Sheger mereja
16/06/2026
የባሕል ሙዚቃ ድምጻዊው ሰማኸኝ በለው ሥርዓተ ቀብር ተፈጸመ።
***
ድምጻዊ ሰማኸኝ በለው ውልደቱ በ1960 ዓ.ም በባሕር ዳር ከተማ እንደኾነ የሕይወት ታሪኩ ያስረዳል።
አጼ ሠርፀ ድንግል የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርት ቤት እና በፋሲሎ መለስተኛ 2ኛ ደረጃ ትምህርት ተምሯል። የሁለተኛ ደረጃ ትምህርቱን ደግሞ በጣና ሐይቅ 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ተምሯል።
በሙዚቃ ሥራው በግሽ ዓባይ ጀምሮ በ1982 ዓ.ም ወደ አዲስ አበባ በመምጣት በታንጎ ሙዚቃ ቤት እና በኤሌክትራ ሙዚቃ ቤቶች አማካኝነት የሙዚቃ አልበሞችን ሠርቷል።
ከአንቱዬዋ እስከ ባላገሩ ዘፈኖቹ በሕዝብ ዘንድ የሚታወቀው ድምጻዊ ሰማኸኝ በለው በካዛንቺስ የራሱን የባሕል ቤት ከፍቶ እንደነበርም ተነግሯል።
ከሙዚቃ በተጨማሪ በትወናው ሥራ ተሳትፎ የነበረው ድምጻዊው የባላገር ፍቅር፣ አላበድኩም/ ያዥኝ፣ ደቦት እንሥራ፣ ዲስካው፣ አውዳመት፣ አለሽ ነገር እና ዝናቡን የመሳሰሉ ዘፈኖችን ሠርቷል።
ሀገራዊ እና ማኅበራዊ ኀላፊነቶች ላይ ንቁ ተሳታፊ የነበረው የባሕል ድምጻዊው ሰማኸኝ በለው በ58 ዓመቱ ከዚህ ዓለም በሞት ተለይቷል።
ሥርዓተ ቀብሩ ለቤተ ክርስቲያኑ ብዙ አስተዋጽኦ ባበረከተበት እና ቀደም ብሎ ባዘጋጀው የቀብር ቦታ በአዲስ አበባ ቦሌ ቡልቡላ መድኃኔዓለም ቤተክርስቲያን ወዳጆቹ፣ የሙያ አጋሮቹ እና ቤተሰቦቹ በተገኙበት ተፈጽሟል።
የአርቲስቱ የመታሰቢያ ፕሮግራምም የፌደራል እና የአዲስ አበባ ከተማ የባሕል፣ ስፖርት እና ኪነ-ጥበብ ተቋማት ኀላፊዎች ጋር በመነጋገር ይዘጋጃል ተብሏል።
13/06/2026
✨ ቅዴዎቼ እንዴት አደራችሁ✨
🌞☕️😁ተ.ሰ.ብ.ሰ.ቡ!!!🌞☕️😁
🤔"ሰው ሁሉም እያለው ምንም እንደሌለው ባክኖ የሚቀረው ትኩረት ሲያጣ ነው።"
✍️ እራስህን ሰብስብ፤ ትኩረትህ ላይ አተኩር፤ ትክክለኛውን፣ አስፈላጊውንና ወሳኙን ነገር ያለ እረፍት ፈልግ። ትኩረትህን የትም እየጣልክ፣ በተባለው ሁሉ እየደነገጥክ፣ ላየኸው ሁሉ አስተያየት እየሰጠህ፣ በማያገባህ ሁሉ ጣልቃ እየገባህ መባከንህን አቁም።
💫💫
አዎ! በመሩት መመራት ብርቅ አይደለም ይልቅ ብርቁ መምራት ነው፤ በተከፈተ በር መግባት አዲስ አይደለም ይልቅ አዲሱ በር እየከፈቱ ማስገባት ነው፤ አድናቂና ደጋፊ መሆን ብዙ ጥረት የሚፈልግ አይደለም ይልቅ ዋናው ጥረትና ትጋትን የሚፈልገው ተደናቂና ተወዳጅ መሆኑ ነው። ይህን አለኝ ያንን የለኝም ማለቱን አቁምና ባለህ ነገር ፍሬ ማፍራት ጀምር። ማንም ሲነዳህ እየተነዳህ፣ ማንም አውቅልሃለሁ ባይ ሁሉ የነገረህን ትርክት እያመንክ፣ አንዱ ከመሬት ተነስቶ ሌላውን የሚያጠለሽና የሚያጥላላ ነገር ሲያነሳ እያዳመጥክ፣ ትኩረትህን እዚህም እዛም እየበተንክ፣ ለደቂቃዎች እራስን ሰብስቦ፣ ውስጥን አረጋግቶ መኖር እያቃተህ የተለየ ነገር በህይወቴ ይከሰታል ብለህ እንዳትጠብቅ።
