ECNTV
07/02/2026
ማስተር አብነት ከበደ እንኳን ለሀገርህ አበቃህ!❤️🙏
ኢትዮጵያውያን የምስራች! የሁላችንም ወንድም ደጎ ማስተር አብነት ከበደ በሰላም ሀገሩ ገብቷል ። ለኢትዮጵያውያን በሙሉ እንኳን ደስ አላችሁ።
በታይላንድ ባንኮክ የህክምና ክትትሉን ሲያደርግ የቆየው ተወዳጁ ወንድማችን ደጉ ሰዉ ማስተር አብነት ከበደ ህክምናውን በድል አጠናቆ ዛሬ ጥር 30/2018 ዓ.ም.አዲስ አበባ ገብቷል።
አሁን ላይ ሙሉ ጤንነት እንደሚሰማው ገልጿል። "የደጋግ ኢትዮጵያውያን ጸሎት ለሀገሬ አብቅቶኛል" በማለት ለጸለያችሁለትና ከጎኑ ለቆማችሁ ሁሉ ልባዊ ምስጋናውን አቅርቧል።
ፈጣሪ አምላክ ለተደረገለት መልካም ነገር ሁሉ ክብር ይግባው ። ፈጣሪ ጨርሶ ይማርህ ወንድማችን !!❤️🙏❤️
07/02/2026
በ1.2 ቢሊየን ብር የተገነባውና በ32 ታዋቂ ባለሙያዎች የተመሰረተው "ዶክተርስ አሊያንስ አጠቃላይ ሆስፒታል" በዛሬው ዕለት ተመረቀ
በኢትዮጵያ የጤናውን ዘርፍ አንድ ደረጃ ከፍ ለማድረግና ጥራት ያለው የሕክምና አገልግሎት ለማቅረብ በከፍተኛ መዋዕለ ንዋይ የተገነባው ዶክተርስ አሊያንስ አጠቃላይ ሆስፒታል የምርቃ ስነ-ስርዓቱን በዛሬው ዕለት በደመቀ ሁኔታ አካሂዷል።
ተቋሙን ልዩ የሚያደርጉት ዋና ዋና ነጥቦች፡
💰 የመዋዕለ ንዋይ አቅም፦ ሆስፒታሉ በ 1.2 ቢሊየን ብር ካፒታል የተቋቋመ ሲሆን፣ ይህም መስራቾቹ ትልቅ ሕልምን ሰንቀው ወደ ተግባር መግባታቸውን ያሳያል።
👨⚕️ የባለሙያዎች ጥርቅም፦ ከ25 ዓመታት በላይ የካበተ ልምድ ባላቸው ከ 32 በላይ ሰብ-ስፔሻሊስት ሐኪሞች የተመሰረተ ነው።
ይህም ታካሚዎች ዓለም አቀፍ ደረጃውን የጠበቀ የሕክምና ምክርና ክትትል በሀገራቸው እንዲያገኙ ያስችላቸዋል።
🏥 የመኝታና የመሠረተ ልማት አቅም፦
ከ 100 በላይ የተኝቶ ማከሚያ አልጋዎች።
በዘመናዊ መሣሪያዎች የተደራጁ 5 የቀዶ ጥገና ክፍሎች።
የ24 ሰዓት የድንገተኛ ክፍልና የፅኑ ሕሙማን (ICU) ሕክምና።
💼 የሥራ ዕድል ፈጠራ፦ በአሁኑ ወቅት ከ120 በላይ ሠራተኞችን የያዘ ሲሆን፣ በሙሉ አቅሙ ሥራ ሲጀምር ከ 300 በላይ ለሚሆኑ ዜጎች የሥራ ዕድል ለመፍጠር አቅዷል።
ምን ምን አገልግሎቶች ይሰጣሉ?
