Gech Gm page

Gech Gm page

Share

18/03/2026

ሰበር ዜና፦ የዒድ አል-ፊጥር በዓል አርብ (የጁምዓ ዕለት) መሆኑ ተረጋገጠ!

መካ — ሳዑዲ ዓረቢያ በዛሬው ዕለት ረቡዕ ምሽት በመላው ሳዑዲ ዓረቢያ ሲከናወን የቆየው የሸዋል ጨረቃ ፍለጋ ውጤት ይፋ ሆኗል። በዚሁ መሠረት የሸዋል ወር ጨረቃ ባለመታየቷ ምክንያት፣

ነገ ሐሙስ የረመዳን 30ኛው ቀን ሆኖ የሚጾም ሲሆን፣ ታላቁ የዒድ አል-ፊጥር በዓል ከነገ በስቲያ አርብ (ጁምዓ) መጋቢት 11 ቀን 2018 ዓ.ም (March 20, 2026) እንደሚውል የሳዑዲ ጠቅላይ ፍርድ ቤት በይፋ አሳውቋል።

በዓሉ ከአርብ የጁምዓ ዕለት ጋር በመገጣጠሙ ልዩ ድምቀት ይኖረዋል።

ለመላው የእስልምና እምነት ተከታዮች እንኳን ለ1447ኛው የዒድ አል-ፊጥር በዓል በሰላም አደረሳችሁ!

ይህ በዓል የሰላም፣ የፍቅር እና የደስታ እንዲሆንላችሁ ከልብ እንመኛለን።

ረመዳንን በሰላም እንዳጠናቀቅን ሁሉ፣ በዓሉንም ከቤተሰብ እና ከወዳጅ ዘመድ ጋር በጋራና በመረዳዳት እንድታሳልፉ መልዕክታችንን እናስተላልፋለን።

ዒድ ሙባረክ! መልካም በዓል!

Via GN

ጉርሻ page

🌴🌴🌴

Photos from Addisu Arega Kitessa's post 21/08/2025
Want your practice to be the top-listed Law Practice in Bonga?
Click here to claim your Sponsored Listing.

Category

Address


Bonga