Bonga University
08/06/2026
ቦንጋ ዩኒቨርሲቲ ለማህበረሰብ ሬድዮ ሰራተኞች ስልጠና ሰጠ።
።።።።።።።ሰኔ 1/2018 ዓ.ም።።።።።።።
ቦንጋ ዩኒቨርሲቲ ለዩኒቨርሲቲው ማህበረስብ ሬድዮ ጣቢያ FM-92.1ላይ በፈቃደኝነት እያገለገሉ ላሉ እና ፊላጎት ላላቸው መምህራን ፣ የአስተዳደር ስራተኞችና ባለሙያዎች የአቅም ግንባታ ስልጠና ሰጥቷል።
በመድረኩ ተገኝተው የመክፈቻ ነግግር ያደረጉት የቦንጋ ዩኒቨርሲቲ መማ/ማስ/ምር/ማህ/አገ/ቴክ/ስር/ም/ኘሬዝዳንት ከለለው አዲሱ (ዶ/ር) ናቸው።
ምክትል ፕሬዝዳንቱ በመልዕክታቸው በግልጽ እንዳሰፈሩት ቦንጋ ዩኒቨርሲቲ የማህበረሰብ ተደራሽነቱን ይበልጥ ለማረጋገጥ የራሱን የሬድዮ ጣቢያ መክፈቱን ገልጸዋል።
በመሆኑም የሬድዮ ጣቢያ ማቋቋም ብቻ ሳይሆን የሰው ሀይል ልማት ላይ መስራት እንዲሁም ማፊራት አስፈላጊ እንደሆነ ገልፀዋል።
የዛሬውም ስልጠና የዚሁ አካል በመሆኑ ሙያው በሚፈልገው ልክ ሰራተኞችን ለማብቃት የታለመ እንደሆነ አስገንዝበዋል።
በተጨማሪም ሚዲያ የተቋምን ገጽታ ለመገንባት ወሳኝ በመሆኑ በሙያው የታነፀ ባለሙያ ሲኖር ደግሞ ጣቢያው የተቋሙን ተልዕኮ ለማሳካት ተጨማሪ አቅም እንደሚሆን አብራርተዋል።
ሰልጣኞችም ስልጠናውን በሀላፊነት ስሜት በመከታተል የሬድዮ ጣቢያውን ወደተሻለ ከፍታ በማሸጋገር ለተቋማዊ ለውጥ የበኩላችሁን እንድትወጡ በማለት በይፋ ስልጠናውን አስጀምረዋል።
ስልጠናውን ከደቡብ ሬድዮና ቴሌቭዥን ድርጅት ቦንጋ ቅርንጫፍ የመጡ ባለሙያዎች በተመረጡ ርዕሰ ጉዳዮች ላይ ትኩረት በማድረግ ሰጥተዋል።
በተጨማሪም ከመሠረታዊ ጽንሰ-ሀሳብ ባሻገር በተግባር የተደገፈ ስልጠናም የመርሀ-ግብሩ አካል ነበር።
የዩኒቨርሲቲው ማህበራዊ ሳይንስና ስነ-ሰብ ኮሌጅ በዋናነት ስልጠናውን አስተባብሯል።
በጋራ እንችላለን!
05/06/2026
ቦንጋ ዩኒቨርሲቲ ከካፋ ዞን የተለያዩ ወረዳ እና ከተማ አስ/ር ለተወጣጡ የተፈጥሮ ሀብት አያያዝ ባለሙያዎች ስልጠና ሰጠ።
ግንቦት 28/2018 ዓ.ም
ስልጠናው በዋናነት በGeo spatial Software skill ላይ ትኩረቱን ያደረገ ሲሆን በዩኒቨርሲቲው የማህበረሰብ አገልግሎት እና ቴክኖሎጂ ሽግግር ዳይሬክቶሬት አሰተባባሪነት ነበር የተሰጠው።
በመድረኩ ተገኝተው የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት ከለለው አዲሱ (ዶ/ር) የቦንጋ ዩኒቨርሲቲ መማ/ማስ/ምር/ቴክ/ሽግ/ማህ/ጉድ /ም/ፕሬዝዳንት ሰልጣኞችን የእንኳን ደህና መጣችሁ መልዕክት ያስተላለፉ ሲሆን. . .
