth all the fulness of the Godhead bodily.”
— Colossians 2:9 (KJV)።
መልካም እግዚአብሔር ሙልአቱን በሰውነቱ ሲያደርግ በዚህ ሰውነቱ ምን ምን አከናውኗል?
1ኛ.....በልጁ ሆኖ ተናግሮናል ዕብ 1፥1
ለዚህም የሚመሰክርልን ራሱ ኢየሱስ ሲሆን ፤ እንዲህ ይለናል
“የማይወደኝ ቃሌን አይጠብቅም፤ የምትሰሙትም ቃል የላከኝ #የአብ ነው እንጂ #የእኔ አይደለም።”
— ዮሐንስ 14፥24
ዮሐንስ 14
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
¹⁰ እኔ #በአብ እንዳለሁ አብም #በእኔ እንዳለ አታምንምን? እኔ የምነግራችሁን #ቃል #ከራሴ አልናገረውም፤ ነገር ግን በእኔ የሚኖረው አብ እርሱ ሥራውን ይሠራል።
¹¹ እኔ በአብ እንዳለሁ አብም በእኔ እንዳለ እመኑኝ፤ ባይሆንስ ስለ ራሱ ስለ ሥራው እመኑኝ።
እሺ የስላሴ አማኞች በእናንተ ትንተና መሰረት ከሄድን ወልድ ራሱን ችሎ በራሱ #እውቀት #ፈቃድና $ስሜት የሚኖር የተለየ ማንነት ሲሆን አብም in Christ ሳይሆን out Christ ሆኖ ይኖራል የሚል ነው
ታድያ በራሱ ስሜት ፈቃድና እውቀት የሚኖር ሌላ እግዚአብሔር ከሆነ ከራሱ መናገር አለመቻሉ እርሱን ማን ያደርግልናል?
ሰው ብቻ ስለሆነ ነው ከራሱ ማይናገረው?
አዎን ካላችሁ =>>አምላክ ነው የሚለውን የመጽሀፍ ቅዱስን ምስክርነትን የት ልንሸሽገው እንችላለን? ፤
አይ ሌላ እግዚአብሔር ነው ግን አብ ያልሆነ እግዚአብሔር ካላችሁ ፤ እግዚአብሔር ከራሱ መናገር የማይችለው እንዴት ነው?
ሲቀጥል እኔ በአብ እንዳለሁ አብም በእኔ እንዳለ የሚለው የኢየሱስ አስተምህሮት ፤ አብ ከክርስቶስ ውጪ እንዳለ ፤ ወልድም free of God እንደሆነ እመኑ የሚለው የእናንተን አስተምህሮት በምን በኩል አልፈው ሊገናኙ ነው?
2ኛ.....እግዚአብሔር አብ በልጁ (በሰውነቱ ተተረከ ታየ ) ዮሐ 1፥18
እግዚአብሔር አብ በክርስቶስ አልተገለጠም የሚለው የእናንተ አስተምህሮት ከየት የመጣ ነው?
3ኛ....እግዚአብሔር አብ በልጁ (በሰውነቱ) እኛን ከራሱ ጋር አስታረቀ ....2ኛ ቆሮ 5፥19
እግዚአብሔር አብ በሰውነቱ ሆኑ ከራሱ ጋር አላስታረቀንም የሚለውን የእናንተን ዶክትሪንን አምነን እንቀበለው ዘንድ ፤ 2ኛ ቆሮ 5፥19 ላይ የተጠቀሰው እግዚአብሔር የትኛው እግዚአብሔር እንደሆነ አስረዱን
4ኛ....እግዚአብሔር በልጁ (በሰውነቱ ) ከእኛ ጋር ሆነ
5ኛ....እግዚአብሔር በልጁ በሰውነትቱ በአለም ሁሉ ላይ በጽድቅ ይፈርድ ዘንድ ቀን ቀጥሮ በመጠባበቅ ላይ ነው ሐዋ 17÷31
በአጠቃ ላይ እግዚአብሔር በስጋ ሲገለጥ በተገለጠበት ሰውነቱ በኩል ከላይ የተጠቀሱትን ለማድረግ ወድዷል
=>> በዮሐ 1፥18 ገለጻ መሰረት ፦ እግዚአብሔር የታየው የተተረከው በልጁ {በሰውነቱ) ነው
=>> በዕብ 1፥1 ገለጻ መሰረት ፦ እግዚአብሔር ቀጥታ የተናገረን በልጁ (በሰውነቱ ) ነው
=>> በ2ኛ ቆሮ 5፥19 ገለጻ መሰረት ፦ እግዚአብሔር አለምን ከራሱ ጋር ያስታረቀው በልጁ (በሰውነቱ) ነው
=>> በቆላ 1፥19 ገለጻ መሰረት ፦እግዚአብሔር ሙልአቱን ሁሉ በልጁ (በሰውነቱ) አድርጓል
=>> በማቲ 1፥23 ገለጻ መሰረት ፦ እግዚአብሔር ከእኛ ጋር የሆነ ተጸንሶ በተወለደው በልጁ (በሰውነቱ ) ነው
=>> በቆላ 1፥9 ገለጻ መሰረት ፦ የመለኮት ሙልአት በልጁ (በሰውነቱ ) ተገልጦ ይኖራል
=>> በሐዋ 17፥31 ገለጻ መሰረት ፦ እግዚአብሔር የሚፈርደው በልጁ (በሰውነቱ) ነው
የስላሴ አማኞች ኢየሱስ ከአብ በተለየ ማንነቱ ራሱን ችሎ አምላክ በመሆኑ ምክንያት ፤ ከላይ የተዘረዘሩት ነጥቦች እንዴ ይስማሙታል?
