SNNPR prison adminstration communication
28/09/2023
በማዕከላዊ #ኢትዮጲያ ማረሚያ ፖሊስ ኮሚሽን በስሩ ከሚገኙ ማረሚያ ተቋማት በጥበቃ ስር የሚገኙ የህግ ታራሚዎች የመስቀል በዓልን እያከበሩ ይገኛሉ።
17/01/2016
በኮሚሽኑ ስር ከሚገኙ ማረሚያ ተቋማት መካከል አንዱ የሆነው
# በዱራሜ ማረሚያ ተቋም
የከንባታ ዞን ምክር ቤት የሀደሮ እና የሽንሽቾ ከተማ በጎ አድራጊ ወገኖች እና ከተቋሙ ጋር በመተባበር በድምሩ ሰባት ሰንጋ በሬ ለክርስቲያን እና ለሙስሊም ታራሚዎች ታርዶላቸው በደማቅ ሁኔታ እንዲያከብሩ የተደረገ ሲሆን ይህን በጎ ተግባር ያደረጉትን ወገኖች በታራሚዎች በኮሚሺኑ እና በተቋሙ ስም እጅግ በጣም እናመሰግናለን
መልካም የመስቀል በአል
መረጃውን የደረሰን የዱራሜ ማረሚያ ተቋም!!
የእንኳን አደረሳችሁ መልክት
ቀን 15/01/2016 ዓ.ም
በሀገራችን የመስከረም ወር (2016) ዓ.ም መግባቱን ተከትሎ የተለያዩ በዓላት ይከበራሉ ከነዚህም ውስጥ በማዕከላዊ ክልል የሚገኙ ዞኖች የሚከበረው በሀዲያ የያሆዴና በከንባታ መሰላ እንዲሁም በጉራጌ የመስቀል በዓል በደማቅ ሁኔታ የሚከበር ሲሆን በደቡብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ጋሪዎሮ፣ጊፋታ፣ዮ-መስቀላ፣ሄቦና ጋዜ መስቀላ የመሳሰሉ በዓለት ይከበራሉ፡፡
በነገው እለት የእስልምና እምነት ተከታዮች የመውሊድ በዓል የሚከበር ሲሆን በክርስትና እምነት ተከታዮች የመስቀል በዓል በቀን 17/01/2016 ዓ.ም በተከታታይ ቀናት ይከበራል፡፡
በክልላችን (በሰባቱም) በ7 ማረሚያ ተቃማት ውስጥ የሚገኙ ታራሚዎችም በዓሉን በሉበት ማረሚያ ተቋም ከጠያቂ ዘመዶቻቸውና እርስ በርሳቸው እንኳን አደረሰን በመባባል የሰልፋሎ፡፡
ኮሚሽናችን ለሞላው ሀገራች እና ክልላችን እዝቦች እንዲሁም በደቡብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ለሚገኙ እህት የማረሚያ ኮሚሽን እና ተቋም አመራሮች እንዲሁም በለሙያዎች ፣በተቋማት ለሚገኙ የህግ ታራሚዎችና ለታራሚ ቤተ-ሰቦች በቀን/16/2016 ዓ.ም 1445 አመተ ሂጅራ ለሚከበረው መውሊድ ወይም የነብዩ መሀመድ (የለህ እዝነትና ሰላም በነብዩ ላይ ይወረድ) ልደት በዓልና በ17 2016 ዓ.ም በክርስትና እምነት ተከታዮች ዘንድ ለሚከበረው መስቀል በዓላት እንኳን አደረሳችሁ እያልን በዓሉ የሰላምና የብልፅግና እንዲሆንላችሁ እንመኛለን፡፡
ኮሚሽናችን በህግ ስልጣን በተሰጠው ፍርድ ቤት ትዕዛዝ የተላኩ የህግ-ታራሚዎችን አርሞና አንፆ ከማረሚያ ተቋም ሲፈቱ ራሰቸውን እንዲችሉና የበደሉትን መህበረሰብ እንዲኪሱ በማድረግ ላይ የሚገኝ ሲሆን ሰብዓዊ መብታቸው #ኢትዮጵያ በዓለም አቀፍ በተቀበለቻቸው መርሆች፣ድንጋጌዎችና ህጎች እንዲሁም በህገ-መንግስቱ የተያዙ ሰዎች መብቶችን ለማክበርና ለማስከበር በተቀመጡ ድንጋጌዎች መሰረት ለማስፈጸም ሰፊ ስራዎችን አከናውኗል፡፡
በቅርቡ የህዝብ ጥያቄን መሰረት በማድረግ በተሰጠው ድምፅ መሰረት የደቡብ ኢትዮጵያ ህዝቡችና የመዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል መቋቋሙ የቅርብ ግዜ ትዝታችን ነው፡፡
የማከላዊ ክልል ማረሚያ ኮሚሽን ከደቡብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል አብሮ የሰራቸውና የፈራቸው የጋራ የአሰራር፣እሴቶች እንዲሁም ለወጦች እጅግ በጣም ከፍታኛ መሆናቸውን ለማየት በቅርቡ የክልሎችና ፊድራል ማረሚያ ኮሚሽኖች በደረጉት ዓመታዊ የጋራ ስብሰባ ላይ ሁለት ተቋማትን በየዓመቱ በሚደረገው የክልሎችና የፊድራል ማረሚያ ኮሚሽኖች የጋራ ስብሰባ እንዲካፈሉና ልመዳቸውን በሀገር አቀፍ ደረጃ እንዲያስተላልፉ ከማስመረጡም በተጨማሪ የቀድሞ ደቡብ ክልል ኮሚሽኑን ጨምሮ ሽልማት ተበርክቶልናል፡፡
ሆኖም በተገኘው ለውጥ መኩራራት ሳይሆን የሚቀሩብን ብዙ ስራዎች እንዳሉ ከግምት ውስጥ በማስገባት በሁለቱም ኮሚሽኖች የተጀመረውን ሁለንተናዊ ለውጥችን ለማስቀጠል በጋራ ለመስራት ዝግጁ መሆኑን በዚሁ አጋጣሚ መግለጽ ይወዳል፡፡
በዓሉን በምናከብርበት ወቅት እንደወትሮ ሁሉ በመረዳዳትና በመደጋገፍ መንፈስ ሊሆን እንደሚገባው ከወዲሁ አደራ ለማለት ይወዳል፡፡
የማዕከላዊ ክልል ማረሚያ ቤቶች አስታዳደር ኮሚሽን!!
Click here to claim your Sponsored Listing.
Category
Contact the practice
Telephone
Website
Address
Hwassa
Awassa