Sales Agent
04/08/2024
22/07/2024
የአንዲት አፍሪካዊት እናት ተማጽኖ !!😢
ከስሯ የተንበረከከችውን ሴት ፡ ከምንም ባለመቁጠር ፡ በዚህ መልኩ እያናገረች ያለችው ኬንያ ውስጥ የአንድ ትንሽ ከተማ አስተዳዳሪ ናት ።
ነዋሪዎቹን ለማወያየት መጥታ ነው ። እና በመከራ የማይገኙትን ባለስልጣናት ድንገት ያገኘችው ይህች እናት አጋጣሚውን በመጠቀም ፡ ተንበርክካ እየለመነች ነው ።
" እባክዎ ልጄን ስራ ያስገቡልኝ " እያለች ።
ክብር ለልጆቻቸው ሲሉ የሰው ፊት የሚያዩ ፡ የባለስልጣናትን ደጅ ለሚጠኑ ወላጆች ይሁን ።😢😔
(ዋሲሁን ተስፋዬ)
10/07/2024
ጥብቅ ማሳሰቢያ ለሴቶች‼️
ራስን የሚያስት መድኃኒት በመጠጣቸው ውስጥ እየተጨመረ የሚደፈሩ ሴቶች ቀን በቀን እየጨመሩ ነው።
(መልእክቱን ሼር ያድርጉ)
በግሌ ከማክማቸው ሴቶች መካከል የተወሰኑ ይሄንን መሰል ታሪኮች የነገሩኝ ሲሆን ከተለያዩ ሰዎችም ተመሳሳይ ገጠመኞችን በየቦታው እየሰማሁ ነው። በተለይም ይሄ በክለቦችና መዝናኛ ስፍራዎች በድራፍትና ውስኪ ውስጥ ተጨምሮ የሚሰጠው አደንዛዥ መድኃኒት ሽታና ቀለም ስለሌለው ለተጠቂዋ ሴት ምንም አይነት ፍንጭ የማይሰጥ መሆኑ ችግሩን አስጊ አድርጎታል።
እናም ይሄንን መድኃኒት ከመጠጧ ተጨምሮባት የጠጣች ሴት በአጭር ጊዜ ውስጥ ንቃተ-አእምሮዋ እጅግ ይወርድና ሰመመን ውስጥ ትገባለች። ብዙዎቹ የሚነቁት ከማያውቁት መኝታ ክፍል ውስጥ ሁሉ ነገር ተከናውኖ ካበቃ በኋላ ነው።
ስለዚህ በቅጡ ከማያውቁት ሰው ጋር በመዝናናት ሰበብ መገናኘት፣ በተለይም መጠጥ ቤቶች ውስጥ መጋበዝና መጠጥ መጎንጨት ትልቅ የአካላዊና ሥነልቦናዊ ጠባሳ ጥሎ ሊያልፍ እንደሚችል ማወቅ ያሻል። በተለይም በተለምዶ የቤት ልጅ የሚባሉ ሴቶችና ታዳጊዎች ላይ ይሄ ነገር እየተበራከተ ስለሆነ ቤተሰቦች ከፍተኛ ጥንቃቄ ማድረግ አለባችሁ።
አያድርገውና ሁኔታው ከተከሰተም ሴቶች ወዲያውኑ ለፖሊስ መጠቆም፣ የእርግዝናና በሽታ መከላከያ መድኃኒቶችን መውሰድ እንዲሁም የሥነአእምሮ ባለሙያ ማማከር አለባችሁ።
ምስጢራዊነቱ ስለሚሻል የመድኃኒቱን ስም ከመጥቀስ ተቆጥቢያለሁ።
(ዶ/ር ኤልያስ ገብሩ አእምሮ፣
የሥነ-አእምሮ ስፔሻሊስትና የሥነ-ልቦና አማካሪ)
10/07/2024
Click here to claim your Sponsored Listing.
Category
Telephone
Website
Address
Addis Ababa