Health Insurance Network

Health Insurance Network

Share

16/05/2026

📢 ጫት መቃም፦ ከጊዜያዊ "መርቃና" ጀርባ የተደበቁት አስከፊ የጤና እና የህይወት ጠንቆች

🩸​ብዙዎች ጫትን ለደስታ፣ ለስራ ማነቃቂያ ወይም ለጭንቀት ማስታገሻነት እንደሚጠቀሙት ይናገራሉ።

🩸ነገር ግን ከዚህ ጊዜያዊ ስሜት በስተጀርባ ሰውነትን የሚያደቁ፣ አእምሮን የሚያዝሉ እና ቤተሰብን የሚበትኑ ዘርፈ ብዙ ምስቅልቅሎች እንዳሉ በሳይንሳዊ መረጃዎች ተረጋግጧል።

🩸የጫት ተፅዕኖ ከግለሰብ አልፎ ሀገራዊ ጠንቅ እየሆነ መምጣቱን ልታውቁት ይገባል።
​➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖
​🕹️በየቀኑ የሚለጠፉ ተመሳሳይ ጠቃሚ ምክሮችን እንድያገኙ በመጀመርያ ፔጃችን ልጥፉን በማድረግ ይጀምሩ!!

​🕹️የባለሙያ ምላሾች ለማግኘት:
​👉Website: https://unitytele-health.com

​📲 አገልግሎቱን በቀላሉ ለማግኘት እና ቀጠሮ ለማያዝ የሞባይል መተግበሪያችንን ከታች ባለው ሊንክ በመጠቀም ይጫኑ፦
​👉https://t.me/Drbrirukhealthtips123/7500
​እናመሰግናለን 🙏🙏🙏
​➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖
​💡 ጥልቅ የጤና ጉዳቶች:

​በጫት ውስጥ ያሉት ካቲኖን (Cathinone) እና ካቲን (Cathine) የተባሉ ንጥረ ነገሮች በማዕከላዊ የነርቭ ስርዓት ላይ ልክ እንደ አምፌታሚን (Amphetamine) አይነት ጠንካራ ተፅዕኖ ያሳድራሉ።

​📌 1. የልብና የደም ዝውውር ስርአት ላይ (Cardiovascular System)፦

​ከፍተኛ የደም ግፊት፦ ጫት የልብ ምትን በማፋጠን እና የደም ቧንቧዎችን በማጥበብ ለድንገተኛ የልብ ህመም (Myocardial Infarction) እና ለስትሮክ (Stroke) ተጋላጭነትን በከፍተኛ ሁኔታ ይጨምራል።ጥናቶች እንደሚያሳዩት ቃሚዎች ላይ የልብ ምት መዛባት (Arrhythmia) በብዛት ይታያል።

​📌 2. የአእምሮ ጤና (Mental Health)፦

​ሳይኮሲስ (Psychosis)፦ በከፍተኛ ሁኔታ የሚቅሙ ሰዎች ከእውነታው ዓለም መራቅ፣ በሌለ ድምፅ መባከን (Hallucinations) እና ከፍተኛ ጥርጣሬ (Paranoia) ሊያጋጥማቸው ይችላል።

​ድብርት (Depression)፦ የጫቱ ስሜት በሚለቅበት ጊዜ (Crash phase) ግለሰቡ ከፍተኛ የሆነ የባዶነት ስሜት፣ የተስፋ መቁረጥ እና ራስን የማጥፋት ሃሳብ ሊመጣበት ይችላል።

​📌 3. የምግብ መፈጨት እና ሜታቦሊዝም፦

​የአፍ ካንሰር፦ በጫት ውስጥ ያሉት ታኒኖች (Tannins) እና አርሶ አደሮች የሚረጩት ፀረ-ተባይ ኬሚካሎች በአፍ ውስጥ የሚገኙ ሴሎችን በመለወጥ ለአፍ እና ለጉሮሮ ካንሰር ያጋልጣሉ።

