Soddo Christian Hospital
20/05/2026
እጅግ በጣም የምንወዳቸውን እና የምንናፍቃቸውን ሚሲዮናዊያንን ወደ ሀገራቸው አሜሪካ ሸኝተናቸዋል!
ከዩናይትድ ስቴትስ ኦፍ አሜሪካ ወደ ሀገራችን ኢትዮጵያ መጥተው ላለፉት በርካታ ዓመታት በሶዶ ክርስቲያን አጠቃላይ ሆስፒታል እንዲሁም በሌሎችም የኢትዮጵያ ክፍሎች በሕክምና ሚሲዮናዊነት እጅግ በጣም በከፍተኛ ርህራሄ፣ ፍቅር እና ትህትና ማህበረሰባችንን በሕክምና አገልግሎት ያገለገሉትን ሚሲዮናዊያንን፦ ዶ/ር ማርክ ካርነስ (የማሕጸን እና ጽንስ ሕክምና ሐኪም) እና ባለቤታቸው አሊሰን ካርነስ፣ ጆይ ፒየርሰን (የአይ.ሲ.ዩ ነርስ)፣ ዶ/ር ቲም ላቭ (የአጠቃላይ ቀዶ ሕክምና ሐኪም፣ የፓን አፍሪካን አካዳሚ ኦፍ ክርስቲያን ሰርጅንስ ፕሮግራም ዳይሬክተር) እና ባለቤታቸው ላውራ ላቭ ከነልጆቻቸው በዚህ ያለውን የአገልግሎት ጊዜያቸውን ስለጨረሱ በክብር ሸኝተናቸዋል።
ሚሲዮናዊያኑ ለሀገራችን ኢትዮጵያ ደግሞም ለሶዶ ክርስቲያን አጠቃላይ ሆስፒታል በሚሲዮን አገልግሎት፣ ድሆችን በመርዳት፣ ካላቸው በማካፈል፣ ሕሙማንን በነጻ በማከም ወዘተ … እጅግ በጣም ከፍተኛ አስተዋጽዖ ያበረከቱ ከመሆናቸውም በላይ ሆስፒታሉ አሁን ላይ ለደረሰበት የሕክምና አድማስ እና ቴክኖሎጂ ትልቅ መሠረት የጣሉም ናቸው። በኢትዮጵያ በነበራቸው የአገልግሎት ጊዜ እጅግ በጣም ደስተኞች መሆናቸውን እና ሀገራችንን እንደቤታቸው እንደሚያስቡም ገልጸዋል።
በአገልግሎታቸው በርካቶች ተፈውሰዋል፣ ልጅ መውለድ ያልቻሉ ወልደዋል፣ ያለቀሱ ተጽናንተዋል፣ በርካቶች የኢየሱስ ክርስቶስን ፍቅር ተካፍለዋል። እያዘኑ እና እያለቀሱ ወደ ሆስፒታላችን ለመጡ እልፍ ታካሚዎች በደስታ እና በሳቅ ለመመለሳቸው ምክንያት መሆን ችለዋል።
ዶ/ር ቲም ላቭ በሆስፒታሉ የአጠቃላይ ቀዶ ሕክምና ሐኪም በመሆን እንዲሁም የ ፓን አፍሪካን አካዳሚ ኦፍ ክርስቲያን ሰርጅንስ ፕሮግራም ዳይሬክተር ሆነው ለበርካታ ዓመታት በትጋት ያገለገሉ ሚሲዮናዊ ሲሆኑ በዛሬው ሽኝታቸው የሥራ ኃላፊነታቸውን ለምክትላቸው ዶ/ር ገዛኸኝ ጥላሁን አስረክበዋል። በኢትዮጵያ በነበራቸው ቆይታ እጅግ በጣም ደስተኛ እንደነበሩ የገለጹ ሲሆን ወደፊትም ከሆስፒታሉ ጋር ሊሠሩ እንደሚችሉ ተናግረዋል፤ ለሆስፒታሉ አጠቃላይ ሠራተኞች “እግዚአብሔርን ነው የምታገለግሉት ወይስ ሥራ ብቻ ነው የምትሠሩት” የሚል ጥያቄን በማቅረብ እግዚአብሔርን ልናገለግል እንደሚገባን በምክራቸው አሳስበውናል።
የሆስፒታሉ ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ ኤፍሬም ገ/ሥላሴ ፣ ምክትል ሥራ አስፈጻሚ ዶ/ር አብርሃም አዴ እንዲሁም የሥራ ክፍል ኃላፊዎች ሚሲዮናዊያኑ ስለ ሠሯቸው ሥራዎች ከፍተኛ አድናቆትን እና ምስጋናን አቅርበዋል።
20/04/2026
ማስታወቂያ
ቀን፡ 12-06-2018 ዓ.ም
