Zeagelo Page

Zeagelo Page

Share

11/11/2025

የመስከረም ወር ተፅዕኖ ፈጣሪ አዶናይ በሰይፉ ሾው ላይ ላለመቅረብ ወሰነ!

የመስከረም ወር የሶሻል ሚዲያ ተፅዕኖ ፈጣሪ አሸናፊ የሆነው አዶናይ፣ በታዋቂው 'ሰይፉ ሾው' ላይ እንዲቀርብ የቀረበለትን ግብዣ እንደማይቀበል አስታወቀ።

አዶናይ ይህን ውሳኔ ያሳለፈበትን ምክንያት ሲገልጽ፣ የዝግጅቱ አዘጋጅ ሰይፉ ፋንታሁን በአሽሙር እንደተናገረው ተሰምቶኛል ብሏል።

ሰይፉ በዝግጅቱ ላይ፣ አዶናይ ሾው ላይ መቅረብ ከፈለገ "ይህ ሾው ለሁሉም ክፍት ስለሆነ" መቅረብ እንደሚችል በመግለጽ የጋበዘው ሲሆን፣ ንግግሩን ሲያጠቃልልም "ዶናይ" የሚል ቃል ተጠቅሟል።

አዶናይ ይህን "ዶናይ" የሚል አጠራር እንደ አሽሙር እና እንደ “ቅኔ” ነው ወስዶታል።

በብዝ የማህበራዊ ሚዲያ ተጠቃሚዎች ዘንድ ሰይፉ የተጠቀመው ቃል 'ዶናይ' ወይም 'ዶናዬ' የሚለው ከአዶናይ ቀደም ሲል ሰዎችን ለማስተማር ሲጠቀምባቸው ከነበሩት ቃላት መጨረሻ ላይ ካለችው 'ዬ' ከምትለው ፊደል ጋር ተመሳሳይነት ስላለው እንደ አሽሙር ተወስዷል።

አዶናይ በመጨረሻ ምላሹን ሲሰጥ፣

ሾው ላይ መቅረብ እንደማይፈልግ በማያሻማ ሁኔታ ገልጿል። ለዚህም ምክንያቶች ሲዘረዝር፦

* በአካል አግኝቼው ነበር፣ በክብር አላወራኝም" ብሏል።

* የምርጫ ቅስቀሳ እያስፈለገኝም" በማለት፣ ሾው ላይ መቅረብ ሽንፈቴን ወይም ድሌን አይለውጠውም የሚል አቋም አንጸባርቋል።

ሰይፉንም እንዲሚያከብረው እና እሱን እያየ እንዳደገም ገልፇል::

በዚህ ጉዳይ ላይ የእርስዎ አስተያየት ምንድን ነው?

* የሰይፉን አጠራር እንደ አሽሙር ትመለከቱታላችሁ?
* አዶናይ የሰጠውን ምላሽ ትደግፋላችሁ?

አስተያየታችሁ አካፍሉ ?

🙏🙏🙏

Via Gursha
fans

Photos from Zeagelo Page's post 04/05/2025

116ኛው የኢትዮጵያ ፌዴራል ፖሊስ ምሥረታ ቀን የማጠቃለይ መርሀ ግብር በመስቀል አደባባይ ዛሬ ተከናውኗል።

መርሀ ግብሩ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)ን ጨምሮ በርካታ ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች በተገኙበት ነው የተካሄደው።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ (ዶ/ር) በስነ ስርዓቱ ላይ ባሰሙት ንግግር " ለተቋም 116 አመታት ማለት ቀላል ትርጉም የሚሰጠው አይደለም " ብለዋል።

" ቀጣይነት ያለው ሪፎርምና ዘመንን የሚዋጅ አቅም መገንባት አስፈላጊ ነው "ሲሉም ተናግረዋል።

" ባለፉት ጥቂት አመታት በኢትዮጵያ የተቋም ግንባታ በሰላምና ደህንነት ጠባቂ ተቋማት ላይ የተሰራው ስራ አመርቂ ቢሆንም አሁን ዓለም ካለበት ሁኔታ አንጻር በቀጣይነት መሰልጠንና መዘጋጀት ይጠበቅባቸዋል " ሲሉ ገልጸዋል።