​የሆድ ድርቀትና ኪንታሮት፦ ጫት የምግብ መፈጨት ጉዞን ስለሚያዘገይ ለከፋ ድርቀት እና ለሄሞሮይድ (Hemorrhoids) ዋነኛ መንስኤ ነው።

​📌 4. የወሲብና የስነ-ተዋልዶ ጤና፦

​የወሲብ ብቃት ማጣት (Erectile Dysfunction)፦ መጀመሪያ ላይ ስሜትን የሚያነቃቃ ቢመስልም፣ በረጅም ጊዜ ግን የደም ዝውውርን በማስተጓጎል እና የነርቭ ስርዓትን በማዛባት ለወሲብ ብቃት ማነስ እና ለዘር ፍሬ (S***m) ጥራት መጓደል ምክንያት ይሆናል።

​🕹️ ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ውድመት:

​◾ የጊዜ ዝርፊያ፦ አንድ ቃሚ በአማካይ በቀን ከ 4 እስከ 8 ሰአታት በመቃም ያሳልፋል። ይህ ማለት በዓመት ውስጥ በሺዎች የሚቆጠሩ የምርታማነት ሰዓታት ይባክናሉ ማለት ነው።

◾ የባህሪ ለውጥ፦ ጫት ሱስ (Dependence) ስለሚያስከትል፣ ግለሰቡ ጫት ባላገኘበት ወቅት ሊንቀጠቀጥ፣ ለንዴት እና ለቤተሰብ አለመረጋጋት ምክንያት ይሆናል።

◾ ተጓዳኝ ሱሶች፦ "ቃናውን ለመስበር" በሚል የሚወሰዱ አልኮል፣ ሲጋራ እና ሺሻ የጤና ጉዳቱን በሶስት እጥፍ ያባብሰዋል።

◾ የኬሚካል አደጋ፦ አሁን ላይ የሚመጡ ጫቶች ላይ የሚረጩት ኬሚካሎች ለኩላሊት እና ለጉበት ከባድ ጉዳት እያደረሱ መሆኑን የህክምና መረጃዎች ይጠቁማሉ።
​➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖
​🩺 መፍትሄዎች፥

📩​ከጫት ሱስ መውጣት የማይቻል ተራራ አይደለም። ህይወትዎን እና ጤናዎን መልሰው ለመቆጣጠር፦

🟢 ቁርጠኝነት፦ ለማቆም የወሰኑበትን ቀን ይሰይሙ።

🟢 አካባቢን መቀየር፦ ከሚቅሙ ጓደኞች እና ከሚቃምባቸው ቦታዎች ለተወሰነ ጊዜ ይራቁ።

🟢 ውሃና ስፖርት፦ በሰውነትዎ ውስጥ ያሉ ኬሚካሎችን ለማስወገድ በቂ ውሃ ይጠጡ፣ ስፖርትም አእምሮዎ የደስታ ሆርሞን (Endorphins) እንዲያመነጭ ይረዳዋል።

🟢 የባለሙያ እገዛ፦ ጭንቀት ወይም እንቅልፍ ማጣት ካጋጠመዎት ወደ ህክምና ተቋም በመሄድ የምክር አገልግሎት ያግኙ።

​ምንጭ = ዶ/ር ብሩክ ዘነበ (Dr. Biruk Zenebe)
​➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖

09/05/2026

ስለ ተአምረኛው ፌጦ ጥቅሞች በጥቂቱ እናካፍላችሁ
******************************************
ለብዙ ችግሮች ሁነኛ መድሐኒት ስለሆነው ፌጦ እናወራለን፡፡ ስለፌጦ ጥቅም የማያቅ ባይኖርም ሰብሰብ አድርገን ይዘን ቀርበናል፡፡

የፌጦ የጤና ጥቅሞች

ፌጦ (Lapidium sativum) በርካታ በሽታዎችን በመቀነስ ረገድ ትልቅ ድርሻ አለው። በሃበሻ አባባልም "ለሁሉም ፌጦ መድሃኒት ነው" እንል የለ። ለማንኛውም ይህችን ታነቡ ዘንድ ጋበዝን።

