Mereja Plus
12/07/2025
ኢትዮጵያና ሩሲያ የብርና የሩብል የቀጥታ የምንዛሪ ልዉዉጥ ማድረግ ጀመሩ
የሩሲያ ማዕከላዊ ባንክ የኢትዮጵያን ብር ከሩሲያ ሩብል ጋር በቀጥታ ከሚመነዘሩ ገንዘቦች ዝርዝር ውስጥ ማካተቱን አስታወቀ።ባንኩ እንዳስታወቀዉ ዉሳኔዉ ብርን ወደ ሩብል ሩብልን ደግሞ ወደ ብር መመንዘር የሚያስችል ነዉ።
የሩሲያ ማዕከላዊ ባንክ የኢትዮጵያን ብር ጨምሮ የ12 ሀገራት ገንዘቦች ከሩሲያ ሩብልስ ጋር ያላቸውን ይፋዊ የምንዛሪ ተመን ለማስቀመጥ ውሳኔ ላይ መድረሱን ከተወሰኑ ቀናት በፊት አስታውቆ ነበር።
ማዕከላዊ ባንኩ ዛሬ ሃምሌ 04 ቀን 2017 ዓ.ም. ማለዳውን ይፋ ባደረገው መረጃም ለ100 የኢትዮጵያ ብር 57.58 ሩብል ወይም ለ1 ብር 0.57 ሩብል የምንዛሬ ተመን አስቀምጧል።
ባንኩ ለኢትዮጵያ ብር ምንዛሬ ተመን የኮድ ቁጥር 230 የሰጠ ሲሆን በየዕለቱም የምንዛሬ ተመኑን የሚያሳውቅ እንደሆነ ነው የገለጸው።
Telegram: https://t.me/Mereja_Plus
YouTube: https://www.youtube.com/
Tiktok: mereja.plus
Click here to claim your Sponsored Listing.
Website
Address
Awassa