" የኢትዮጵያን ብሔራዊ ጥቅም፣ ሰላምና አንድነት የማረጋገጥ ስራ ከፖሊስ ሰራዊቱ ይጠበቃል " ብለው " አንድ መሆን ከቻልን የኢትዮጵያን የግዛት አንድነት እና ብልጽግና ማረጋገጥ እንችላለን " ሲሉ ተናግረዋል።

" የጠላቶቻችን ፍላጎት እኛን መለየትና መበተን በመሆኑ፥ የእኛ ዓለማ ብሔራዊ ፍላጎቶቻችንን አንጥረን ማወቅ፣ ሰላማችንን መጠበቅ፣ ተባብረን መትጋትና ከወንድም የጎረቤት ህዝቦች ጋር በጋራ መስራት ነው " ሲሉ ገልጸዋል።

" ከዚያ ያለፈ ነገር ካለ እንደ አባቶቻችን በአርበኝነት ስሜት የኢትዮጵያን አንድነትና ብሔራዊ ጥቅም ማስከበር የሁል ጊዜ ስራችን ነው " ሲሉ ለሰራዊቱ መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡

" የኢትዮጵያን ሰላምና አንድነት የማይፈልጉ ሀይሎች በተለመደው መንገድ በክንዳችን ይፈርሳሉ " ሲሉ አስጠንቅቀዋል።

08/04/2025

የትግራይ ህዝብ ላሳየኝ ክብር እና ድጋፍ ላቅ ያለ ምስጋና አለኝ - አቶ ጌታቸው ረዳ

የትግራይ ህዝብ ላሳየኝ ክብር እና ድጋፍ ላቅ ያለ ምስጋና አለኝ ሲሉ አቶ ጌታቸው ረዳ ገለጹ።

አቶ ጌታቸው ረዳ የሁለት ዓመት የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ርዕሰ መስተዳድር ኃላፊነታቸውን በይፋ ማስረከባቸውን በማኅበራዊ ትስስር ገፃቸው ባሰፈሩት መረጃ አመልክተዋል።

በኃላፊነት ቆይታዬ የትግራይ ህዝብ ላሳየኝ ክብር እና ድጋፍ ላቅ ያለ ምስጋና አለኝ ያሉት አቶ ጌታቸው÷ ህዝባችን ወደ ተሻለ ሁኔታ እንዲመለስና ሁለንተናዊ ፍላጎቱ እንዲሟላለት የተቻለኝን ሁሉ አደርጋለሁ ብለዋል።

የሰላም እና የለውጥ ፍላጎቶች እንዳይሰናከሉ ትግላችንን እናጠናክር ሲሉም ገልጸዋል።

Photos from Zeagelo Page's post 07/04/2025

አቶ ጌታቸው ረዳ ምስጋና ቀርቦላቸው ከጊዜያዊ አስተዳደር ፕሬዜዳንትነት ተሰናበቱ።

ጠ/ሚ ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) አቶ ጌታቸው ረዳ ላለፉት ሁለት ዓመታት የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ርዕሰ መስተዳድር በመሆን ላበረከቱት አስተዋጽኦ ምስጋና አቅርበዋል፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ፥ በፕሪቶሪያው የሰላም ስምምነት መሰረት አቶ ጌታቸው ረዳ ላለፉት ሁለት ዓመታት የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ርዕሰ መስተዳድር በመሆን ላበረከቱት አስተዋጽኦ አመስግነዋል፡፡

በተለይ አቶ ጌታቸው የተገኘው ሰላም እንዲጸና ለነበራቸው ከፍተኛ ጥንቃቄና አመራር የፌደራል መንግስት እውቅና እንደሚሰጥ አስገንዝበዋል፡፡

በቀጣይ ሥራዎች በጋራ ተቀራርበው እንደሚሰሩ ያረጋገጡት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ (ዶ/ር) ለነበራቸው ቆይታም ምስጋና አቅርበዋል፡፡

አቶ ጌታቸው ረዳ የትግራይ ጊዜዊ አስተዳደር በመሆን ለሁለት ዓመት መርተዋል። አሁን ላይ አዲስ የክልሉ ፕሬዝዳንት እንዲሰየም ሂደት ላይ ነው።