አክለውም ም/ፕሬዝዳንቱ እንደገለፁት ያለንን የተፈጥሮ ሀብት ለማስተዳደር እና መጠቀም የሚያስችል ስልጠና እንደሆነ ጠቅሰዋል።
በተጨማሪም በተፈጥሮ ሀብት ለታደለው ለእንደኛ አይነት አካባቢ የGeo spatial siftware Skill ስልጠና ፋይዳው የጎላ እንደሆነ አሳስበው ሰልጣኞች በትኩረት እንዲከታተሉ አስገንዝበዋል።
ስልጠናውን የቦንጋ ዩኒቨርሲቲ የጂኦግራፊ ት/ት ክፍል መምህርና የብዝሀ ህይወት ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ጊንጆ ጊትማ (ዶ/ር) ከሌሎች የት/ት ክፍሉ GIS and Remote Sensing እንዲሁም የደን ሀብት ጥበቃ /Forestry/ ምሁራን ጋር በመሆን ሰጥተዋል።
በስልጠናው ላይ የተሳተፉ የተለያዩ የግብርናና የተፈጥሮ ሀብት ጥበቃ ጽ/ቤት ባለሙያዎች በበኩላቸው በስልጠናው መሠረታዊ የሆኑ የክህሎት ክፍተቶቻችንን መሙላት ችለናል ብለዋል።
ቦንጋ ዩኒቨርሲቲም እንደዚህ አይነት ስልጠና ማዘጋጀቱ ተቋሙን ለየት ያደርገዋል በማለት ለዩኒቨርሲቲው ያላቸውን አድናቆት ገልጸዋል።
በጋራ እንችላለን!
04/06/2026
ቦንጋ ዩኒቨርሲቲ ሀገር ዓቀፍ የአቅም ማሻሻያ /Remedial/ተማሪዎች ፈተና መስጠት ተጀመረ።
*ግንቦት 27/2018ዓ.ም*
ቦንጋ ዩኒቨርሲቲ በዛሬው ዕለት ሀገር ዓቀፉን የአቅም ማሻሻያ /Remedial /ተማሪዎች ፈተና መስጠት ጀምሯል።
ፈተናው በበይነ - መረብ /Online / እንደመሰጠቱ ተማሪዎች ተገቢው የፀጥታ ስርዓቶችን እንዲፈፅሙ በማድረግ ወደመፈተኛ ክፍል ገብተዋል።
ፈተናው ዛሬን ጨምሮ ለተከታታይ ስድስት ቀናት ይሰጣል።
በዚህ ጊዜም ተማሪዎች ተገቢውን የፈተና ስነ-ሥርዓት በመከተል ፈተናውን ተረጋግተው በመስራት ተገቢውን እንዲፈፅሙ ቦንጋ ዩኒቨርሲቲ ለተማሪዎች ያሳስባል።
በጋራ እንችላለን!
03/06/2026
የአቅም ማሻሻያ /Remedial/ ፈተናን አስመልክቶ ለተለያዩ አካላት ገለፃ ተደረገ።
*ግንቦት 26/2018 ዓ.ም*
የ2018 ዓ.ም ሀገር ዓቀፍ የአቅም ማሻሻያ /Remedial/ ፈተና አስመልክቶ ለቦንጋ ዩኒቨርሲቲ የተለያዩ አስፈፃሚ አካላት ገለፃ ተደረገ።
በዩኒቨርሲቲው የመማ/ ማስ/ ምር/ ማ/ አገ/ እና ቴክ/ስር/ም/ፕሬዝዳንት ከለለው አዲሱ(ዶ/ር) መሪነት ነበር መድረኩ የተካሄደው።
በተጨማሪም ከኢ.ፌ.ዲ.ሪ ት/ት ሚ/ር ፈተናውን ለማስተባበር የመጡት አቶ ተክል ዘለቀ ባደረጉት ገለፃ ለሁሉም ፈፃሚ አካላት ተግባር እና ሀላፊነት ዙሪያ ገለፃ ሰጥተዋል።
ፈተናው እንደተለመደው በበይነ መረብ /Online /እንደመሆኑ ተገቢውን በማድረግ የተሳካ የፈተና ሂደት ማከናወን የሁሉም ሀላፊነት ሊሆን እንደሚገባ ጠቅሰዋል።
በመጨረሻም ከለለው አዲሱ (ዶ/ር)በሠጡት ማጠቃለያ ይሄንን ትልቅ ሀገራዊ ሀላፊነት በተሳካ ሁኔታ ለማከናወን ሁላችንም የበኩላችንን መተግበር ይገባናል በማለት የአደራ መልዕክት አስተላልፈዋል።
ተማሪዎችም ፈተናውን በአገባቡ ከመፈተን አንፃር የተለመዱ የፈተና ሥነ-ሰርዓቶችን በመጠበቅ ግዴታችሁን እንድትወጡ በማለት ዩኒቨርሲቲው መልእክት ያስተላልፋል።
ፈተናው ከግንቦት 27 - ሰኔ 03/2018 ዓ.ም እንደሚሰጥ ከወጣው መርሀ-ግብር መረዳት ይቻላል።
በጋራ እንቸላለን!
Click here to claim your Sponsored Listing.
Category
Telephone
Website
Address
Bonga
334