Documents Authentication and Registration service

Documents  Authentication and Registration service

Share

26/05/2026

ለመላው የእስልምና እምነት ተከታዮች
እንኳን ለኢድ አል-አድሃ (አረፋ) በዓል በሰላም አደረሳችሁ!
*******
የሰነዶች ማረጋገጫና ምዝገባ አገልግሎት በዓሉ የሰላም እና የደስታ እንዲሆን ይመኛል።

ኢድ ሙባረክ!
********
የሰነዶች ማረጋገጫና ምዝገባ አገልግሎት
ምንጊዜም ቅድሚያ ለተገልጋይ!
authentication and registration service

14/05/2026

ሌላ የአገልግሎት የክፍያ አማራጭ

የሰነዶች ማረጋገጫ እና ምዝገባ አገልግሎት ክፍያዎን
በሲቢኢ ብር በቀላሉ ይፈፅሙ!


✅ የሲቢኢ ብር ፕላስ መተግበሪያዎን ከፍተው 'ክፈል’ / ‘Pay’ ወደሚለው አማራጭ ይግቡ፤

✅ ‘ሂሳብ ክፍያ’/ ‘Pay Bill’ የሚለውን ይምረጡ፤

✅ ‘Gov Services’ የሚለውን ተጭነው ወደ ‘Dars (Documents Authentication and Registration Service)’ አማራጭ ይግቡ፤

✅ የቢል ማጣቀሻ ቁጥር (Bill Reference Number) አስገብተው የክፍያ መጠኑን በማረጋገጥ ክፍያዎን ይፈፅሙ፡፡

**************
#ክፍያዎን

12/05/2026

ይህንን ያውቃሉ?

ግንቦት4 ቀን 2018 ዓ.ም

የሰነዶች ማረጋገጫና ምዝገባ አገልግሎት በቀን ከስድስት ሺህ በላይ ተገልጋዮች በማስተናገድ በርካታ ልዩ ልዩ አገልግሎቶችን ተደራሽ እያደረገ ይገኛል፡፡ ከነዚህ አገልግሎቶች አንዱ ከጋብቻ በፊት የሚደረግ የግል ንብረትን ማግለል ውል ሰነድ አረጋግጦ መመዝገብ፣ (የቤተሰብ ህ/ ቁ/42) ነው፡፡

*ይህንን አገልግሎት ለማግኘት ተገልጋዮች ማሟላት ያለባቸው ቅድመሁኔታዎች የሚከተሉት ናቸው :-

ሀ. የሚረጋገጠውን የውል ሰነድ ይዘት በተቋሙ የአገልግሎት መስጫ ሲስተም ተሞልቶ የጉዳይ መከታተያ ቁጥር መያዝ ፤

ለ. የፈራሚዎች አና የእንዳንዳቸው ሁለት ሁለት ምስክሮች፤ የነዋሪነትና እና ፋይዳ መታወቂያ ፤

ሐ. የተዋዋዮች የአገልግሎት ጊዜው ያላለፈበት ያላገባ ማስረጃ ፤

መ. የሚገለለው ንብረት የባለቤትነት ማስረጃ ፡፡

Want your organization to be the top-listed Government Service in Addis Ababa?
Click here to claim your Sponsored Listing.

Telephone

Address


Addis Ababa
29935