የሶዶ ክርስቲያን ሆስፒታል ኃላ.የተ.የግ.ማህበር የጥበቃ ሠራተኞችን አወዳድሮ ለመቅጠር ባለው ፍላጎት በቁጥር SCH-16/265/18 በቀን 10/07/2018 ዓ.ም እና በቁጥር SCH-187-10-18 በቀን 2-7-2018 ዓ.ም ባወጣው ማስታወቂያ መሠረት ቀርባችሁ የተመዘገባችሁና ፈተና የተፈተናችሁ፡-
ጠቅላላ ድምር 68 እና ከዚያ በላይ ያመጣችሁ ተወዳዳሪዎች ያለፋችሁ ስለሆነ በቀን 19/08/2018 ዓ.ም ወደ ሆስፒታሉ ግቢ አስተዳደር ቢሮ ቀርባችሁ የቅጥር ፎርማሊቲ እንድታሟሉና ስትመጡ ቀደም ሲል ያቀረባችሁትን የትምህርት ማስረጃ original copy እና softcopy እንዲሁም ለጤና ምርመራ የሚሆን ገንዘብ ይዛችሁ እንድትቀርቡ ማስፈለጉን ጭምር እንገልፃለን፡፡
ሁሌም ለላቀ የሕክምና አገልግሎት እንተጋለን!
ሶዶ ክርስቲያን አጠቃላይ ሆስፒታል
አድራሻችን፦ ወ/ሶዶ ከጉታራ በስተጀርባ እንገኛለን
ለበለጠ መረጃ: 0465511164 ይደውሉ
ጤና ነክ የሆኑ መረጃዎችን በየጊዜው ለማግኘት የቴሌግራም ቻናላችንን ይከታተሉ
https://t.me/soddochristiangeneralhospital
በጤና ይቆዩ
08/04/2026
በዛሬው ዕለት 30/07/2018 ዓ.ም በሶዶ ክርስቲያን አጠቃላይ ሆስፒታል የRHD (Rheumatic Heart Disease) Prevention and Control Program የRHD በበይነ-መረብ የታገዘ የታካሚዎች (ልየታ የተደረገላቸው ዕድሜያቸው ከ5-20 የሚደርሱ በትምህርት ቤት የሚገኙ ልጆች እና ወጣቶች) የምዝገባ እና የሕክምና ሁኔታዎች መከታተያ እንዲሁም የተሟላ የሕክምና የመረጃ አያያዝ ዘዴ ACT (Active Community Case Management Tool) የተሰኘ ሲስተም / Platform የማስመረቅ እና ለRHD ቡድን አባላት የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ተሰጥቷል።
ይህ Platform ወደ ትግበራ መግባቱ የታካሚዎችን መረጃ በዘመናዊ እና ዲጂታል መንገድ ለመሰነድ የሚረዳ ከመሆኑም በተጨማሪ የሐኪሞችን እና ታካሚዎችን ጊዜ ከአላስፈላጊ ብክነት የሚታደግ መሆኑም ጭምር በስልጠናው ላይ ተመላክቷል።
ከስልጠናው ተሳታፊዎች ለተነሱ ጥያቄዎች በአቶ ፈቃዱ ኤልያስ እና በዶ/ር ሚሼል ዬትስ ምላሽ እና ማብራሪያ ተሰጥቷል።
ሁሌም ለላቀ የሕክምና አገልግሎት እንተጋለን!
ሶዶ ክርስቲያን አጠቃላይ ሆስፒታል
አድራሻችን፦ ወ/ሶዶ ከጉታራ በስተጀርባ እንገኛለን
ለበለጠ መረጃ: 0465511164 ይደውሉ
ጤና ነክ የሆኑ መረጃዎችን በየጊዜው ለማግኘት የቴሌግራም ቻናላችንን ይከታተሉ
https://t.me/soddochristiangeneralhospital
በጤና ይቆዩ!
Click here to claim your Sponsored Listing.
Category
Contact the organization
Telephone
Website
Address
Christian Hospital Street
Sodo