እንግዲህ አብ ሚባል እግዚአብሔር አላችሁ ፤ ወልድ ሚባልም አግዚአብሄርም አላችሁ
መልካም እግዚአብሔር ከእኛ ጋር ሆነ የሚለው የማቲ 1፥23ን ጥቅስ አንብቡና የቱ እግዚአብሔር ከእኛ ጋር ሆኖ የቱ እግዚአብሔር ከእኛ እንደራቀ አስረዳን.........?
👉ዕብ 1፥1ን አንብቡና የቱ እግዚአብሔር በየቱ እግዚአብሔር እንደተናገረ ንገሩኝ
👉2ኛ ቆሮ 5፥19ን አንብቡና ፦ የቱ እግዚአብሔር ታራቂ ፦ የቱ እግዚአብሔር አስታራቂ እንደሆነ ንገሩኝ
👉ኢሳ 59፥16ንአንብቡና የቱ እግዚአብሔር አማላጅ ሰውን በማጣቱ ምክንያት እንዳዘነ እንደተከፋ አስረዱን
👉ኢሳ 9፥6ን አንብቡና የሚወለደው ህጻን ጽድቅንና ፍርድን በማድረግ አለቅነቱ በዳዊት ዙፋን ላይ ይበዛል የተባለውን ማንነት ንገሩኝ
ማነው ህጻኑ?
ዮሐ 1፥14 በመሰከረልን የእውነት ቃል መሰረት ቃል ስጋ ሆኖ በመጸነስ፦ በሮሜ 1፥3 መሰረት በኃይል የእግዚአብሄር ልጅ ሆኖ በመወለዱ ምክንያት ፦ ስለ እናንተ ከእግዚአብሄር ዘንድ የተገለጠ #ሰው ነበር ብሎ ሐዋ 2፥22 በዘገበልን መሰረት ህጻን የተባለው ሰውነቱ ነው?
ወይንስ መጽሀፍ ቅዱሳዊ ባልሆነው በእናንተ አስተምህሮት መሰረት the 2nd personal god ነው ህጻኑ??
👉ዮሐ 16ን አንብቡና ከአብ ወጥቼ እንደመጣሁ ሲባል ፤ ስለ ምኑ እየመሰከረ እንደሆነ አስረዱኝ
ከአብ ወጥቼ ሲል ሙሉ እግዚአብሔር ከሙሉ እግዚአብሔር ውስጥ መውጣቱን ያሳያል ወይንስ ሙሉ አምላክ ከሙሉ አምላክ ውስጥ መውጣቱን ያሳያል?
👉ኢሳ 43፥10ን አንብቡና ከእኔ በፊት አምላክ የለም ፤ ከበኃላዬም አይኖርም ያለውን ማንነት ንገሩኝ
አባትየው እግዚአብሔር ነው ይህንን ቃል ተናጋሪ? ወይስ ልጅየው እግዚአብሔር ነው በተለየ አካሉ የተናገረው?
አባትየው ነው ካላችሁ ፤ ከበኃላዬ አምላክ የለም ብሎ ሲናገር እየዋሸ ነው? ወይንስ ምን ምክንያት ቢኖረው ነው?
