OCS ICT
29/06/2020
✍ #የህጻናት #ምግብ #አዘገጃጀት
*******************************
ውድ የዶክተር አለ ቤተሰቦች በዚህ ጽሁፋችን ላይ ለልጆቼ ምልሰራ ብለው ለሚያስቡ ወላጆች ቀላል እና ጣፋጭ የሆነ ሁለት አይነት የህጻናት ምግብ አቅርበናል ይጠቀሙት ልጆቾን ያስደስቱበታል
👉👉 #የሩዝ #፣ካሮትና #ድንች #ውህድ #ለህጻናት #ልጆቻችን
✅ #ግብዓቶች
📌 ሁለት የሻይ ማንኪያ ሩዝ
📌 አንድ መካከለኛ መጠን ያለው ካሮት
📌 አንድ መካከለኛ መጠን ያለው ድንች
👉👉 #አዘገጃጀት
📌 ሩዙን በደንብ ማጠብ
📌 ካሮቱንና ድንቹን ልጦ በትንንሽ መጠን መክተፍ
📌 አንድ የውሃ ብርጭቆ ውሃ ወይም የተዘጋጀ ወተት ጨምሮ አንድ ላይ ጨምሮ ማብሰል።
📌 በጎድጓዳ ሳህን ጨምሮ በማንኪያ መመገብ
👉👉 #የምስር #እና #አትክልት #ሾርባ
✅ #ግብአቶች
📌 1 የቡና ሲኒ የተለቀመ ምስር
📌 1 ሽንኩርት
📌 1 ድንች
📌 1 ካሮት
📌 4 የአበባ ጎመን ግንድ
📌 4 የጥቅል ጎመን ቅጠሎች
📌 1 የሻይ ማንኪያ እርድ
📌 1 የሾርባ ማንኪያ ዘይት
📌 4 የቡና ሲኒ ውሃ
👉👉 #አዘገጃጀት
📌 የተለቀመውን ምስር በደንብ ማጠብ
📌 ሽንኩርት ልጦና አጥቦ መክተፍ፤ ሽንኩርቱን ከዘይቱ ከምስሩ እና ከእርዱ ጋር ለ 5 ደቂቃ ማቁላላት እና ውሃ ከልሶ ማንተክተክ
📌 ድንቹንና ካሮቱን ልጦ አጥቦ መክተፍ፤ ጥቅል ጎመኑንና አበባ ጎመኑን አጥቦ መክተፍ
📌 የተከተፉትን አትክልቶች ድስቱ ውስጥ ጨምሮ ከ15-20 ደቂቃ ማብሰል
📌 መብሰሉን ካረጋገጥን በኃላ፤ በመፍጫ በምንፈልገው የልስላሴ መጠን ማላም (ከወፈረ ለማቅጠን ውሃ መጠቀም ይቻላል)
📌 የተፈጨውን ውህድ ደስት ላይ ገልብጦ ለ10 ደቂቃ ማንተክተክ
📌 በመመገቢያ ሰሃን ቀንሶ መመገብ፡፡
📌 የተረፈ ካለ በ24 ሰዓት ውስጥ አሙቆ መመገብ፡፡
**********************************
👌👌👌 ከህጻናት አመጋገብ ጋር በተያያዘ እንዲሁም በማንኛውም የጤና ጉዳይ ጋር በተያያዘ ማማከር ከፈለጉ የዶክተር አለ 8809 ሀኪሞች ላይ በመደወል ያማክሩ!! ከጧት 2 ሰዓት እስከ ማታ 12 ሰዓት ከሰኞ እስከ ሰኞ ቢደዉሉ የዶክተር አለ ሀኪሞች ሊያማክሩዎ በመስመር ላይ ይገኛሉ!!!
**********************************
👌👌👌ተጨማሪ የጤና መረጃ እንዲደርሶ፦
✅ የዶክተር አለ 8809 የቴሌግራም ገፅ ፦
👉👉👉 T.ME/DOCTORALLE8809
✅ የዶክተር አለ 8809 የፌስቡክ ገፅ፦
👉👉👉 http://tiny.cc/gf606y
( #በጤና #ባለሙያ #ርብቃ)
20/09/2019
ቪፒኤን ለምን እንጠቀማለን? ጥቅሙስ ምንድን ነው?
ቪፒኤን (VPN) የኢንተርኔት ግንኙነታችንን ደህንነቱ የተጠበቀ እንዲሆን እና የምንለዋወጣቸዉ መረጃዎች ከመረጃ በርባሪዎች ጥቃት የተጠበቁ እንዲሆኑ የሚረዳ ሶፍትዌር ነው፡፡
ተጠቃሚዎች የቪፒኤን ግንኙነት ሲፈጥሩ ደህንነቱ የተረጋገጠ የመረጃ መተላለፊያ መንገድ ይፈጥራሉ፡፡
ቪፒኤን በተለየ ማስተላለፊያ መንገድ የሚተላለፉ ዳታዎችን ሚስጥራዊ የሚያደርግ በመሆኑ ማንኛዉም የመረጃ በርባሪ የመረጃዉን ይዘት ማዎቅ እንዳይችል ከማድረጉ ባሻገር የመረጃ ግንኙነቱ የሚሆነዉ በሁለቱ ባለመብት(ባለፍቃድ) አካላት ብቻ ነዉ፡፡
ሶፍትዌሩ የቀጥታ የበይነ-መረብ ግንኙነት 'የኦንላይን' እንቅስቃሴ በመደበቅ እንዲሁም እንዳይታይ በማድረግ(የትኛዉን ድረ-ገጽ እንደጎበኘን እና ምን አይነት ዳታዎችን እያስተላለፍን መሆኑን) ባለማሳዎቅ ያግዘናል፡፡
ይህን አገልግሎት በተገቢው መንገድ ማግኘት የምንችለው ደግሞ የቪፒኤን ሶፍትዌር ደንበኛ በመሆን አገልግሎቱን መጠቀም ስንጀምር ነዉ፡፡
ደንበኛ በመሆናችን የምናስተላልፋቸዉ ዳታዎች ከመዳረሻዉ ኔትወርክ ከመድረሳቸዉ በፊት ይመሰጠራሉ፡፡
ቪፒኤንን ለምን መጠቀም አስፈለገ?
• ማንኛዉንም የዌብ ተግባራት ኢንክሪፕትድ(የተመሰጠሩ) እንዲሆኑ ያደርጋል
• የቀጥታ የበይነመረብ ግንኙነት (online) ተግባራችንን በመደበቅ ከሚከታተሉን የመረጃ መንታፊዎች ያድነናል፡፡
• መዳረሻችንን በግልፅ እንዳይታይ እንዲሁም በቦታ የተገደቡ ዌቦችና ይዘቶችን አገልግሎት ማግኘት እንድንችል ይረዳናል
• በዌብ(በይነ-መረብ) ተግባር ላይ የማንነት መታዎቅ አጋጣሚን በእጅጉ ያጠባል
• የህዝብ ዋይፋይ ሆትስፖቶችን በምንጠቀምበት ጊዜ ግንኙነቱ ደህንነቱ የተጠበቀ እንዲሆን ያደርግልናል፡፡
በአጠቃላይ ደህንነቱ የተጠበቀ መረጃና የመረጃ ልዉዉጥ መንገድ ይፈጠርልናል ማለት ይቻላል፡፡
Click here to claim your Sponsored Listing.
Category
Website
Address
Addis Ababa
Opening Hours
| 09:00 - 17:00 |