CMTV

CMTV

Share

Photos from CMTV's post 18/05/2026

በክርስቶስ ተልዕኮ ቤተክርስቲያን የእሁድ አገልግሎት

ርዕሰ ፦ ለእግዚአብሔር ክብር መገለጥ እራሳችንን እናዘጋጅ

- እግዚአብሔር አምላክ ክብሩ በእኛ እንዲገለጥ ይፈልጋል ።

- የሀጢያት ትልቁ ክፋት የእግዚአብሔርን ክብር ከህዝቡ መዉሰድ ነው ።

- እግዚአብሔር ሰዉን የፈጠረው በዚህ ምድር ላይ እንደ እንሰሳ ኑሮ እንዲያልፍ ሳይሆን የእግዚአብሔር ክብር መገለጫ እንዲሆን በዚህ ምድር ላይ ክብሩን እና ማንነቱን ተሸካሚ እንዲሆን ነው ።

- በሰማይ የእግዚአብሔርን ክብር የሚያንፀባርቅ የሚያስተጋባ እግዚአብሔርን በሙላት ሲገልጠዉ የኖረ ከዘላለም ዘመናት ጀምሮ ልጁ ኢየሱስ ክርስቶስ ነው ።

- እግዚአብሔር አስቀድሞ እኛን በእቅድ ደረጃ ሲያዉቀን ገና ሳይፈጥረን የወሰነን የልጁን መልክ እንድንመስል ነው ።

- እግዚአብሔር እኛን አስቀድሞ የወሰነን ያን የእግዚአብሔር ባህሪ እና ማንነት መገለጫ የሆነዉን ክርስቶስን እንድንመስል ነው ።

- ክርስቶስ የእግዚአብሔር የክብሩ የባህሪዉ የማንነቱ ነፀብራቅ ነው ።

- እግዚአብሔር በፈጠረው ፍጥረት ክብሩ ይገለጣል ።

- የእግዚአብሔር መገኘት ጥልቅ የሆነ የእግዚአብሔርን ህያዉነት መኖሩን ይገልጣል ።

- የእግዚአብሔር ክብር ሲመጣ ሰዎች ንሰሃ ይገባሉ ።

- የእግዚአብሔር ክብር ሲመጣ የሰው ልብ ይነካል ይቀልጣል።

- የሰዉን ልብ የሚነካዉ የእግዚአብሔር ክብር መገለጥ መገኘት ነው።

- የእግዚአብሔር ክብር ሲመጣ የህይወት መለወጥ ያመጣል ።

- የእግዚአብሔር ክብር ሲገለጥ የቅድስናዉ መታየት ይገለጣል ።

- ታምራት የእግዚአብሔርን ክብር ይገልጣል ።

- የእግዚአብሔር ክብር ቅድስናዉ ፣ ፍቅሩ ፣ ምህረቱ ፣ ፅድቁ ፣ እዉነተኛነቱ ፣ እነዚህ ባህሪያቶች የእግዚአብሔር ክብር ነው ።

Want your place of worship to be the top-listed Place Of Worship in Addis Ababa?
Click here to claim your Sponsored Listing.

Category

Address


Ararat Round About To Gurd Sholla 1 Street
Addis Ababa

Opening Hours

Monday 08:00 - 18:00
Tuesday 08:00 - 18:00
Wednesday 08:00 - 18:00
Thursday 08:00 - 18:00
Friday 08:00 - 19:00
Saturday 08:00 - 18:00
Sunday 07:00 - 15:00