ልጅየው ነው እንዲህ ያለው ካላችሁ ደግሞ ፤ ልጅየው የአባትየውን አምላክነት ቀምቶት ነው ከበፊቴ አምላክ አልነበረም ፤ በኃላዬም አይኖርም ያለው??
👉ዘዳ 32፥39ን አንብቡና እኔ ብቻዬን ነኝ ተመልከቱ ብሎ የተናገረውን ማንነት ለይልን
ማነው ብቻውን እንዳለ ምስክርነትን የሰጠው? አባትየው እግዚአብሔር? ወይስ ልጅዬው እግዚአብሔር?
👉1ኛ ቆሮ 8፥4 ን አንብቡና ፦ ከአንዱ በቀር አምላክ እንደሌለ እናውቃለን ሲል ፤ ይህ አንዱ አምላክ ማን እንደሆነ ለይታችሁ ንገሩኝ
አባትየው እግዚአብሔር ነው? ወይንስ ልጅየው እግዚአብሔር ነው አንዱ ተብሎ በነጠላ ቁጥር የተገለጸው?
ከታች ያለውን የ Telegram channel join አድርጉ በየቀኑ single መዝሙሮች በኮንፈረንስ የተሰበኩ ስብከቶች እና የፅሁፍ ትምህርት ይለቀቃል
join አድርጉ
👉https://t.me/ApostolicchurchofAreka
👉https://t.me/ApostolicchurchofAreka
26/02/2026
ይህ ቦታ የናፈቀው??
እንኳን አደረሳችሁ🙏
የናፈቃችሁ እስቲ ንገሩኝ
ከታች ያለውን የ Telegram channel join አድርጉ በየቀኑ single መዝሙሮች በኮንፈረንስ የተሰበኩ ስብከቶች እና የፅሁፍ ትምህርት ይለቀቃል
join አድርጉ
👉https://t.me/ApostolicchurchofAreka
👉https://t.me/ApostolicchurchofAreka
YouTube link=https://www.youtube.com/
በ England የነበረ ቆይታ
22/02/2026
እውነተኛ አምላክ" (The True God)
በዮሐንስ 17:3 ላይ ኢየሱስ "እውነተኛ አምላክ የሆንህ አንተን..." ብሎ መጸለዩ፣ አብን ከእርሱ ለመለየት ሳይሆን፣ በምድር ላይ ያለውን የሰውነት (የወልድነት) ሚና ለማሳየት ነው።
ነገር ግን ሐዋርያው ዮሐንስ በመጀመሪያው መልእክቱ ላይ እንዲህ በማለት ደምድሞታል፦
1 ዮሐንስ 5፥20፦ "...እውነተኛም በሆነው በእርሱ አለን፥ እርሱም ልጁ ኢየሱስ ክርስቶስ ነው። እርሱ እውነተኛ አምላክና የዘላለም ሕይወት ነው።"
English: "He [Jesus Christ] is the true God and eternal life."
ማጠቃለያ ሐሳብ
ኢየሱስን ከአብ ለይቶ "አብ አይደለም" የሚል ሰው፣ "እውነተኛ አምላክ" የሚለውን ስም ለኢየሱስ መስጠት ይከብደዋል። ምክንያቱም ከአብ ውጭ ሌላ እውነተኛ አምላክ የለም። ኢየሱስ እውነተኛ አምላክ ከሆነ ደግሞ፣ እርሱ ራሱ ያ የተገለጠው አብ መሆኑን መቀበል የግድ ይሆናል።
ፊልጶስም የተረዳው ይህንን ነው፦ አብን በሰማይ ርቆ የሚኖር ሌላ አምላክ አድርጎ ሲጠብቅ፣ አብ ግን በእርሱ ፊት ቆሞ "አይታችሁትማል" አለው።........ጌታ አምላካችን አንድ ጌታ ነው ማርቆስ 12÷ 29...... አንድ ተስፋ .... አንድ አምላክ የሁሉም አባት አለን ,,,,, ኤፍሶን 4÷4
!
ከታች ያለውን የ Telegram channel join አድርጉ በየቀኑ single መዝሙሮች በኮንፈረንስ የተሰበኩ ስብከቶች እና የፅሁፍ ትምህርት ይለቀቃል
join አድርጉ
👉https://t.me/ApostolicchurchofAreka
👉https://t.me/ApostolicchurchofAreka
YouTube link=https://www.youtube.com/
Click here to claim your Sponsored Listing.
Category
Telephone
Website
Address
Areka
S**o
AREKA