Reset code

Reset code

Share

06/04/2023

ምርጥ ሀገር አለን። ዓይናችንን ገልጠን ብንሠራ ለዓለም መስሕብ መሆን የሚችሉ በርካታ ቦታዎች በሀገራችን አሉ። አካባቢያችንን እንቃኝ፤ አካባቢያችንን እንፈትሽ። የኔ ያልነውን የጋራ ሀብት እናድርግ፤ እናልማ፤ አብረን ተግተን ሠርተን እንበልጽግ።

Biyya bayeettii qabna. Ija keenya banannee yoo hojjenne biyya keenya keessa bakkeewwan addunyaaf hawwataa ta'uu danda'an hedduutu jiru. Nannoo keenya haa sonnu, nannoo keenya haa sakattaanu. Isa kankooti jenne qabeenya waloo haa taasifnu; haa misoomsinu; waliin cimnee hojjennee haa badhaadhomnu.

We have a great country. If we open our eyes, there are many places in our country that can be attractive to the world. Let's explore and examine our surroundings. Let us turn what we think is only ours into our collective wealth. Let us develop our resources and collectively work hard and prosper. ዶክተር ልዩ

06/04/2023

Que Jesus Christ de
Nazareth te protège dans tous tes projets

02/04/2023

መገለጥ፤የተሰወረው ግልጥ መሆን። እግዚኣብሔር ራሱን ባይገልጥ ኖሮ ልናውቀው አንችልም ነበር፤ ኢሳ. 55፥8፤ 1ቆሮ 2፥14፤ 2ቆሮ. 4፥4። ግን ኃይሉንና ክብሩን ፈቃዱንም ገልጧል። ይህም ሲባል እግዚአብሔር ለሰው አስፈላጊውንና ተገቢውን እንጂ ሁሉን ገልጧል ማለት ኣይደለም፤ ዘዲ 29፡29። መገለጥ በመሠረቱ ሁለት ዓይነት ነው፥
ሀ) ተፈጠሩ ነገሮችና ሰመጋቢነት ተግባሩ፤ ሮም 1፥19-21፤ ሓ.ሥ. 14፥ 17። ነገር ግን ይህ መገለጡ በቃል ጭምር ካልተደገፈ የእግዚአብሔርን ፈቃድ ሙሉ በሙሉ አይገልጥም፤ የደኅንነትንም መንገድ አያሳይም፡
ለ) በቃሉ፤ ሰመ.ቅ. የመገለጥ ቃል ሰብዙ መንገድ መጥቷል :-
1. ቃልን በመናገር፤ ሰብ.ኪ. ዘመን ይህ ዋና መንገድ ነሰር። ብዙ ጊዜ አሳቡን ለነቢያት ሰጠ። እነርሱም [ ለሕዝብ ተናገሩ፤ ዕብ. 1፥1። 2. በሕልምና በራእይ፤ ዘኍ. 12፥6-8። ሆኖም ሰዎች እንዲያስተውሉ ብዙ ጊዜ ትርጓሜ እስፈላጊ ነበር፤ ዳን. 2፥19:28-30።
3. ዓለምን በመፍጠሩና በመጠበቁ (መዝ. 19፣ ሮም 1፥ 19-21፤ ሐ.ሥ. 14፡ 17)፥ ተአምራትንም በማድረግ (መዝ 18፥11)። ሆኖም ብዙ ጊዜ ተአምራት በእግዚአብሔር እንደተደረጉ ሰዎች በመልእክተኞች ቃል ተረዱ።
4 በልጁ፤ ዮሐ 1፡18፤ 1ጢሞ. 3፥16፤ ዕብ 1፥23።
5. መንፈስ ቅዱስን በመስጠት፣ ዮሓ 15፥26፤ 16፥ 13፤ 1ቆሮ 2፥11:12፤ ዕብ. 2፡4።

እግዚአብሔር የሃይማኖትን ትምህርት ፈጽሞ ለሐዋርያት ገልጧልና ምእመናን አሁን በዚህ ትምህርት ጸንተው መቆም እንጂ ሌላ መግለጫ መፈለግ ወይም መከታተል አይገባቸውም፤ ኤፌ. 3፥5:6፤ ይሁዳ 3፤ ራእ. 22፥ 18:19። የእግዚአብሔር መገለጥ በመቅ ተጽፏል። መቅ.ም ጠቅላላውን የእግዚአብሔርን መገለጥ የያዘ ነው።

ዛሬም ሰዎች ራሳቸው ለግል ሕይወታቸው የእግዚአብሔርን ፈቃድ እንዲያውቁ መንፈስ ቅዱስ ይመራቸዋል፤ ሮም 8፥14፣ 1ቆሮ. 14፥26፤ ገላ 2፥2።

በዓለም መጨረሻ ክርስቶስ ይገለጣል (ሉቃ 17፥30፤ ቲቶ 2፥12:13) ደግሞም የሰው ሥውር አሳብ ሁሉ ይገለጣል፤ ሉቃ 12:2፤ ሮም 8፥18፤ 1ቆሮ. 3፥13።

ምንጭ:
የመጽሐፍ ቅዱስ መዝገበ ቃላት (የኢትዮጵያ መጽሐፍ ቅዱስ ማህበር)

Want your business to be the top-listed Shop in Shashemene?
Click here to claim your Sponsored Listing.

Website

Address


1239
Shashemene
541999