25/03/2025

#ልዩመረጃ ‼️ ማምሻውን የ EBS ዋና ዳሬክተርና የዝግጅቱ አዘጋጅ እንዲሁም አንድ ኤዲተር በፌደራል ፖሊስ ተይዘው ቃላቸውን እየሰጡ እንደሆነ አረጋግጫለሁ::

22/03/2025

" እኔን እስካሁኗ ደቂቃ ድረስ ፕሬዜደንት አድርጎ የሾመኝ የለም " - ሌ/ጄነራል ታደሰ ወረደ

በአሁኑ ባለው የትግራይ ቀውስ " አሸናፊም ሆኖ ተሸናፊ የለም " አሉ የትግራይ ጊዚያዊ አስተዳደር ምክትል ፕሬዜዳንት ሌተናል ጀነራል ታደሰ ወረደ።

እስካሁኗ ሰዓት ድረስ የትግራይ ክልል ጊዚያዊ አስተዳደር ፕሬዜዳንት አቶ ጌታቸው ረዳ ናቸው ያሉ ሲሆን " የሚጠበቅ ማስተካከያ ቢኖርም እኔን እስካሁኗ ደቂቃ ድረስ ፕሬዜደንት አድርጎ የሾመኝ የለም " ብለዋል።

" ሆኖም ያሉንን ችግሮች በአንድነት መንፈስ ለመፍታት የሚያስችል እድል ከተፈጠረ ሃላፊነቱ ያለመቀበል ፍላጎት የለኝም " ሲሉ ገልጸዋል።

" ፕሬዜዳንት ጌታቸው ከመቐለ ወጥተዋል፤ ፕሬዜዳንት ጌታቸው ወጥቶ የሚቀርባት ትግራይ መኖር የለባትም ፤ ትናንት እንደዛ ከነበረ ዛሬና ነገ መኖር መደረግ የለበትም " ብለዋል።

የትግራይ ጊዚያዊ አስተዳደር ምክትል ፕሬዜዳንት ሌተናል ጀነራል ታደሰ ወረደ ' በራኸ ሾው ' ለተባለ የዩቱብ ሚድያ በሰጡት ቃለመጠይቅ ምን አሉ ?

➡️ ለውጥ መቀበል የግድ ነው ተወደደም ተጠላም በቆየው የፓለቲካ አካሄድ መሄድ አይቻልም።

➡️ ታሪክ ዳቦ አይሆንም ስለሆነም በትናንት አንኑር ወደ ነገ እንመልከት እናተኩር ፤ ትግራይ ሳትድን የሚድን አከባቢ የለም።

➡️ በወጣቱ ያልተመራ ትግል እውነተኛ ለውጥ ነው ማለት አይቻልም ስለሆነም ከአፍ በዘለለ ወጣቱ የመሪነት ሚናው እንዲረከብ ከልብ መሰራት አለበት።

➡️ የትግራይ ችግር የተከማቸ ነው፤ ከህወሓት መከፋፈል በፊትም የነበረ ነው፤ ሁለቱ የህወሓት ቡድኖች ላለመስማማት የተስማሙ መሆናቸው አሁን ያለውን የትግራይ ፓለቲካ እጅግ የተወሳሰበ እንዲሆን አድርጎታል።

➡️ የሁለቱ ቡድኖች የከረረ መከፋፈል ወደ ለየለት አደጋ እንዳያድግ የሰራዊቱ አመራር ሚናውን ለመወጣት ሞክሯል ይህ ሆኖም ሁለቱ ቡድኖች ፊት ለፊት ተቀምጠው እንዲወያዩ ያደረገው ጥረት አልተሳካም።

➡️ የእኛ ጥረት ብቻ አይደለም ያልተሳካው የትግራይ የሃይማኖት አባቶች ፣ የአገር ሽማግሌዎች ፣ ሙሁራንና ሌሎች አካላት ሁለቱ ቡድኖች ለማቀራረብ ያደረጉት ጥረት ውጤት አላማጣም።

