John Tube
26/08/2024
[ፍቅር ተወደደ] የሚለው የኃይለእየሱስ ፈይሳ ዘፈን ላይ ያለች አንዲት ሀረግ ነገር ብክንክን አድርጋ ታስቀኛለች።
"የቆላውም መጥቶ እምዬ ይላታል"
የቆላው😓
13/06/2020
┉✽̶»̶̥🌺 #የማይሽር ጠባሳ🌺̶̥✽̶┉
❣:¨·.·¨: ❣
══════❁✿❁ ══════
🌺🌺ክፍል 2
እውነተኛ ታሪክ የምጠቀመው ስም የታሪኩ ባለቤቶች እንዳልሆኑ ልገልፅ እወዳለው
አዲስ አበባ ደረስን ግን የህይወቴ የመጀመርያው ስቃይ እዚህ ጀመር
አዎ ገና ልጅነቴን ሳልጨርስ ጠግቤ ሳልጫወት በእናት እቅፍ ውስጥ እንደ ልጅ ሳልተኛ በልጅነቴ በጨቅላነቴ ገላ የቤት ውስጥ ስራ መስራት ጀመርኩ
አስተምራታለው እኔ እንደ ልጆቼ አድርጌ አሳድጋታለው ብላ ያዘነች መስላ ከወንድሜ የነጠለችኝ አውሬ የስቃይ በር ከፋቼ ነበረች
ትምህርቱ ቀርቶ ምግብ በአግባቡ አሰጠኝም ከልጆችዋ ትራፊ እንዲሁም አጋጣሚ እንግዳ ከመጣ ያ ትራፊ ነበር እንደ ውሻ የኔ ቀለብ
እሱንም ተመስገን ብዬ እመገብ ነበር
መቼም እራብ ድንጋይስ ያስበላ የለ እኔም ያገኘውትን የተሰጠኝን እመገባለው
ከዚህ ባሻገር ግን ያለ አቅሜ ከምሰራው ስራ ባሻገር ድብደባው ከእለት ወደ እለት ይበረታብኝ ነበር
በበአላት ወቅት ለልጆችዋ ልብስ ሲገዛ ለኔ ግን አደለም ልብስ ምግብ እንኳን አላገኝም ነበር አንዳንዴ እንደ ውሻ እቃ ቤት ሁላ ይቆለፍብኛል
ፈጣሪ ሆይ እኔ ጨቅላ ልጅህን አስበኝ እላለው የምጣራው ማንም ስላልነበረኝ
ይህ ስቃይ በረታ የሚያዩ የጎረቤት ሰዎች አንዳንዴ እስዋ በሌለችበት ምግብ ደብቀው ይሰጡኝ ነበር
አዎ ሳይኖራት ቢሆን ማንም ባላዘነባት ነገር ግን ቤትዋ ሙሉ ከመሆኑ ባለፈ ለማንም ይተርፍ ነበር
ይህ ስቃይ የዱላው የእራቡ ከጊዜ ወደ ጊዜ አቅም እያሳጣኝ መጣ
አስታውሳለው አንድ ወቅት በአል ነበር እንደ ተለመደው ምግብ ሰራርታ እኔም ያቅሜን አግዤ ሳበቃ በጣም እራበኝ እስከ ዛሬ ስኖር አንድም ቀን እራበኝ ስጪኝ የሚል ቃል ወቶኝ አያውቅም ነበር ዛሬ ግን አፍ አውጥቼ እራበኝ እባክሽ ምግብ ስጭኝ አልኳት
