HHCS
12/04/2022
Wachemo University?
ወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ ከ464,000,000 ብር (አራት መቶ ስልሳ አራት ሚሊዮን ብር) በላይ ወጪ በማድረግ ያስገነባው የመምህራን መኖሪያ አፓርታማ በዛሬው ዕለት በመመረቅ ላይ ይገኛል
…………………………………………………………………………………………………..
ዩኒቨርሲቲው በከተማው ውስጥ ያለውን የመኖሪያ ቤት እጥረት በውል በመገንዘብ ለመምህራን የመኖሪያ ቤት ግንባታ በቂ በጀት በመመደብና ሰፊ ትኩረት በመስጠት ይህንን ግንባታ ማስጀመሩ ይታወቃል:: በመሆኑም የወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ መምህራንን የመኖሪያ ቤት ችግር በከፊልም ቢሆን ለማቃለልና በተለይም መምህራን በዩኒቨርስቲው አቅራቢያ ሆነው በተረጋጋ ሁኔታ መደበኛ ስራቸውን ለማከናወን እንዲያግዛቸው ታስቦ በዩኒቨርሲቲው አቅራቢያ በጉብሬ ክፍለ ከተማ የተገነባው ይህ ዘመናዊ ባለአምስት ፎቅ የመምህራን መኖሪያ አፓርታማ ግንባታው ተጠናቅቆ እነሆ ዛሬ በመመረቅ ላይ ይገኛል::
ግንባታው ያረፈበት ስፍራ 1719 ካሬ ሆኖ አፓርታማው አራት ብሎኮች ያሉት ሲሆን ባለ ሁለት መኝታ ያላቸው 72 ቤቶች፤ ባለ አንድ መኝታ ቤት ያላቸው 120 ቤቶች እና 60 እስቱዲዮዎች ሲሆኑ በድምሩ 252 አባወራዎችን የሚያስተናግድ የመኖሪያ ክፍሎች ያሉት ነው::
የግንባታው ደረጃና ውስጣዊ ይዘቱን ስንመለከት እጅግ ዘመናዊ የሆነ ሲሆን ደረጃውን የጠበቀ የኪችን ካቢኔት የተገጠመለት፤ ነዋሪዎችን የዋይፋይ አገልግሎት ተጠቃሚ እንዲሆኑ የሚያደርግ ቴክኖሎጂን የግንባታው አካል ያደረገ፤የራሱ የሆነ ትራንስፎርመር ተገጥሞለት የተሟላ የመብራት አገልግሎት እንዲኖር ለማድረግ የሚያስችል ሆኖ የተገነባ ፤የውሃ እጥረት እንዳይከሰት በማሰብ የራሱ የሆነ ጥልቅ የመጠጥ ጉድጓድ ውሃ ተቆፍሮለት የተሟላ አገልግሎት መስጠት የሚያስችል ሆኖ የተገነባ ሲሆን ለህንጻው ነዋሪዎች አገልግሎት የሚሰጡ 24 ሱቆች ( በእያንዳንዱ ብሎክ 6 ሱቆች) ፤ 4 ካፍቴሪያዎች ( በእያንዳንዱ ብሎክ 1ካፍቴሪያ ) ፤ 4 ሱፐር ማርኬት (በየብሎኩ 1 ሱፐርማርኬት)፤ አንድ ፋርማሲ ያለው ሆኖ ለዘመናዊ የአኗኗር ዘዴ አመቺ እና ለእይታም እጅግ ማራኪ ሆኖ የተገነባ ነው::
Click here to claim your Sponsored Listing.
Category
Website
Address
Hossana