Ephrem Eshetu

Ephrem Eshetu

Share

08/08/2020

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ ከመደመር መጸሀፍ ሽያጭ የተገኘውን ገንዘብ ለቀዳሚዊ እመቤት ጽህፈት ቤት ሰጡ
***********************
ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አቢይ አህመድ ከመደመር መጸሀፍ ሽያጭ የተገኘውን ከ110 ሚሊዮን ብር በላይ ገቢ ለትምህርት ቤቶች ግንባታ እንዲውል ለቀዳሚዊ እመቤት ጽህፈት ቤት አስረከቡ፡፡
ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አቢይ አህመድ ዛሬ በገንዘብ ርክክቡ ሥነ ስርዓቱ ላይ እንደተናገሩት፤ የመደመር መጸሀፍ ሽያጭ ገቢ በኢትዮጵያ የትምህርት ቤት ችግር ባለባቸው አካባቢዎች ትምህርት ቤት ለማስገንባት እንደሚውል በመፅሀፉ የመጀመሪያ ገፅ ላይ ቃል ተገብቷል። ዛሬ የተፈጸመው ርክክብም በዚሁ መሰረት የተከናወነ ነው።
ባለፉት ጊዜያት በአገር ደረጃ ከመደመር መጸህፍ ሽያጭ 110 ሚሊዮን 671 ሺህ ብር መሰብሰብ መቻሉን የጠቀሱት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፤ ይህ ገንዘብም ሙሉ በሙሉ ለቀዳሚዊት እመቤት ጽህፈት ቤት የተሰጠ መሆኑን ገልጸዋል።
ዛሬ በጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት የተካሄደውን የገንዘብ ርክክብ ቀዳማዊት እመቤት ዝናሽ ታያቸው ከጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐብይ አህመድ ተቀብለዋል።
የቀዳማዊት እመቤት ዝናሽ ታያቸው ፅህፈት ቤት ባለፈው ዓመት ከተለያዩ አካላት ገንዘብ በማሰባሰብ 20 ትምህርት ቤቶችን እያስገነባ ሲሆን፤ ሰባቱ መጠናቀቃቸውንና የተቀሩት ደግሞ ግንባታቸው በኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ ምክንያት ቢዘገይም በአሁኑ ወቅት አጠቃላይ አፈጻጸማቸው 90 በመቶ መድረሱ ታውቋል።

Ye Eyesus Menged - Single by Dawit Getachew Abreham 07/08/2020

Ye Eyesus Menged - Single by Dawit Getachew Abreham Album · 2020 · 1 Song

07/08/2020

በሀገራችን ኢትዮጵያ 80% የሚሆኑ የዓይን ብርሃን ሊያሳጡ የሚችሉት ችግሮች በቀላሉ በህክምና መስተካከል የሚችሉ ሲሆኑ ከነዚህ ውስጥ ዋነኞቹ የዓይን ሞራ ግርዶሽ ( ) እና በመነፅር ሊስተካከሉ የሚችሉ የእይታ ችግሮች ( ) ናቸው፡፡ ዓይንዎን ይመርመሩ፤ የእርስዎን እና የቤተሰብዎን ጤና ይጠብቁ፡፡

Want your business to be the top-listed Business in Awassa?
Click here to claim your Sponsored Listing.

Telephone

Website

Address


University Of Hawassa
Awassa