Alie Assefa
08/03/2026
Get ready for the Revelation of Jesus Christ the King and His Eternal Kingdom. ከ ዓመተ-ምኅረት ወደ ሰዐተ-ፍርድ ከዛም ወደ ሺሁ ዓመት የክርስቶስ መንግስት ከዛም ወደ ነጩ ዙፋን ቅጽበተ ፍርድ በመጨረሻም ወደ አዲሲቱ ኢየሩሳሌም=የአዲሱ ሰማይና የአዲሷ ምድር ዋና ከተማ። ሁሉም በየተራው እንዲሁ ነው። አዎ! ሰማይና ምድር ያልፋል፤ የእግዚአብሔር ቃል ግን ለዘለዓለም ጸንቶ ይኖራል።
TikTok · WordSword 23.1K likes, 3858 comments. “The Moment John Survived Boiling Oil, Rome Realized Who Was Really in Control.”
11/09/2024
የኢየሱስ ክርስቶስን መምጣት በተስፋ እና በናፍቆት ነቅተን እየተጠባበቅን የምንኖርበት አዲስ ዓመት ይሁንልን። አዲሱን ዓመት የመንፈስ ቅባት ዘይታችን ሳያልቅብን፣ ብርሐናችን በዓለም ሁሉ እየበራ፣ በማስተዋል፣ በእውቀት፣ በጥበብና በእውነት ጀምረን የምንዘልቀው ያድርግልን።
በሥጋ መሠረት አንታለልምና
************************
የመጨረሻው መጨረሻ ተፈጽሞ ነቅተውና ተዘጋጅተው ለሚጠባበቁት መልካሙን የኢየሱስን ዳግም መምጣት የምናይበት ዘመን በደጅ ነው። ከማይረባውና ከምናምንቴው ዓለማዊ ወሥጋዊ ሕይወት ዘወር ብለን ጌታን በንቃትና በትጋት ተዘጋጅተን እንጠብቅ። ስለ ዓለማዊ ምናምንቴ ሥርዓቶችና ጉዳዮች መጨነቅ ጣኦትን ከማምለክ ክፋት አይተናነስም፤ ስለ ሥጋ ማሰብም ሞት ነው። በሥጋ መሠረት ልንታለል አይገባንም።
1ኛ ተሰሎንቄ 1
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
⁵ ወንጌላችን በኃይልና በመንፈስ ቅዱስ በብዙ መረዳትም እንጂ በቃል ብቻ ወደ እናንተ አልመጣምና፤ በእናንተ ዘንድ ስለ እናንተ እንዴት እንደ ነበርን ታውቃላችሁ።
⁶ ደግሞ እናንተ ቃሉን በብዙ መከራ ከመንፈስ ቅዱስ ደስታ ጋር ተቀብላችሁ፥ እኛንና ጌታን የምትመስሉ ሆናችሁ፤
⁷ ስለዚህም በመቄዶንያና በአካይያ ላሉት ምእመናን ሁሉ ምሳሌ ሆናችሁላቸው።
⁸ ከእናንተ ወጥቶ የጌታ ቃል በመቄዶንያና በአካይያ ብቻ አልተሰማምና፥ ነገር ግን ምንም እንድንናገር እስከማያስፈልግ ድረስ፥ በእግዚአብሔር ዘንድ የሚሆን እምነታችሁ በሁሉ ስፍራ ተወርቶአል።
⁹-¹⁰ እነርሱ ራሳቸው ወደ እናንተ መግባታችን እንዴት እንደነበረ ስለ እኛ ይናገራሉና፤ ለሕያውና ለእውነተኛ አምላክም ታገለግሉ ዘንድ፥ ከሙታንም ያስነሳውን ልጁን እርሱንም ኢየሱስን ከሚመጣው ቍጣ የሚያድነንን ከሰማይ ትጠብቁ ዘንድ፥ ከጣዖቶች ወደ እግዚአብሔር እንዴት ዘወር እንዳላችሁ ይናገራሉ።
