Labena's library
11/03/2025
04/03/2025
የኢትዮጵያ የባሕር በር ጥያቄ ለየትኛውም የጎረቤት ሀገር ስጋት ሊሆን አይገባም
**********************
(ኢ ፕ ድ)
የተለያዩ ሀገራት ከርቀት በመምጣት በቀይ ባሕር የጦር ሰፈር ማቋቋም ደረጃ እየደረሱ ባሉበት ሁኔታ ኢትዮጵያ ከተቀረው ዓለም ጋር መገናኘት እንድትችል የባህር በር መጠየቋ ስጋት የሚሆንበት ምክንያት እንደሌለ በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ መምህር ፕሮፌሰር አድማሱ ገበየሁ ተናገሩ።
ኢትዮጵያ ስትጠይቅ በነጻ ስጡኝ አላለችም፤ ጥያቄው የቀረበው በሰጥቶ መቀበል መርህን ነው ብለዋል።
እፕሮፌሰር አድማሱ ገበየሁ ለኢፕድ እንደገለፁት ኢትዮጵያ በአፍሪካ ቀንድ ትልቋ ሀገር መሆኗን ብዙዎቹ የዓለም ሀገራት ይቀበላሉ፡፡ ኢትዮጵያ ባላት ሀገራዊ ሀብትና በሕዝብ ብዛት አሁን ባለው ወቅታዊ መረጃ ትልቅ ሀገር ናት፡፡
ኢትዮጵያ የባሕር በር አግኝታ ይበልጥ ተጠቃሚ ብትሆን ጎረቤት ሀገራትን ጨምሮ ሌሎችም ገበያቸው ይሰፋል፤ ተጠቃሚ ይሆናሉ እንጂ ሊገጥማቸው የሚችል ችግር አይኖርም ያሉት ፕሮፌሰር አድማሱ፤ አንዳንድ ሀገራትና ግለሰቦች የባሕር ኃይል መቋቋሙን እንደ ስጋት ሲመለከቱ እናያለን። ይህ ግን ስህተት ነው ብለዋል።
ሀገሪቷ ወደብ ላይ የሚንቀሳቀስ ሀብትና ንብረት አላት፡፡ በአካባቢው የሚንቀሳቀሱ የባሕር ላይ ወንበዴዎች አሉ፡፡ ሀብት ንብረቷን በመጠበቅ ራሷን ከእነዚህ ኃይሎች ለመከላከል የሰለጠነ ወታደራዊ የባሕር ኃይል ያስፈልጋታል።
ኢትዮጵያ በምንም መልኩ በጉልበቷ ከሌላ ለመንጠቅ የተንቀሳቀሰችበት ታሪክ እንደሌላት አመልክተው፤ የባሕር በር ለማግኘት በቅርብ ጊዜ የሰማነው ከሶማሌ ላንድ ጋር ያለው ጉዳይ ብቻ ሳይሆን ከሌሎችም ዙሪያችን ካሉ የቅርብም ሆነ የሩቅ የባሕር በር ባለቤቶች ጋር በተለያየ ደረጃ ሙከራዎች እየተደረጉ ነው፡፡ ከሁሉም ጎረቤቶቻችን ጋር የባሕር በር በተመለከተ መነጋገርና ሁኔታዎችን የተሻለ የማድረግ ሂደትን መከተሉ ተገቢና ሊቀጥል የሚገባው እንደሆነ ገልጸዋል።
ኢትዮጵያም የተለያዩ ሀገራት ወደ ቀጣናው እየመጡ በቀይ ባሕር ላይ የጦር ሰፈር እየገነቡ ባሉበት ወቅት ከመቶ ኪሎ ሜትር ባነሰ ርቀት ላይ ያለችው ኢትዮጵያ የባሕር በር ጥያቄ ማቅረቧ ላይ ቅሬታ ማሰማት ትርጉም የለውም ብለዋል።
Click here to claim your Sponsored Listing.
Category
Telephone
Website
Address
S**o