Bisrat Promotion

Bisrat Promotion

Share

31/08/2024

በ17ኛው የፓራሊምፒክ ጨዋታዎች አትሌት ትዕግስት ገዛኸኝ በ1500 ሴቶች የጭላንጭል (T-13) ፍጻሜ ለኢትዮጵያ የመጀመሪያ የወርቅ ሜዳሊያ አስገኝታለች።

80 ሺህ ተመልካች በሚያስተናግደው የስታድ ደ ፍራንስ ብሔራዊ ስታዲየም በተደረገው ውድድር አትሌት ትዕግስት 4 ደቂቃ ከ22 ሴኮንድ ከ39 ማይክሮ ሴኮንድ አሸንፋለች።

አትሌት ትዕግስት እ.አ.አ በ2021 በቶኪዮ በተካሄደው 16ኛው የፓራሊምፒክ ጨዋታዎች በተመሳሳይ ርቀት ተሳትፋ በውድድሩ ታሪክ ለኢትዮጵያ የመጀመሪያውን የወርቅ ሜዳሊያ ማምጣቷ የሚታወስ ነው።

ሞሮኮዋዊቷ አትሌት ፋጡማ ኢዝሃራና አሜሪካዊቷ አትሌት ሊዛ ኮርሶ ሁለተኛና ሶስተኛ በመውጣት የብርና የነሐስ ሜዳሊያ አግኝተዋል።

በውድድሩ ላይ 11 አትሌቶች ተሳትፈዋል።

በተያያዘም ዛሬ ቀን ላይ በተካሄደ የወንዶች 1500 ሜትር የእጅ ጉዳት (T-46 ምድብ) የፍጻሜ አትሌት ገመቹ አመኑ ስምንተኛ ደረጃን ይዞ አጠናቋል።

10/02/2024

የኢቢሲ ጋዜጠኛ ኢያሱ ፈጠነ ከዚህ አለም በሞት ተለየ
**************

ለረጅም አመታት በኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን ያገለገለው ጋዜጠኛ ኢያሱ ፈጠነ ከዚህ አለም በሞት ተለየ።

ጋዜጠኛ ኢያሱ ፈጠነ ከ1999 ዓ.ም ጀምሮ በኢቢሲ ከሪፖርተርነት እስከ ከፍተኛ ኤዲተርነት አገልግሏል።

በ1975 ዓ.ም ሰኔ 12 ቀን በወንጂ ሸዋ የተወለደው ኢያሱ በተወለደ በ41 አመቱ በድንገተኛ አደጋ ከዚህ አለም በሞት ተለይቷል።

ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በኢትዮጵያ ቋንቋዎችና ስነ ጽሑፍ በመጀመሪያ ድግሪ የተመረቀው ጋዜጠኛ ኢያሱ ህይወቱ እስካለፈችበት ቀን ድረስ ላለፉት 17 አመታት በሞያው ሀገሩን ሲያገለግል ቆይቷል።

ጋዜጠኛ ኢያሱ ፈጠነ ባለትዳርና የሁለት ልጆች አባትም ነበር።

የኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን በጋዜጠኛ ኢያሱ ፈጠነ ህልፈተ ህይወት የተሰማውን ጥልቅ ሃዘን እየገለፀ፤ ለቤተሰቦቹ ለወዳጅ ዘመዶቹ እና ለስራ ባልደረቦቹ መፅናናትን ይመኛል፡፡

Want your business to be the top-listed Media Company in Addis Ababa?
Click here to claim your Sponsored Listing.

Telephone

Website

Address


Addis Ababa
27526