መዳን ሁለመናዊ ነው፦ መንፈሳችን፣ ነፍሳችንና ሥጋችን ማለትም ሁለመናችን ሲድን እንዲህ ነው፦
፩. “ስለዚህ ማንም በክርስቶስ ቢሆን አዲስ ፍጥረት ነው፤ አሮጌው ነገር አልፎአል፤ እነሆ፥ ሁሉም አዲስ ሆኖአል።”
— 2ኛ ቆሮ 5፥17....መንፈሳችን ሲድን/ዳግም መወለድ፣
፪. “የእግዚአብሔር ፈቃድ እርሱም በጎና ደስ የሚያሰኝ ፍጹምም የሆነው ነገር ምን እንደ ሆነ ፈትናችሁ ታውቁ ዘንድ በልባችሁ መታደስ ተለወጡ እንጂ ይህን ዓለም አትምሰሉ።”
— ሮሜ 12፥2. በልብ/በአእምሮ/በነፍስ ዕለት በዕለት በእግዚአብሔር ቃል መታደስ/ መለወጥ...የነፍሳችን መዳን፣
፫. “እርሱም ሁሉን እንኳ ለራሱ ሊያስገዛ እንደሚችልበት አሠራር፥ ክቡር ሥጋውን እንዲመስል የተዋረደውን ሥጋችንን ይለውጣል።”
— ፊልጵስዩስ 3፥21. ክርስቶስ ዳግም ሲመጣ ደግሞ ሥጋችን ይከብራል።
በዚህም ሁለመናዊ መዳናችን እርግጥ ይሆናል።
በአንዱና በብቸኛው መንገድ፣ በአንዱና በብቸኛው እውነት፣ በአንዱና ብቸኛው ሕይወት፣ በኢየሱስ ክርስቶስ እንመላለስ። ሁለተኛውንና የመጨረሻውን መለከት ለመስማት ጆሯችንን አንቅተን በእሱ ብቻ እንኑር። መለከቱን ለመስማትና ለመነጠቅ የሚጠባበቁትን ለተወሰነው ጊዜ በአባቱ ቤት የደስታ መኖሪያን ቤት አዘጋጅቷልናል። ኖህንና አብረውት የነበሩትን፣ ሎጥንና ቤተሰቡን ያስመለጠው እሱ እኛንም በምድር ሊሆን ካለው እጅግ ከባድ መከራና ጥፋት አስመልጦ በአባቱ ቤት ባዘጋጀልን የበጉ ሰርግ ድግስ ሊወስደን ቀኑ እጅግ ቀርቧል፤ ጥሪው በደጅ ነውና ነቅተን እንጠባበቅ።
ማራናታ። ጌታ ሆይ ቶሎና።
ዮሐንስ 14
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
¹ ልባችሁ አይታወክ፤ በእግዚአብሔር እመኑ፥ በእኔም ደግሞ እመኑ።
² በአባቴ ቤት ብዙ መኖሪያ አለ፤ እንዲህስ ባይሆን ባልኋችሁ ነበር፤ ስፍራ አዘጋጅላችሁ ዘንድ እሄዳለሁና፤
³ ሄጄም ስፍራ ባዘጋጅላችሁ፥ እኔ ባለሁበት እናንተ ደግሞ እንድትሆኑ ሁለተኛ እመጣለሁ ወደ እኔም እወስዳችኋለሁ።
⁴ ወደምሄድበትም ታውቃላችሁ፥ መንገዱንም ታውቃላችሁ።
⁵ ቶማስም፦ ጌታ ሆይ፥ ወደምትሄድበት አናውቅም፤ እንዴትስ መንገዱን እናውቃለን? አለው።
⁶ ኢየሱስም፦ እኔ መንገድና እውነት ሕይወትም ነኝ፤ በእኔ በቀር ወደ አብ የሚመጣ የለም።
“ከዚያ በኋላም አየሁ፥ እነሆም በሰማይ የተከፈተ ደጅ፥ እንደ መለከትም ሆኖ ሲናገረኝ የሰማሁት ፊተኛው ድምፅ፦ ወደዚህ ውጣና ከዚህ በኋላ ሊሆን የሚያስፈልገውን ነገር አሳይሃለሁ አለ።”
— ራእይ 4፥1
Click here to claim your Sponsored Listing.
Category
Contact the school
Telephone
Website
Address
Addis Ababa
251