Bonga Town Communications
01/06/2026
እስካሁን ባለው የምርጫው ሂደት ያልተገባ የሰብዓዊ መብት አያያዝ አለመመልከቱን የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን ገለጸ።
ኢትዮጵያ ሰባተኛውን ጠቅላላ ምርጫ እያካሄደች ትገኛለች።
በምርጫው ሂደት የመራጮች የሰብዓዊ መብት አያያዝን በተመለከተ የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን በሀገሪቱ የተለያዩ ከተሞች በሚገኙ የምርጫ ጣቢያዎች የምርጫ መታዘብ ቅኝት እያደረገ ይገኛል።
በኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) ዋና ኮሚሽነር ብርሃኑ አዴሎ የተመራው የኮሚሽኑ ቡድን በአርባምንጭና በጅማ ምርጫ ጣቢያዎች የምርጫ መታዘብ አድርጓል።
በምርጫ መታዘቡ ላይ ኤንቢሲ ኢትዮጵያ ያነጋገራቸው የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) ዋና ኮሚሽነር ብርሃኑ አዴሎ፥ ኮሚሽኑ ባደረገው ቅኝት፥
መራጮች ለመምረጥ አስቻይ የምርጫ ጣቢያዎች የተመቻቹበት ፣ ወንዶች፣ ሴቶችና አካል ጉዳተኞች በተመቻቸ የምርጫ ጣቢያዎች እየመረጡ የሚገኙበት ሁኔታ መኖሩንን ገልጸዋል።
የምርጫው መስፈርቶችን ያሟላ የምርጫ ሂደትን መታዘቡንም ተናግዋል።
ኮምሽኑ በትዝብቱ የምርጫ ሂደቱ ፍጹም ሰላማዊና ምንም መስተጓጎሎች ያልታዩበትና የጠቀሱት ኮሚሽነሩ፥ እስካሁን ባለው የምርጫው ሂደት ያልተገባ የሰብዓዊ መብት አያያዝ አለመመልከቱን አብራርተዋል።
የምርጫው ታዛቢዎች እና መራጩ ዜጋ በሰዓቱ በምርጫ ጣቢያው በመገኘት ምርጫውን ከ ጥዋቱ 12:00 ጀምሮ እያከናወነ እንደሚገኝም ገልጸዋል።
ዋና ኮሚሽነሩ፥ ምርጫው ህብረተሰቡ ለቀጣይ አምስት አመታት የሚመራውን አካል በድምጹ የሚያረጋግጥበት በመሆኑ እንደሀገር ለመምረጥ የተመዘገበው ከ 54 ሚሊየን በላይ ህዝብ ይበጀኛል የሚለውን ፓርቲ በመምረጥ ህገመንግስታዊ መብቱን እንዲጠቀም ሲሉ ጥሪ አቅርበዋል።
ኮሚሽኑ ከትግራይ ክልል በስተቀር ምርጫው በሚካሄድባቸው በሁሉም አካባቢዎች በአጠቃላይ በ175 የምርጫ ክልሎችና ከ 2700 በላይ የምርጫ ጣቢያዎች የመታዘብ ስራውን እያከናወነ እንደሚገኝም ዋና ኮሚሽነሩ ገልጸዋል።
በምርጫ ሂደቱ ያለውን የሰብዓዊ መብት ሁኔታ በመከታተልና በድህረ ምርጫ የሚኖረውንም ሂደት በአግባቡ በመምራት እንደሚሰራም አረጋግጠዋል።
በምርጫ ሂደቱ ቅሬታዎችን ለማስተናገጃ በተዘጋጀው የቅሬታ መከታተያ ስርዓትም የምርጫውን ሂደት እየተከታተለ መሆኑንም አመላክተዋል።
01/06/2026
የቦንጋ ከተማ አስተዳደር ብልጽግና ፓርቲ ቅ/ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ፍሬው አበበ ድምፅ ሰጡ
የቦንጋ ከተማ አስተዳደር ብልፅግና ፓርቲ ቅ/ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ፍሬው አበበ በዛሬው ዕለት በተካሄደው ምርጫ ተገኝተው ድምፃቸውን ሰጥተዋል።
ኃላፊው ድምፃቸውን ከሰጡ በኋላ በሰጡት መግለጫ፤ መላው የከተማዋ ነዋሪዎች በማለዳ ተነስተው በነቂስ በመውጣት መምረጣቸው የከተማዋንና የሀገሪቱን ዲሞክራሲያዊ ሥርዓት ለመገንባት ያለውን ከፍተኛ ፍላጎትና ቁርጠኝነት የሚያሳይ መሆኑን ገልጸዋል።
አቶ ፍሬው አክለውም፤ የምርጫው ሂደት ፍጹም ሰላማዊ፣ ነጻና ስነ-ስርዓትን የተከተለ እንዲሆነ ገልፀዋል።
ቦንጋ ከተማን በጋራ እናልማ ❗️
✍ተጨማሪ መረጃዎቸን ✍
በቴሌግራም 👉 t.me/BongatownGCAO
በፌስቡክ 👉 https://www.facebook.com/BTGCA
በቲውተር 👉 https://twitter.com/BongaTown?t=1Hfq-1TmjDHkrNlWUiPA7g&s=09 ተወዳጅተው ይከታተሉን፡፡
🙏ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን🙏
01/06/2026
የእውነተኛ ቁርጠኝነት ማሳያ!
