Dicha Media

Dicha Media

Share

ይሄ ድቻ ሚዲያ የዜና እና የወቅታዊ መረጃ ገጽ ነው። አዳዲስ መረጃ ለማግኘት Like Page የሚለውን በመጫን Follow ያድርጉ! መረጃ ሲኖራችሁ፣ የሚዲያ ሽፋን ስትፈልጉ በውስጥ መስመር inbox ያድርጉልን ወይም በቴሌግራም @Dicha1bot በኩል ላኩልን።

05/06/2026

አስደሳች ዜና! ከፀጉ ዴሊቨሪ

የተፈጥሮ ማር፣ ንፁ ቅቤ እንዲሁም የወላይታ ዳጣ(ዳታ) ይፈልጋሉ እስካሉበት እናደርሳለን። ሌሎችንም የቤት ውስጥ ሙሉ አስቤዛ ዘይት፣ አትክልት፣ ሽንኩርት ፍራፍሬ ወዘተ ካስፈለጉ በስልክ ቁጥራችን ደውሎ ሀሎ ይበሉ።

☎️ - 09 91 84 84 40
📍Location - Wolaita S**o

05/06/2026

የዎላይትኛ መዝሙር🤲

04/06/2026

የዎላይትኛ ስብከት በአባ ወልደአማኑኤል👏
De7o Qaalaa Siso 27☦️🤲

Photos from Dicha Media's post 04/06/2026

⚖️ የሰበር ሰሚ ችሎት ፦ "ስራ ባልተሰራበት የጦርነት ወቅት ደመወዝ አይከፈልም!"

​የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት በትግራይ ክልል በተከሰተው ጦርነት ምክንያት ስራ ተቋርጦባቸው በነበሩ ፕሮጀክቶች ላይ ሲያከራክር የነበረውን ጉዳይ መቋጫ ሰጥቷል።
​📌 የጉዳዩ መነሻ
​በትግራይ ክልል በመንገድ ስራ ላይ ተሰማርቶ የነበረው የቻይና ገዙባ እና ሰንሻይን ኮንስትራክሽን ጆይንት ቬንቸር (GDGC-Sunshine JV) ሰራተኞች፤ "ከጥቅምት 2013 ዓ.ም ጀምሮ ለ34 ወራት ከ15 ቀናት ያልተከፈለን ደመወዝ ይከፈለን" በማለት ክስ መስርተው ነበር። የቀድሞ የመቀሌ ወረዳ፣ ከፍተኛ እና የክልሉ ጠቅላይ ፍርድ ቤቶች ሰራተኞቹ ደመወዙ ሊከፈላቸው ይገባል በማለት ወስነው ነበር።
​⚖️ የሰበር ሰሚ ችሎት ውሳኔ
​ኩባንያው "በጦርነት ምክንያት ስራ ባልተሰራበት ሁኔታ ደመወዝ መክፈል የለብኝም" በማለት ያቀረበውን አቤቱታ የመረመረው የፌዴራል ሰበር ሰሚ ችሎት የክልሉን ፍርድ ቤቶች ውሳኔ በሙሉ ድምፅ ሽሮታል።
​ፍርድ ቤቱ ለውሳኔው የጠቀሳቸው ዋና ዋና ነጥቦች፦
​ደመወዝ ለስራ የሚሰጥ ክፍያ ነው፦ በአዋጅ ቁጥር 1156/2011 አንቀጽ 54(1) መሰረት ደመወዝ የሚከፈለው ለተሰራ ስራ ብቻ ነው።
​የአቅም በላይ ምክንያት፦ ጦርነቱ ኩባንያው ስራ እንዳያሰራ፣ ሰራተኞቹም ስራቸውን እንዳያከናውኑ የከለከለ "የአቅም በላይ ምክንያት" (Force Majeure) ነው።
​የአሰሪው ጥፋት አለመኖር፦ ሰራተኛው ስራ ለመስራት ዝግጁ ሆኖ እያለ አሰሪው የስራ መሳሪያ ባለማቅረቡ ስራ ቢፈታ ደመወዝ ሊከፈለው ይችል ነበር። ነገር ግን በዚህ ጉዳይ ስራው የተቋረጠው በሁለቱም ወገኖች ቁጥጥር ውጭ በሆነ የጦርነት ሁኔታ ነው።
​የውል መቋረጥ፦ ስራው ከተቋረጠ ከ90 ቀናት በላይ ከሆነ ውሉ በህግ እንደተቋረጠ የሚቆጠር በመሆኑ፣ ኩባንያው በጦርነት ለቆመ ስራ የዓመታት ደመወዝ የመክፈል ግዴታ የለበትም።
​🔍 ትርጉሙ
​ይህ ውሳኔ በጦርነት ወይም በተመሳሳይ ከአቅም በላይ በሆኑ ምክንያቶች ስራ አቁመው ለነበሩ በርካታ ተቋማት እንደ ትልቅ የህግ መመሪያ (Precedent) ሆኖ የሚያገለግል ነው።

Via Lawyer Teketel's Views

Want your business to be the top-listed Media Company in Sodo?
Click here to claim your Sponsored Listing.

Address


Wolaita S**o
S**o
4620