እስዋ ግን ከለከለችኝ እኔም ከምሞት ብዬ አጠገቤ ያገኘውትን የቡና አሻራ በውሀ በጥብጬ ጭልጥ አድርጌ ጠጣው እራቤንም አስታገስኩ ውስጤ ግን ጥላቻ በእስዋ ላይ አሳደረ
እንዲ እያልኩ 2 አመታት በስቃይ አለፈ
ታድያ አንድ ቀን ዘመድ የሆነችው ሰብለ ሁሌም ስቃዬን ታይ ስለነበር እሷ በሌለችበት መጣች
ቅድስቴ ነይ አንድ ድርጅት አለ ያስተምራሉ እዛም ትቀመጫለሽ የዚህ ቤት ስቃይ ያበቃል ብላ አዛኝ መስላ አታላ አሳልፋ ለሌሎች ሰዎች ሸጠችኝ
ምን አደረኩ በልጅነቴ በየትኛው ሀጥያቴ ነው ምቀጣው
አሁን የተሸጥኩበት ቤት 1 ልጅ ያላት ሴት ነበረች በርግጥ ትምህርቴን ብታስተምረኝም ምግብ ብበላም ግን ሰይጣናዊ ባህሪ ስለነበራት ያለ ምክንያት ትደበድበኝ ነበር
አዎ የሰው ልጅ አደለም ገና በጨቅላነቱ ይቅርና ቢያረጅም በፍቅር ሊያዝ ይገባዋል ማንም ይውለደው ማንም ሁሉም የፈጣሪ ፍጡር ስለሆነ ሊከበር ይገባው ነበር
ይህ ግን ለኔ ህልም ቅዥት እንጂ በእውን የማይሆን ነገር ነው
ትምህርቴን የቀን እየተማርኩ እንደ አቅሜ የቤት ውስጥ ስራ እየሰራው ጎን ለጎን ደግሞ ከ አቅሜ በላይ የሆነ ዱላ እርግጫ እየቻልኩ ኑሮዬን መግፋት ጀመርኩ
ልጅነቴ በአንድ በኩል የሰው ፍቅር ሲሰጠኝ በሌላ በኩል ደግሞ በአስሪዎቼ መጥፎ ነገር ነበር
ሳስበው ዛሬ ላይ አንዳንዴ ቢያስቀኝም ይበልጡኑ ግን አዝናለው
አንድ ወቅት እቺ አሰርዬ እርጉዝ ነበረች እና እኔን ለመምታት ዱላ ይዛ ሰፈር ለሰፈር ታባረኛለች ነገር ግን ሰዎች እርግዝናዋ ከወደቀች መጥፎ እንደሆን እየጮሁ ቁሚ ቁሚ አታስሩጫት ይሉኝ ነበር እኔም ዱላው ላይቀር ለምን እሷስ ትጎዳ ብዬ ቆሜ እመታ ነበር
ነገር ግን አንድ ወቅት ላይ ግን ከትምህርት ቤት መጥቼ ዩንፎርሜን ሳላወልቅ ገና ከበር አውሬ ሆና ጠበቀ
10/05/2020
Mari Tija:
....
