YeneApp.com

YeneApp.com

Share

01/04/2020

➖ Dr. Nuredin Luke ➖

➽ ከሌላው አለም በመማር ሊመጣብን የሚችለውን ጉዳት ለመቀነስ እንስራ፡፡

በኮሮና -19n እመም መያዝ ማለት መሞት ማለት አይደለም፡፡

ወደ 80 % የሚሆኑ ሰዉች ከቀላል እስከ መካከለኛ የህምሙ ምልክት ያሳዩ ሰዎች ከሀለት እስከ ሶስት ሳምንት ውስጥ ይሻላቸዋል፡፡
የተቀሩትም በከፈተኛ የህክምና እርዳታ ተደርጎላቸው ከአራት እስከ ስምንት ሳምንታት እየተሸላቸው ይገኛሉ፡፡ አሁን እያገኘን ባለው ማስረጃ ህይወታቸውን እያጡ ያሉት ከ5% በታች ነው፡፡
ይሁን እንጂ ይሄ በሽታ ከባዱን ነገር አሳይቶናል፡፡

1፡- ትዳራቸውን ከ60 ዓመት በላይ አንድላይ የኖሩትን አሮጊት እና ሽማግሌ በአንድ ቀን ህይወታቸውን አጥቷል፡፡

2፡- በዚሁ እመም በአንድ ቤተስብ ውስጥ ከሚኖሩት ከሶስት እሰከ አራት ሰውች እየሞቱ እንደሆነ እየሰማን ነው፡፡

3፡- ሙሉ ቤተሰብ በዚሁ ተላላፊ እና አስከፊ በሽታ በመታመም አስታማሚ እንኳን እያጡ እንደሆነ እየሰማን ነው፡፡

4፡- ሀኪሞች ቀን ከለሊት ሰዎችን ለማዳን ደፋ ቀና እያሉ በሚሰሩበት ጊዜ በዚሁ እመም በመያዝ ህይወታቸውን እያጡ እደሆነም ሰምተናል፡፡

5፡- ልጆች ያለቤተሰብ እየቀሩ ነው፡

6፡- ሀኪም ቤት መድረስ አቅቶት መንገድ ላይ ወድቆ የቀረም እያየን ነው፡፡

7፡- ወጉን የጠበቀ የቀብር ስነ- ስረዓት እንኳን አጥቶ ቤተሰብ ከሩቅ ሆኖ ሲያዝን አይተናል፡፡

8፡- ሰርግ እና ሀዘን ላይ የተገኙት ሰዎች በዚሁ አስከፊ ቫይረስ ተይዘው ሲመለሱ ታውቋል፡፡
ከእንደዚህ አይነቱ አሳዛኝ ነገር ቀድመን ተምረን እራሳችን እና ማህበረሰባችን በመጠበቅ ሊመጣብን ከሚችለው ጉዳት መቀነስ እንችላለን፡፡
ይሄም የሁላችን አላፊነት ነው፡፡
ሰላም ሁኑ፡፡

➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖

Photos 06/09/2017

Happy New Year to all Ethiopians!
#2010

Want your business to be the top-listed Computer & Electronics Service in Addis Ababa?
Click here to claim your Sponsored Listing.

Telephone

Address


Addis Ababa