1. ለመተንፈሻ አካል ችግር

- ለጉንፋን፣ አስም፣ ሳል፣ ራስ ምታት፣ ለጉሮሮ ቁስል ሁለት ማንኪያ ፌጦ ፈጨት አድርገው ከማር ጋር በመለወስ ይዋጡት፡፡

2. በብረት (iron) ማነስ ምክንያት የሚከሰትን አኒሚያ የተሰኘ በሽታን ለማቃለል።

- ከፍተኛ የብረት ማዕድን የያዘው ፌጦ በአንጀታችን ውስጥ በቀላሉ ስለሚመጠጥ በደም ውስጥ የሚገኘውን የሂሞግሎቢን መጠን ይጨምራል፡፡

3. የቆዳ ችግርን ለማስተካከል

- በፀሐይ የተቃጠለ ቆዳ፣ የተቆጣ ቆዳ፣ ደረቅ ቆዳ ካሎት የተፈጨ ፌጦ ከማር ጋር ቀላቅለው ይቀቡት ችግሩን ለማባረር ይረዳዎታል፡፡

4. ለአንጀትና ለሆድ ዕቃ ሕክምና

- ለተቅማጥ፣ ለሆድ ድርቀት እና ለምግብ ያለመንሸራሸር ወይም የመፈጨት ችግር ሁነኛ መፍትሔ ነው፡፡ በተላይ የፌጦ ፍትፍት ምርጥ ነው፡፡

5. ደም ግፊትን ይቀንሳል፣ የተፈጥሮ የበሽታ የመከላከል አቅምን ያጠናክራል።

- ጠቃሚ የሆኑ የተለያዩ አሲዶችን ማለትም ፋቲ አሲድ፣ አስፓርቲክ አሲድ፣ ግሉታሚክ አሲድ፣ ሊኖሊክ አሲድ፣ ኦሊክ አሲድ፣ ኦሜጋ 3 ፋቲ አሲድ ያሉት በመሆኑ ደም ግፊትን ይቀንሳል፣ የተፈጥሮ የበሽታ የመከላከል አቅምን ያጠናክራል፣ የደም ስኳር መጠንን ይቀንሳል፣ ለአእምሮ እና የልብ ጤናን ከመጠበቅ በተጨማሪ ድባቴንና ጭንቀት አዲዮስ ያሰኛል፡፡

6. በአየርና በኬሚካል ሳቢያ የሚከሰትን የካንሰር ዓይነት ነጥሎ ይዋጋል

- ፀረ-ብግነት እና ቫይታሚን ኢ ስለያዘ በአየርና በኬሚካል ሳቢያ የሚከሰትን የካንሰር ዓይነት ነጥሎ ይዋጋል፡፡ የሕዋሳትን ውድመት በመከላከሉም ያለዕድሜ ማርጀትን ይከላከላል፡፡

7.የወር አበባ አመጣጥን ያስተካክላል

- ፌጦ የወር አበባ አመጣጥን ያስተካክላል፡፡ እንዲሁም ለምታጠባ እናት የጡት ወተቷን ይጨምራል፡፡

8. የፀጉር መነቀልን ይከላከላል

- መጥፎ የሰውነትን ጠረን ከማስወገዱ በተጨማሪ የፀጉር መነቀልን ይከላከላል፡፡

9.የአይን ጤንና ያሻሽላል

ምን ያህል መወሰድ እንዳለበት በሳይንስ የተረጋገጠ ነገር ባይኖርም የመድሐኒት ያህል በትንሹ ብቻ መጠቀም ይመከራል።

Want your public figure to be the top-listed Public Figure in Addis Ababa?
Click here to claim your Sponsored Listing.

Category

Telephone

Website

Address


Gurde Shola
Addis Ababa

Opening Hours

Monday 00:00 - 23:59
Tuesday 00:00 - 23:59
Wednesday 00:00 - 23:59
Thursday 00:00 - 23:59
Friday 00:00 - 23:59
Saturday 00:00 - 23:59
Sunday 00:00 - 23:59