Addisout.Com

Addisout.Com

Share

Provide Information on Ethiopia Entertainment, Business,Politics and Travel

11/05/2026

አቡነ ፋኑ ኤል ይናገራሉ....🙏🏿

አሮጌ ጫማውን የማይሰጥ ሁሉ እኔን 120 ሚልዮን ብር ከየት አምጥቶ ሰጠ ይለኛል....

ቤቱን የሰራሁት ከዛሬ 21 አመት በፊት 3.1 ሚልዮን ብር ነው የፈጀብኝ ዛሬ ግን
ባለሙያዎች ገምተው 120 ሚልዮንብር ነው አሉ።

የብዙ ሰው ጥያቄ ግን ከዛሬ 21 አመታት በፊት 3 ሚልዮን ብር እጅግ ብዙ ብር ነው የሚል ነው....

❤️AddisOut Media❤️

08/05/2026

8 ሰው አስረዋል 9ኛው ቴዲ አፍሮ ራሱ ይሆን....?

የቴዲ አፍሮ አዲስ አልበም የሆነው "ኢቶሪካ" ግራፊክስ ባለሙያ ዳዊት ሰሎሞን በቁጥጥር ስር መዋሉ ዘግበናል። የ23 ዓመቱ ወጣት ዳዊት፣ ጓደኞቹ ጋር በሄደበት አጋጣሚ የተያዘ ሲሆን፣ ከመያዙ በፊትም ቤቱ በፖሊስ መፈተሹ ታውቋል።

ከእስሩ በስተጀርባ ያሉ አነጋጋሪ ነጥቦች...

✶ የ"ኢቶሪካ" አልበም መውጣቱን ተከትሎ፣ ዳዊትን ጨምሮ ለአርቲስቱ ቅርበት ያላቸው የታሰሩ ሰዎች ቁጥር አሁን ላይ 8 መድረሱ አውቀናል። ይህም በአብዛኛው መረጃ የማሰባሰብ ጉዳይ ይመስላል... በተለይ በእጽና ህገወጥ መሳሪያ ከዛ ዶክመንታሪ ወይም ቴዲን ማሰር?

✶ የዳዊት ቤተሰቦች እንደሚሉት፣ ወጣቱ የቀረበበት ክስ "ከአደንዛዥ ዕፅ እና ከሕገ-ወጥ መሣሪያ ዝውውር" ጋር የተያያዘ ነው። ፖሊስ በአራዳ ፍርድ ቤት አቅርቦት የ14 ቀናት የጊዜ ቀጠሮ ተፈቅዶበታል።

✶ የቴዲ ቅርብ የልብ ወዳጅ የአቶ ዩሱፍ ያሲን የጤና ሁኔታ አሳሳቢ ደረጃ ላይ መሆኑን ቤተሰቦቻቸው በጭንቀት ገልጸዋል።

የፖሊስ ምላሽ ምን ይመስላል?

የጀርመን ድምጽ እንደዘገበው የፌዴራል ፖሊስ የሕዝብ ግንኙነት ኃላፊ አቶ ጄላን አብዲ፣ ስለ ዳዊት ሰሎሞን እስር መረጃው እንደሌላቸውና ጉዳዩን አጣርተው ምላሽ እንደሚሰጡ ገልጸዋል።

እስከ አሁን ባለው መረጃ በአርቲስት ቴዎድሮስ ካሣሁን ላይ የደረሰ አንዳችም ነገር የለም።ይህ በቴዲ አፍሮ የቅርብ ሰዎች ላይ እየተወሰደ ያለው እርምጃ በብዙዎች ዘንድ ጥያቄን እያስነሳ ይገኛል።

የእናንተስ አስተያየት ምንድነው? የጥበብ ስራ ውጤት ወይስ ሌላ? በኮሜንት ያጋሩን።

❤️Addis🌕ut Media❤️

07/05/2026

የቴዲ አፍሮ አድናቂ ነኝ ግን...

ታዋቂው የአፋን ኦሮሞ ድምጻዊ ዮሰን ጌታሁን ከቴዲ አፍሮ ጋር ስላለው የሃሳብ ልዩነት ማብራሪያ ሰጠ።

ዮሰን "ሀገር የሞተችበት የት ሄዶ ያለቅሳል" በሚለው የቴዲ አፍሮ ግጥም ላይ እንደማይስማማ ገልጿል።ዮሰን ሲናገር፦ "ቴዲ 'ሀገር የሞተችበት...' ሲል እኔ ደግሞ 'ሀገሬ አልሞተችም፣ አለች' ብዬ አምናለሁ።

ኪነ-ጥበብ ለቴዲ እንደፈቀደችለት ሁሉ ለእኔም ሃሳቤን የመግለጽ መብት ትሰጠኛለች" ብሏል።ድምጻዊው አክሎም ከቴዲ አፍሮ ጋር ምንም ዓይነት የግል ቅሬታ እንደሌለውና እንደ ማንኛውም ኢትዮጵያዊ አድናቂውና ወዳጁ መሆኑን ጠቁሞ፣ ልዩነቱ "ሀገር ሞታለች" በሚለው የሃሳብ ፍሰት ላይ ብቻ መሆኑን አስገንዝቧል።

❤️Addis🌕ut Media❤️

Want your business to be the top-listed Media Company in Addis Abeba?
Click here to claim your Sponsored Listing.

Address


Addis Abeba