Muroed-QR

Muroed-QR

Share

Photos from Muroed-QR's post 29/07/2022

ገዳዮቻችን ግን ሽንፈታቸውን ሲያስታውሱባት ይኖራሉ!

[ ብጹዕ አባታችን አቡነ ናትናኤል ያስተላለፉት መልዕክት]

| ሰማዕተ ጽድቅ ብፁዕ አቡነ ጴጥሮስ ዘር ቀለም ሃይማኖት ሳይለየን ለኢትዮጵያውያን ሁሉ የመንፈስም የሥነ ልቡናም አሸናፊነት ተምሳሌት ናቸው

እንኳን ለ ብጹዕ አብነ ጴጥሮስ ሰማዕት ለተቀበሉበት መታሰብያ አደረሰን አደረሳቹ

በቅድሚያ የአሸናፊነት ሥነ ልቡናን ተላብሰን አሸናፊውን ሰማዕተ ጽድቅ ብፁዕ አቡነ ጴጥሮስን ለምናስብበት ለዚህ ዕለት ያደረሰን አምላካችን ይክበር ይመስገን።

ሰማዕተ ጽድቅ ብፁዕ አቡነ ጴጥሮስ ዘር ቀለም ሃይማኖት ሳይለየን ለኢትዮጵያውያን ሁሉ የመንፈስም የሥነ ልቡናም አሸናፊነት ተምሳሌት ናቸው።

እኛ ይህቺን ዕለት ሞተንም በማሸነፋችን ስናስታውሳት ገዳዮቻችን ግን ሽንፈታቸውን ሲያስታውሱባት ይኖራሉ።

ብፁዕነታቸው ለጠላት ቢንበረከኩ ኖሮ ዛሬ እኛ ልጆቻቸው እንዲህ ቀና ብለን የጀግና አካሄድ ባልሄድን ነበር። ለአሸናፊዎች ይዘመራል እንጂ ስለማይለቀስ በሳቸው ሞት እኛ እንዘምራለን እንጂ አናለቅስም።

ይሁን እንጂ ዛሬ የኋልዮሽ የምንሄድ በሚመስል መልኩ እሳቸው በጠላት ጥይት ተደብድበው ቀና ያደረጉትን አንገታችንን እኛ እርበርስ በመደባደብ ስናጎነብስ እንደማየት ምን የሚያሳፍር ነገር አለ? ውድ ወገኖቼ ብፁዕነታቸውን ባሰብን ቁጥር ከሳቸው የምንማረው የሃይማናት፣ የሀገርንና የወገንን ፍቅር ነው ።

ስለሆነም በጥላቻ ወደኋላ ከመመለስ ይልቅ ብፁዕነታቸው እንደ አምላካቸው በደም ዋጋ ያወረሱንን ፍቅር ይዘን ወደፊት እንድንራመድ አምላከ ጴጥሮስ ይርዳን። የሞቱ ወገኖቻችንን ነፍስ ይማር የብፁዕነታቸው በረከት በሁላችንም ላይ ይደር አሜን።

ብጹዕ አብነ ናትናኤል
የምዕራብ ሸ የምሥራቅ ወለጋና የሆሮ ጉድሩ አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ

27/07/2022

ከቅዱስ አባቴ ጎን ነኝ!!! እናንተስ?💚💛❤😘😍

ለዻዻሳችሁ፣ ለቅዱስ አባታችሁ፣ ያላችሁን ድጋፍ አሳዩና ጠላት ይደንግጥ እስቲ! ከፊታቸው ቅዱስ መንፈስ፣ ከጀርባቸው 80 ሚሊየን ልጆቻቸው አለንላቸው!በውሸት ለተፈበረከ ቅራቅንቦ ጆሮ አንሰጥም!

ሚዲያ ኃይል አለው ባለማዕተቦች፣ ታዘዙ!

24/07/2022

ቅድስት አርሴማ በዓለም አደባባይ !

አርሴማን በአንገት በልቧ ይዛ በዓለም አደባባይ በ5000 M የተወዳደረችው ጉዳፍ ጸጋዬ ወርቅ ለኢትዮጵያ አስመዝግባለች።

Photos from Muroed-QR's post 23/07/2022

በስልጤ ዞን በአክራሪ ሙስሊሞች ከተቃጠሉ አብያተክርስቲያናት መሐከል አንዱ የሆነው..........

የፃዲቁ አባታችን ገብር ክርስቶስ ቤተክርስትያን ህንፃ መቅደስ የግንባታ ጽዳት ሥራ ተጀምሯል።

እግዚአብሔር ይመስገን!

Want your place of worship to be the top-listed Place Of Worship in Addis Ababa?
Click here to claim your Sponsored Listing.

Address


Addis Ababa