ፀሀይዋን ተመልከታት አታምርም ? ጨረቃዋስ ከዋክብቱስ ዛፎቹ ወንዙና ተራራውስ አያምሩም ? ያምራሉ ። እኚ ሁሉ ግን ያልፉሉ አንተ ግን በሞት ከዚህ አለም ብትለይ እንኳን በሰማይ ለዘላለም ትኖራለህ ። ፈጣሪ ፍጥረታትንን ሁሉ በቃሉ በመናገር እና በሀሳብ (በሀልዮ) ሲፈጥር አንተን ግን በእጁ አሽሞንሙኖ ፈጥሮሀል። አንተ ማለት ክርስቶስ እነሆ በደጅ ቆሜ አንኳኳለው ማንም ሚከፍትልኝ ቢኖር ገብቼ እራቴን ከእርሱ ጋር እበላለው ብሎ የተናገረልህ ። ፈጣሪ አለምን ከፈጠረበት ጥበብ ይልቅ አለምን ያዳነበት ጥበቡ ይበልጣል ተብሎ የተነገረልህ ዋጋ የከፈለልህ የመንግስቱ ወራሽ ውድ ልጁ ነህ።
ምን አልባት ዛሬ በተለያየ ሱስ ተይዘህ ይሆናል ምን አልባት ስራ በማጣት ፍቅረኛ በማጣት ትሰቃይ ይሆናል ።ምን አልባት ቤተሰብህ ወገንህ ተስፉ ቆርጦብህ ይሆናል ። ምን አልባት ሞትህን እየተመኘህ ይሆናል። ግን አይዞህ ፈጣሪ በአንተ የጀመረውን ስራ ሳይጨርስ አትሞትም። Never Give Up በቀላሉ ተስፉ አትቁረጥ ። ተመልከት ሰይጣን ተስፉ የለውም ግን ተስፉ አይቆርጥም ። ሰው ግን ተስፉ አለው ግን ተስፉ ይቆርጣል። 1 አምፖል ሽቦው ከረገፈ አያበራም ጠርሙስ ይሆናል ። የሰውም የብርሃን ሽቦው ተስፉ ነው ። ሰው ተስፉ ቢቆርጥብህ እራስህም ተስፉ ብትቆርጥ የፈጠረህ በአንተ ላይ ተስፉ አይቆርጥብህምና አይዞህ ። 1 ጠጠር አንስተህ ተራራ ላይ ብትወረውር ተራራው ምንም አይሆንም ጠጠሩ ተንከባሎ እግሩ ስር ይሆናል ። ያን ጠጠር አንስተህ መስታወት ላይ ብትወረውረው ግን መስታወቱ ይሰባበራል። ጠጠሩን በችግር እንመስለውና ችግር ወዳንተ ሲመጣ እንደ መስታወቱ አትሰባበር እንደ ተራራው በቁጥጥር ስር አውለው ። 1 የተለኮሰ የክብሪት እንጨት ጭድ ላይ ብትጥለው ይቀጣጠላል ። ውሀ ላይ ብትጥለው ግን ውሀው ያጠፉዋል ። የሚያቃጥሉ ነገሮች በህይወትህ ውስጥ ሲከሰቱ እንደ ጭድ አትቀጣጠል እንደ ውሃው አጥፉቸው ። 1 በረዶ ፀሀይ ላይ ብታረገው ይቀልጣል የተቦካ ሲሚንቶ ፀሀይ ላይ ብታረግ ግን ይጠነክራል። እንደ ፀሀይ የከረሩ ችግሮች በህይወትህ ሲያጋጥሙህ እንደ በረዶ አትቅለጥ እንደ ሲሚንቶው ጠንክርባቸው። እህቴ ምን አልባት ለስራ ጉዳይ በተለያየ ሀገር ውስጥ ሆነሽ ይሆናል ያለሽው ።መፈጠርሽ ሴትነትሽም አስጠልቶሽ ይሆናል። ግን ክርስቶስ ወደ አለም ሲመጣ ምድራዊ እናት እንጂ አባት አላስፈለገውም የሴት ልጅ ተብሎ እስኪጠራ ድረስ ማርያም ብቻዋን ነው ያሳደገችው። በኛ ቤተክርስቲያን ህንፃ ቤተክርስቲያኑ ተሰርቶ አለቀ የሚባለው ጉልላቱ ተሰርቶ ሲያልቅ ነው ። ፈጣሪም ፍጥረትን ሁሉ ፈጥሮ ሲጨርስ አዳምን ፈጠረ በመጨረሻም ከጎኑ ሄዋንን ወይም አንቺን የስነ ፍጥረት ጉልላት አርጎ ፈጠረሽ። ስለዚህ እህቴ ክብርት ፍጥረት ነሽና ደስ ይበልሽ።
ስላም እግዚአብሔር በያለንበት ይብዛልን።
መልካም ምሽት ይሁንላችሁ✝
&
22/03/2020
Rip Italy 😨😷
Click here to claim your Sponsored Listing.
Category
Contact the university
Telephone
Website
Address
Addis Ababa