Peps or coca

Peps or coca

Share

24/07/2024

ጎፋ ከአደጋው ማግሥት

ጎፋ፦በመሬት መንሸራተት አደጋው በአሁኑ ወቅት ከ40 በላይ የሚሆኑ ሰዎች ከአፈር በታች ይገኛሉ የሚል ጥርጣሬ መኖሩን የገዜ ጎፋ ወረዳ ባለሥልጣናት ዐሳውቀዋል ።

ከትናንት በስቲያ ሰኞ በደረሰው የመሬት መንሸራተት አደጋ 16 የቤተሰብ አባላቱን ያጣ፤ አምስት የባለቤታቸው ቤተሰብ አባላትን የቀበሩም አሉ።

አደጋውን አስከፊና በቃላት ለመግለጽ እንደሚከብድ የተናገሩት አቶ ዘለቀ « የቤተሰብ አባሎቻቸውን ከአፈር ናዳ ሥር ለማግኘት ያለውን ፈተና ከባድና የሚጨንቅ ነው ብለዋል።

ከተጫነው ናዳ ሥር የወጡ ሟቾች በጭቃ የተለወሱ ናቸው ። ሰዎች የቤተሰብ አባሎቻቸውን የሚለዩት የአስክሬኖችን ፊት በማጠብ ነው።

16 የቤተሰብ አባላቱን ያጣ ፣ ስምንት ልጆቿን ያጣች እናት አለች ፣ ቤተሰቦቹ አልቀውበት ብቻው የቀረ ሕጻንም አለ ፡፡ ሁኔታው ዘግናኝና አስጨናቂ ነው» ብለዋል ። በቀበሌው የደረሰው አደጋ ቁጥሩ ቢለያይም እያንዳንዱን ቤት ለከፋ ኃዘን መዳረጉን ተጎጂዎች ለዶቹ ቬለ ተናግረዋል ።

በመሬት መንሸራተት አደጋው ሕይወታቸው ያለፈ ቀሪ ሰዎችን የመፈለጉ ሂደት አሁንም መቀጠሉን የወረዳ የአደጋ ሥጋት ሥራ አመራር ጽሕፈት ቤት ኃላፊ አቶ ማስረሻ ማንአየ ለዶቼ ቬለ ገልጸዋል።

ሸዋንግዛው ወጋየሁ ዶቸ ቬለ

Want your business to be the top-listed Food & Beverage Service in Awassa?
Click here to claim your Sponsored Listing.

Category

Culinary Team

Attire

Website

Address


Hawassa
Awassa