አዎ! ጀግናዬ..! ተሰብሰብ፤ እራስህን ሰብስብ፤ ትኩረትህ ላይ አተኩር፤ ትክክለኛውን፣ አስፈላጊውንና ዋሳኙን ነገር ያለእረፍት ፈልግ። ትኩረትህን የትም እየጣልክ፣ በተባለው ሁሉ እየደነገጥክ፣ ላየሀው ሁሉ አስተያየት እየሰጠህ፣ በማያገባህ ሁሉ ጣልቃ እየገባህ መባከንህን አቁም። ምርታማነትህ (productivity) የሚያሳስብህ ከሆነ ትኩረትህን አጥብቀህ ጠብቀው፤ የእውነት በህይወትህ ላይ ተጨባጭ ነገር ማምጣት የምትፈልግ ከሆነ ብክነትህን ቀንስ፣ እራስህን ወደ አንድ አቅጣጫ ሰብስበው፣ ሃሳብህን ፈር አስይዘው፣ ለእንቅስቃሴህ ትርጉም ፈልግለት። ቀላል ህይወት በምኞት ሳይሆን በከባድ ልፋትና ጥረት የሚመጣ ነው። ገና ከጅምሩ የትኩረት አቅጣጫውን በሚገባ ያልተረዳ ሰው ስለህይወቱ ቅለትና ክብደት ከመጨነቁ በፊት የትኩረቱን አቅጣጫ ማስተካከል ይኖርበታል።
አዎ! እስከመቼ በተበታተነ ሃሳብ፣ በተበታተነ መርህ ህይወትህን እንደምትመራ እራስህን ጠይቅ። እውቀቱ፣ ጥበቡ፣ ማስተዋሉ እያለህ ስለምን ከውጤት ጎዳና እንደራክ፣ ስለምንስ ህይወትህን በአግባቡ መምራት እንደተሳነህ እራስህን መርምር። እንደምትችል ማንም ያውቃል፣ ጉብዝናህን ማንም ይመሰክራል፣ ብዙ ችሎታ እንዳለህ ማንም ይናገራል፣ ነገር ግን በችሎታህና በጉብዝናህ ምንም የተለየ ውጤት ስታመጣ አትታይም። ትኩረትህን መሰብሰብ ባለመቻልህ ብቻ ሙሉ ህይወትህን እያባከንክ እንደሆነ አስተውል። ሁሉ ነገር እያለህ ምንም እንደሌለው ምስኪን ሰው መኖር ይብቃህ። ያለህን ሁሉ በትኩረት አሟጠህ ተጠቀመው፣ በስጦታህ ማሾፍ አቁምና አይንህን ወደ ጥራትና ውጤታማት አዙር። ትኩረትህን ሰብስብ፣ ስጦታህን ተጠቀም፣ የህይወት ደረጃህንም ከፍ አድርግ።
ምርጥ ጽሁፍ✍️
*
ቅዴዎቼ ተ.ሰ.ብ.ሰ.ቡ!!!🌞!!! ሰናይ ቅዴ፡፡🌞
ሰኔ 06 ቀን 2018 ዓ/ም
*
11/06/2026
ዛሬ የሚጀምረው ተናፋቂው የዓለም ዋንጫ‼
***
በመላው ዓለም በጉጉት የሚጠበቀውና ከምድር ታላላቅ የስፖርት ሁነቶች አንዱ የሆነው የዓለም ዋንጫ ዛሬ በይፋ ይጀምራል።
ይህ ታላቅ መድረክ ልዩ ልዩ ሀገራትን፣ ባህሎችንና በቢሊዮን የሚቆጠሩ የእግር ኳስ አፍቃሪያንን በአንድነት የሚያስተሳስር ልዩ የደስታ በዓል ነው።
በውድድሩ ታሪክ ለመጀመሪያ ጊዜ ሦስት ሀገራት — አሜሪካ፣ ካናዳ እና ሜክሲኮ በጋራ ይህንን ውድድር ያስተናግዳሉ።
ይህ ታሪካዊ እትም፣ የእግር ኳስን ዓለም አቀፋዊ ዕድገትና ሰዎችን የማስተሳሰር አስደናቂ ኃይል የሚያሳይ፣ በታሪክ እጅግ ግዙፍ እና ታላቅ ዓላማ ያነገበ የዓለም ዋንጫ እንደሚሆን ይጠበቃል።
ከቦነስ አይረስ ጎዳናዎች እስከ አዲስ አበባ መንደሮች፣ ከአውሮፓ ከተሞች እስከ አፍሪካና እስያ ገጠራማ አካባቢዎች፣ የመላው ዓለም እግር ኳስ አፍቃሪያን ዓይኖች አሁን ወደ አንዱ ታላቅ መድረክ አቅንተዋል።
ለሚቀጥሉት ሳምንታት፣ ሀገራት ለላቀው የእግር ኳስ ክብር በሚያደርጉት ፍልሚያ፣ መላው ዓለም በጋራ ይደሰታል፣ አብሮ ይጨነቃል፣ እንዲሁም አብሮ ያልማል።
የዓለም ዋንጫ ከእግር ኳስ ውድድር በላይ ነው፤ ጀግኖች የሚወለዱበት፣ ክብረ ወሰኖች የሚሰበሩበት እና ታሪክ የሚጻፍበት መድረክ ነው።
ውድድሩ ሲጀመር በቢሊዮን የሚቆጠሩ አድናቂዎች የሚጠይቁት አንድ ጥያቄ አለ፦
🏆 የዘንድሮውን የዓለም ዋንጫ ማን ያነሳ ይሆን?
Click here to claim your Sponsored Listing.
Category
Contact the public figure
Telephone
Website
Address
Addis Ababa