Abruzzi Media
01/12/2021
ሰበር
የኢትዮጲያ መከላከያ ሰራዊት ፣ የአፋር ልዩ ሃይል ፣ የአማራ ልዩ ሀይል እንዲሁም ሚሊሻዎች በቅንጅት ከስትራቴጂካዊዋ ከተማ ጋሽና በተጨማሪ ታሪካዊቷን የላስታ ላሊበላ ከተማንና የላሊበላ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያን ተቆጣጥሯል።
19/11/2021
ሲኤንኤን ፣ ቢቢሲ ፣ ሮይተርስ እና ኤፒ ማስጠንቀቂያ ተሰጣቸው።
የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ባለስልጣን ለአራት የውጭ ሚዲያዎች የማስጠንቀቂያ ደብዳቤ ፅፏል።
እነዚህ ሚዲያዎች ሲኤንኤን (CNN)፣ ቢቢሲ (BBC)፣ ሮይተርስ (Reuters) እና አሶሺየትድ ፕሬስ (AP) ናቸው።
በማስጠንቀቂያ ደብዳቤው ላይ ሚዲያዎቹ ፦
- TPLFን ዓላማ ለማገዝ በኢትዮጵያ ላይ የሀሰት ዜናዎች እና የዜና ትንታኔዎችን ማዘጋጀታቸው እና ማሰራጨታቸው ፥
- የህግ ማስከበር ዘመቻውን የዘር ማጥፋት (Genocide) ዘመቻ አድርገው ሪፖርት ማድረጋቸው ፥
- በትግራይ ክልል የተፈጠረውን ሰብዓዊ ቀውስ ለመፍታት መንግስት የሚያደርገውን ጥረት የሚያበላሽ ዘገባዎችን መስራታቸው፣
- በትግራይ ክልል መንግስት ረሃብንን እና አስገድዶ መድፈር እንደጦር መሳሪያ እንደተጠቀመበት ሪፖርት ማድረጋቸው ፤
- በሀገሪቱ መሪ ተቋማት ላይ የስም ማጥፋት ሪፖርቶችን ማዘጋጀታቸው፤
- የሀገሪቱን መሪ በዓለም አቀፍ መድረክ ለማጣጣል እና ሀገሪቱን ከፍተኛ የዲፕሎማሲ ጫና ውሥጥ የሚከቱ ዜናዎችን ማዘጋጀታቸው ተገልጿል።
ተቋማቱ የጋዜጠኝነት መርህን አክብረው እንዲሰሩ መደበኛ እና መደበኛ ባልሆነ መልኩ ተደጋጋሚ ምክርና ማሳሰቢያ ሲሰጥ መቆየቱን የጠቀሰው ባለስልጣኑ፤ መገናኛ ብዙኃኑ ከድርጊታቸው ከመታቀብ ይልቅ አባብሰው መቀጠላቸውን አስታውቋል።
ለኢትዮጵያዊያን ደህንነት ሲባል የሚዲያ ተቋማቱ በቀጣይ ከዚህ ድርጊታቸው የማይታቀቡ ከሆነ ባለስልጣኑ በተሰጠው ስልጣን እና ሃላፊነት በመጠቀም የሰጣቸውን የሥራ ፈቃድ ለመሰረዝ እንደሚገደድ አስጠንቅቋል።
በኢመብባ ዋና ዳይሬክተር መሀመድ ኢድሪስ ተፈርሞ የወጣው የማስጠንቀቂያ ደብዳቤ ከላይ ተያይዟል።
Click here to claim your Sponsored Listing.
Category
Contact the business
Telephone
Address
Hawassa
Awassa