አሊ መሀመድ ሀሙድ የአፋር ክልል፣ ዞን አምስት፣ ሰሙሮቢ ወረዳ ነዋሪ ናቸው። በሀሞና ሀማር ጌራ ቀበሌ ኮማሚ ምርጫ ጣቢያ ድምፃቸውን በአፋቸው ሰጥተዋል። ግለሰቡ እጆቹን መጠቀም አለመቻሉ ሳይበግረው፣ በከፍተኛ ጥረት ጎንበስ ብሎ በአፉ የድምፅ መስጫ ወረቀቱን በምርጫ ሳጥኑ ውስጥ ሲያስገባ ይታያል። በአጠገቡ የቆመው የምርጫ አስፈጻሚም ይህንን ታላቅ የዜግነት ግዴታ የመወጣት የጽናት ታሪክ በአክብሮትና በትዕግስት ይመለከታል።
ይህ አንድ ምስል ተራ የድምፅ አሰጣጥ ሂደት የሚያሳይ ብቻ ሳይሆን እጅግ ጥልቅ የሆነ የዜግነት ቁርጠኝነትን ያመላክታል። የአካል ጉዳተኝነትም ሆነ ማንኛውም ዓይነት ፈተና የራሱን አሻራ ከማሳረፍና የዜግነት መብቱን ከመጠቀም ሊያግደው አልቻለም።
የግለሰቡ ድምፅ ትልቅ ዋጋ እንዳለው ጠንቅቆ ያውቃል፤ ምርጫው እንዲቆጠርለትና ድምጹ እንዲሰማ ማንኛውንም መሰናክል ለመሻገር ቆርጦ ተነስቷል።
በማኅበረሰባችን ውስጥ ንቁ ተሳታፊ መሆንና የወደፊት ዕድላችንን በራሳችን መወሰን በቀላሉ የሚታይ ሳይሆን፣ በብዙ ቁርጠኝነት የሚገኝ ትልቅ ዕድል መሆኑን የሚያረጋግጥ የዘመናችን ቆራጥ ግለሰብ ነው።
ኢትዮጵያ የራሷን የዴሞክራሲ ባህል እየገነባች ባለችበት በዚህ ታሪካዊ ዕለት ዜጎቿ አካል ሀዘን፣ ጉዳተኝነት፣ ህመምና ሌሎች አስቸጋሪ ሁኔታ ሳይበግራቸው አሻራቸውን እያኖሩ ለዴሞክራሲ ስርዓት መገንባት ያላቸውን መሻት እያስመሰከሩ ይገኛሉ።
01/06/2026
ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የሚወዳደሩት የፓን አፍሪካ ፓርላማ ተቀዳሚ ምክትል ፕሬዝዳንት እና የኢትዮጵያ ኦሎምፒክ ኮሚቴ ፕሬዝዳንት አሸብር ወልደጊዮርጊስ ( ዶ/ር ) በሚወዳደሩበት ምርጫ ክልል በመገኘት ድምፅ ሰጡ::
ዶክተር አሸብር ምርጫው በእስካሁን ሂደቱ ሰላማዊ መሆኑን ተናግረው ህዝቡ በነቂስ ወጥቶ ድምጽ እየሰጠ በመሆኑ በውጤቱ ስኬታማ እንደሚሆን ያላቸውን እምነት ገልጸዋል ::
ዶክተር አሸብር አክለው ማንም ቢያሸንፍ ትልቁ ነገር ኢትዮጵያ ማሸነፏ ነው ብለው ሂደቱ ሕዝቡን የሚጠቅም እና ኢትዮጵያን ከፍ የሚያደርግ መሆን እንዳለበት አንስተዋል::
በርካታ ታላላቅ ድሎችን ባስመዘገብንበት ማግስት መሆኑ የዘንድሮን ምርጫ ልዩ ያደርገዋል ያሉት ዶክተር አሸብር ኢትዮጵያ ገናና ስም ይዛ ጠንክራ በታየችበት ሰዓት የሚካሄድ ምርጫ መሆኑ ይበልጥ ልዩ ያደርገዋል ነው ያሉት።
#ካፋ ቲቪ
Click here to claim your Sponsored Listing.
Category
Telephone
Website
Address
Bonga Town
Bonga