➡️ በመጨረሻ የሰራዊቱ አመራር ለሁለት በመከፈል አንዱ ክፍል ጉባኤ ያካሄደውን የህወሓት ቡድን ሲደግፍ የተቀረው ደግሞ የህዝብና የአገር ተልእኮ ከማስከበረ በዘለለ የቡድኖች የፓለቲካ አቋም አልደግፍም ያለ አለ።

➡️ ቡድኖቹ በየአከባቢው ከቀበሌ ጀምሮ እስከ ዞን የየራሳቸው አስተዳዳሪ መሾም ሲጀምሩም የሰራዊት አመራሮች ድርጊቱ ልክ እንዳልሆነ ለማሳመን ሞክረዋል ሆኖም አድማጭ አልተገኘም። በፊት በትግራይ የተለመደ የሹመት ስነ-ስርዓት አለ። ፓርቲ ነው ከቀበሌ እስከ ዞን አስተዳዳሪ የሞሾመው። አሁን ግን ፓርቲው ይመድባል ፤ ጊዚያዊ አስተዳደሩ ድግሞ ይሾማል። ይህ አካሄድ የመንግስት የስራ ሃላፊነት ከአንድ ማእከል የሚቀዳበት አሰራር እያጠፋው ሄደ። ስለሆነም ከአሁን በፊት ያልተለመደ ምደባው ህዝቡ መንግስታዊ አገልግሎት ከማሳጣት በዘለለ የፀጥታ ችግር እስከ መሆን ደርሷል።

➡️ የፀጥታ ሃይሉ በዚህ መሃል በሁለት ገመድ እየተጎተተ ስራውን ለመሰራት ተቸግሯል።

➡️ የአሁኑ መከፋፈል ከ93 ዓ.ም መከፋፈል የከፋ ነው። 93 ዓ.ም ያጋጠመው መከፋፈል የመንግስት ስልጣን የተቆጣጠረው ቡድን ነው ያሸነፈው ከመንግስት መዋቅር ውጪ ያለውም ደግሞ ተሸናፊ ሆነ። የአሁኑ ግን እንደዛ አይደለም ምክንያቱም ሁለቱ ልዩነት የፈጠሩ ቡድኖች በመንግስት የሰራ ሃላፊነቱ የነበሩ ስለሆኑ።

➡️ ችግሩ ሲጀመር የፀጥታው አካል የሁለቱ ቡድኖች የመከፋፈል አካል አልነበረም። ፓርቲው እንጂ የፀጥታ አካሉ በሚያስከፋ መልኩ ሳይከፋፈል ለረጅም ጊዚያት ተጉዘዋል። ኋላ ላይ ግን የፓርቲው መከፋፈል ምሁሩን ፣ ፓሊሱን ፣ የፓለቲካ ኤሊቱን ሌላውን እንደተከፋፈለ ሁሉ የፀጥታ ሃይሉም እንዲከፋፈል ሰለባ አድርጓል። ይህ ሆኖ ቀውሱ ከአቅም በላይ ሆኖ ትርምስ እንዳይፈጠር የፀጥታ ሃይሉ ከባድ የሆነ ስራ ሰርቷል።

➡️ ሰራዊቱ የፓለቲካ ብልሽቱ ተጠቂ (Victim ) እንጂ ግጭትና ቀውስ ጠማቂ አይደለም።

➡️ በአሁኑ ወቅት አሸናፊ የሚባል የፓለቲካ ሃይልም ይሁን ቡድን የለም ፤ ሁለቱ የህወሓት ቡድኖች የወጣቱ ስሜት ከማጋጋል ባለፈ ያመጡት ለውጥ የለም ስለሆነም ነው አሸናፊና ተሸናፊ የለም የሚባለው።

➡️ አሁን በትግራይ ያለውን የከፋ ሁኔታ በጠበንጃ እፍታለሁ ብሎ መንቀሳቀስ ውጤቱ የባሰ እንጂ የተሻለ ተብሎ የሚወሰድ አይደለም። እርስ በራሳችን ለመዋጋት ከሆነ የሚፈለገው ? በዚህ አካሄድ የሚገኝ አወንታዊ ውጤት የለም። ስለሆነም በእርጋታ ማሰብ ያለብን ጊዜ ቢኖር አሁን ነው።

