Computer trick and hacking ethiopia

Computer trick and hacking ethiopia

Share

30/08/2021

የአይፎን 13 የሳተላይት ግንኙነቶችን እንደ አማራጭ ይዞ እንደሚመጣ ተነገረ፡፡

በመስከረም ወር ለገበያ እንደሚቀርብ የሚጠበቀው አዲሱ የአፕል ኩባንያ ምርት አይፎን 13 የሳተላይት ግንኙነቶችን እንደ አማራጭ ይዞ እንደሚመጣ ተነገረ፡፡

የቴሌኮም አገልግሎቶች ተደራሽ በማይሆኑባቸው አካባቢዎች በታችኛው የመሬት ምሕዋር የሚገኙ ሳተላይቶችን በመጠቀም የድምፅ እና የአጭር መልዕክት አገልግሎቶችን ተደራሽ ማድረግ እንደሚችል ሲኔት ዘግቧል፡፡

አዲሱ ስልክ በሳተላይት አማካኝነት አገልግሎት መስጠት የሚያስችለው Qualcomm X60 የተባለ ቺፕ እንደሆነ ተገልጿል፡፡

ይህ አዲስ ገፅታ ከቴሌኮም አገልግሎቶች ርቀው ለሚኖሩ እና መሰል አገልግሎቶች ተደራሽ ባልሆኑባቸው አካባቢዎች የሚጓዙ ተጠቃሚዎችን ትኩረት እንደሚያገኝ ይጠበቃል፡፡ (Cnet, AICE)

23/03/2021

💥የቢል ጌት እና ጆ ባይደንን አካውንት ሀክ ያደረገው ታዳጊ እስር ተፈረደበት

ባሳለፍነው ሐምሌ የታዋቂ ግለሰብ እና ተቋማትን ትዊተር ገፅ ሀክ በማድረግ እነርሱን መስሎ የቢትኮይን ገንዘብ ዝውውር ይደረግለት ዘንድ በትዊት የጠየቀው የ18 ዓመት ታዳጊ ሦስት ዓመታትን በእስር ለማሳለፍ ተስማማ፡፡ ከአሜሪካኗ የፍሎሪዳ ግዛት የሆነውና ጥቃቱን ሲሰነዘር ገና የ17 ዓመት ታዳጊ የነበረው ግሬሄም አይቫን ክላርክ የጆ ባይደን፣ ቢል ጌት፣ ኢለን መስክ፣ ባራክ ኦባማ እና የሌሎችንም ዝነኞች ትዊተር የትዊተር ገፅ ነው ሀክ አድርጎ ድርጊቱን የፈፀመው፡፡

ክላርክ በቅድሚያ ወደ ገፆቹ መግባት የቻለው የትዊትር ሰራተኞችን በዚያው በድርጅቱ የኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ክፍል ውስጥ እንደሚሰራ ማሳመን ከቻለ በኋላ ነው፡፡ የግለሰቦቹ ገፅ ውስጥ ከገባ በኋላም “ከታች ባለው ሊንክ የሚላኩ ሁሉም ቢትኮይኖች እጥፍ ሆነው ይመለሳሉ” ብሎ ትዊት አድርጎባቸዋል፡፡ የፍርድ ቤት ሰነዶች እንደሚያሳዩት ከሆነ ግሬሄም በዚህ ድርጊቱ ከ100 ሺህ ዶላር በላይ መሰብሰብ ችሏል፤ ምንም እንኳን ጠበቆቹ የኋላ ኋላ አንድም ሳያስቀር መመለሱን ቢናገሩም፡፡

በከፍተኛ የደህንነት ጥሰት ውስጥ የወደቀው ትዊተርም ሁኔታው እንደተከሰተ ማንኛቸውም ማረጋገጫ የተሰጣቸው ወይም ቨርቲፋይ የሆኑ አካውንቶች ለሰዓታት ትዊት ማድረግ እንዳይችሉ አድርጓቸው ቆይቷል፡፡ በወቅቱ የከፍተኛ ሁለተኛ ደረጃ ተማሪ የነበረው ግሬሄምም በቀናት ጊዜ ውስጥ በሕግ አካላት ቁጥጥር ስል እንዲውል ሆኗል፡፡

ታዳጊው ከሕግ አካላቱ ጋር ባደረገው ስምምነት በተደራጀ የማጭበርበር ወንጀል ጥፋተኛነቱን አምኖ የቀረበ ሲሆን እስከ 30 ዓመታት ዘብጥያ ሊያስወርድ በሚችለው በዚህ ወንጀልም እንደ ታዳጊ ወንጀለኛ ተቆጥሮ ሦስት ዓመታትን ብቻ በእስር እንደሚያሳልፍ ተነግሯል፡፡ የተወሰነው የእስር ጊዜውንም “ቡት ካምፕ” ተብለው በሚታወቁት የታዳጊ ማቆያቀዎች እንደሚያሳልፍም ተነግሯል፡፡ የሂልስብሮ ግዛት አቃቢ ሕጉ አንድሪው ዋረን አላማቸው የታዳጊዎችን ሕይወት ማበላሸት ሳይሆን ከስህተታቸው እንዲማሩ መሆኑን ከግምት በማስገባት የቅጣት እርምጃዎቹ መወሰዳቸውን ተናግረዋል፡፡