➡️ ዳግም ጦርነት ይፈጠራል ወይ ? የውስጣችን ችግር በሰላማዊ መንገድ ይፈታል የሚል እምነት አለኝ። ከዚህ በመነሳት በውስጣችን የእርስ በርስ ጦርነት ይካሄዳል የሚል አልቀበልም አይኖርምም።

➡️ በኢትዮጵያ እና በኤርትራ መካከል የሚታየውን መሳሳብ ወደ ጦርነት እንዳያመራ እንደ ትግራይ የበኩላችንን ጥረት ማድረግ ይጠበቅብናል። የውስጣችን ችግር ከፈታን ደግሞ ከውጭ የሚመጣ ጦር ይኖራል ብዬ አልገምትም አላምንም።

➡️ የፕሪቶሪያ የሰላም ስምምነት በተሟላ መልኩ እንዲተገበር በተዋዋዮች መካከል ቅንነት እና ትብብር መኖር አለበት።

➡️ እስካሁኗ ሰዓት ድረስ የትግራይ ጊዚያዊ አስተዳደር ፕሬዜዳንት ጌታቸው ረዳ ናቸው ፤ የሚጠበቅ ማስተካከያ ቢኖርም እኔ እካሁኗ ደቂቃ ድረስ ፕሬዜደንት አድርጎ የሾመኝ የለም። ሆኖም ያሉንን ችግሮች በአንድነት መንፈስ ለመፍታት የሚያስችል እድል ከተፈጠረ ሃላፊነቱ ያለመቀበል ፍላጎት የለኝም።

Photos from Zeagelo Page's post 16/03/2025

#ሻሸመኔ 😢
ትላንትና አሰቃቂ የመኪና አደጋ ደርሶባቸው ህይወታቸው ካለፉት መካከል የ11ምዕመናን ሥርዓተ ቀብር ዛሬ ተፈፅሟል።

በትናትናው ዕለት ከአርባምንጭ ዝጊቲ አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ በዓለ ንግስ ሲመለሱ ወላይታ ዞን ዳሞት ወይዴ ወረዳ በዴሳ ከተማ አቅራቢያ በደረሰዉ የመኪና አደጋ 14 ምእማናን ወዲያዉኑ ህይወታቸው አልፏል።

ከባድ ጉዳት ደርሶባቸዉ በኦቶና ሆስፒታል በሕክምና ላይ ከነበሩት 21 ሰዎች ደግሞ 4ቱ ህይወታቸው ማለፉን ከዞኑ ፖሊስ የደረሰን መረጃ ያሳያል።

በአጠቃላይ የሟቾች ቁጥር ይህ መረጃ እስከተዘጋጀበት ጊዜ ድረስ 18 ደርሷል።

ዛሬ የ11ዱ ስርዓተ ቀብር በሻሸመኔ ከተማ ተፈጽሟል።

➡️ በደብረ አሰቦ አቡነ ተክለሃይማኖት ቤተክርስቲያን 6 ሰዎች
➡️ በልደታ ቤተክርስቲያን 3 ሰዎች
➡️ በቅዱስ ዮሐንስ ቤተክርስቲያን በወቅቱ መኪናዉን ስያሽከረክር የነበረዉ #ሹፌር እና በአጠቃላይ የ11ዱ ምእመናን ሥርዓተ ቀብር መፈፀሙን ከአድባራቱ አረጋግጧል።

የቀሪዎቹ ሥርዓተ ቀብርም በልዩ ልዩ ምክንያቶች በነገዉ ዕለት እንደሚደረግ ከቤተሰቦቻቸው ማጣራት ተችሏል።

በቀብር ሥነሥርዓቱ ላይ የምዕራብ አርሲ ዞን የመንግስት የስራ ሃላፊዎችና የሃይማኖት መሪዎች እንዲሁም በርካታ ቁጥር ያላቸዉ የከተማዉ ነዋሪዎች ምዕመናን ፣ ከተለያዩ አከባቢዎች ለማፅናናት የተገኙ ሰዎች ተገኝተው ነበር።

Want your public figure to be the top-listed Public Figure in Jimma?
Click here to claim your Sponsored Listing.

Category

Telephone

Address


Jimma
Jimma
1983