ከጥቃቱ ጋር በተገናኘ ሜሶን ሼፐርድ እና ኒማ ፋዝሊ የተባሉ ከብሪታንያ እና ከዚያው ከፍሎሪዳ የሆኑ ሌሎች ሁለት ታዳጊዎችም ክስ የተመሰረተባቸው ሲሆን የእነርሱ ጉዳይ በሕግ እየታየ ይቆያል፡፡

ምንጭ፤ The Guardian

ETHIO _Sat TVET TOT 15/01/2021

✳️ ኦርጅናሉን ስልክ ከፌኩ በቀላሉ እንዴት መለየት ይቻላል። እነዚን መንገዶች በመጠቀም ፌክ ሳምሰንግ ስልኮችን መለየት ይችላሉ።

🏷 የስልኩን ቀፎ አካላዊ ገጽታዎች በመገምገም
ፌክ ሳምሰንግ ስልክ

1. የስክሪኑ መስታወት ጥራት የለዉም
2. ስክሪኑ ከቀፎዉ ጠርዝ በጣም ይርቃል
3. ስክሪኑ ድምቀት ይጎድለዋል
4. የሳምሰንግ ሎጎ (ሳምሰንግ የሚለዉ ጽሁፍ) ሲነካ
ይሻክራል፣ በደንብ ከተጫኑት ይለቃል
5. ከኦርጂናል ስልኮች ጋር ሲያስተያዩት፤ የባትሪ መክደኛዉን ሲከፍቱ የሚታዩ ትንንሽ አካሎች እና ባትሪዉ ላይ የሚገኙት መረጃዎች የተለያዩ መሆናቸዉን
ይመለከታሉ፡፡

🏷 የስልኩን ፍጥነት እና ትእዛዞችን አፈጻፀም በመገምገም

1. በስልኩ ፎቶዎችን ለማንሳት ይሞክሩ፣ በፌክ ሳምሰንግ
ስልኮች የሚያነሱት ፎቶ ጥራት የወረደ ይሆናል
2. በተመሳሳይ ጊዜ በርካታ ጌሞች እና አፕሊኬሽኖችን
ለመክፈት ይሞክሩ፣ ፌክ ስልኮች ስታክ(ቀጥ) የማለት ባህሪይ ያሳያሉ፡፡
3. ስልኩን አጥፍተዉ ያብሩት፣ ፌክ ስልኮች ቶሎ አይከፍቱም

🏷 የስልኩን የምርት መረጃዎች በመገምገም

1. ከአፕሊኬሽን ማዉጫዉ ላይ፣ Settings የሚለዉን ይጫኑ
3. ከ Settings ላይ More የሚለዉን ይጫኑ እና የሚለዉን በመጫን ስልኩ ላይ መጫን ሚችሉትን የዳታ መጠን ይመልከቱ፤ ከኦርጂናሎቹ ስልኮች በጣም ያነሰ ከሆነ ፌክ መሆኑን ያረጋግጣሉ፡፡

እንዲሁም About device የሚለዉን ይጫኑ እና
የስልኩን ሞዴል ቁጥር እና baseband, build number
ጉግል ላይ ይፈልጉት፣ የሚያገኙት መልስ ፌክ ወይም ኦርጅናል መሆኑን ይነግሮታል፡፡

የሳምሰንግ ኮዶችን በመጠቀም ወደ ስልክ መደወያዉ በመሄድ፣ ከዚህ በታች የተጠቀሱትን ኮዶች ያስገቡ እና Call የሚለዉን ይጫኑ፤ ስልኩ
ያስገቡትን ኮድ አዉቆ መልስ መስጠት ከቻለ ኦርጅናል
መሆኑን ያረጋግጣሉ፡፡ ካልሆነ ግን ፌክ ስልክ ነዉ፡፡

🔔 * #0* # #አጠቃላይ መገምገሚያ
🔔 * #1234 # or * #9999 # ስልኩ የሚጠቀመዉን
#ሶፍትዌር እና #ሞደም ማወቂያ
🔔 * #12580*369 # #ስለ ስልኩ #ሶፍትዌር እና #ሀርድዌር ማወቂያ
🔔 * #06 # #የስልኩን ኢንተርናሽናል #መለያ ቁጥር
ማወቂያ
🔔 * #9998*246 # #የስልኩን #የባትሪ እና ሚሞሪ መረጃዎች ማወቂያ
ሳምሰንግ ኪይ(Samsung Kies) ሶፍትዌርን በመጠቀም ከላይ በተጠቀሱት መንገዶች ፌክ ሳምሰንግ ስልክን መለየት ካልቻሉ ይህን ሶፍትዌር ይጠቀሙት፡፡

1. Samsung Kies ሶፍትዌርን ኮምፒዉተሮት ላይ
ይጫኑት
2. ለማረጋገጥ የፈለጉትን ስልክ ከኮምፒዉተሮት ጋር ያገኛኙት
3. ሶፍትዌሩ ስልኩን ያነበዉ እና የስልኩን ስም ፣ የሚጠቀመዉን ሶፍትዌር እና ሀርድዌር ያሳያል፤
ሶፍትዌሩ ስልኩን ማንበብ ካልቻለ በድጋሚ ይሞክሩት በድጋሚ ማንበብ ካልቻለ ሰልኩ ፌክ መሆኑን ያረጋግጣሉ፡፡

ETHIO _Sat TVET TOT You can view and join right away.

29/12/2020
Want your business to be the top-listed Computer & Electronics Service in Addis Ababa?
Click here to claim your Sponsored Listing.

Telephone

Website

Address


Addis Ababa
1000