ሆስፒታሉ ሁሉንም አገልግሎቶች በአንድ ጣራ ሥር በጥራትና በተመጣጣኝ ዋጋ ያቀርባል። ከእነዚህም መካከል፦
👉የእናቶችና ሕፃናት ሕክምና
👉የልብ፣ የኩላሊትና የስኳር ሕመም ክትትል
👉አጠቃላይና የውስጥ ደዌ ቀዶ ጥገናዎች
ተላላፊ ያልሆኑ በሽታዎች ሕክምና
🌍 የሕክምና ቱሪዝምና የወደፊት ዕቅድ፦
ቀደም ሲል ዜጎች ለከፍተኛ ሕክምና ወደ ውጭ አገር የሚጓዙበትን ወጪና እንግልት ለማስቀረት ሆስፒታሉ ትልቅ ግብ ሰንቋል። በተጨማሪም ከአጎራባች አገራት ታካሚዎችን በመቀበል የሆስፒታል ቱሪዝምን (Medical Tourism) የማሳደግና የውጭ ምንዛሬን የማዳን ዕቅድ ይዟል።
📍 አድራሻ፦ አዲስ አበባ፣ ራስ ደስታ አካባቢ፣ ከአርበኞች ትምህርት ቤት ጎን፣ ሰናይ ሕንፃ ላይ።
ሆስፒታሉ ከጥር 1 ጀምሮ አገልግሎት መስጠት የጀመረ ሲሆን፣ ዛሬ በተደረገው የምርቃ ስነ-ስርዓት ላይ የጤና ሚኒስቴርና የአዲስ አበባ ጤና ቢሮ ከፍተኛ ኃላፊዎች፣ ስፔሻሊስት ሐኪሞችና የማህበረሰብ ተወካዮች ተገኝተዋል።
05/02/2026
ዓለም አቀፍ የሲያናይድ ማኔጅመንት ጉባዔ በአዲስ አበባ ሸራተን አዲስ ኤሌግዠሪ ኮሌክሽን ሆቴል እየተካሄደ ነው፡፡
የማዕድን ሚኒስትሩ ሀብታሙ ተገኘ (ኢ/ር) የዓለም አቀፍ የሲያናይድ ማኔጅመንት ፕሬዚዳንት ፖል በትማንና የሚድሮክ ኢንቨስትመንት ግሩፕ ቺፍ ኦፕሬሽን ኦፊሰር አቶ አበበ ተክሉ ተግኝተዋል።
በጉባዔዉ ላይ ከ14 የተለያዩ የዓለም ሀገራት የተወጣጡ አካላትከወርቅ ማዕድን ስራ ጋር ግንኙነት ያላቸው አለም አቀፍ ኩባንያዎች፣ ወርቅ አምራቾችና ሲያናይድ ትራንስፖርት ዘርፍ ላይ የተሰማሩ አምራቾች እና ሌሎች ባለድርሻ አካላት እየተሳተፉ ነው።
ይህ ጉባዔ በኢትዮጵያ ለመጀመሪያ ጊዜ የሚካሄደው ሚድሮክ ኢንቨስትመንት ግሩፕ በሲያናይድ ትራንስፖርት እና ሲያናይድ አጠቃቀም ደህንነት ባስመዘገበው ውጤት ነው።
ሚድሮክ ኢንቨስትመንት ግሩፕ - የሀገር ሀብት
ℹ️ ለበለጠ መረጃ
▤▤▤▤▤▤▤▤
Youtube ገፃችንን subscribe ያድርጉ
👉 https://www.youtube.com/
Facebook ገፃችንን follow ያድርጉ
👉https://www.facebook.com/ecntv
01/02/2026
የክብረት ሽልማት፦ አርቲስት ሱራፌል ተካ መኪናውን ተረክቧል!
ለሳምንታት ሲጠበቅ የነበረው ታላቅ ቀን ዛሬ ጥር 24/2018 ዓ.ም.እውን ሆኗል!
ፖፑላር ኤሌክትሮኒክስ
(Popular Electronics) ለአርቲስት ሱራፌል ተካ ቃል የገባውን ዘመናዊ መኪና ዛሬ እሁድ ጥር 24/2018 ዓ.ም.በደመቀ ስነ-ስርዓት አስረክቧል።
ይህ ሽልማት እንዲሳካና ውጤታማ እንዲሆን የቲክቶክ ቻሌንጁን (Challenge) ተቀብሎ በብቃት የተወጣው ቲክቶከር አዶናይ ሊመሰገን የሚገባው ትልቅ ስራ ሰርቷል። አዶናይ ላሳየው ቁርጠኝነት እና ለፈጠረው መነቃቃት አድናቆት እየተቸረው ይገኛል።
አርቲስት ሱራፌል ተካ የመኪናውን ቁልፍ ሲረከብ በቦታው የነበሩ እንግዶች በታላቅ ጭብጨባ አጅበውታል።
በዝግጅቱ ላይ በርካታ ቲክቶከሮች ጋዜጠኞች የአርቲስት ሱራፌል ተካ ወዳጆች እንዲሁም ሌሎች ጥሪ የተደረገላቸው ታዋቂ ግለሰቦች በመገኘት ለዝግጅቱ ድምቀት ሰጥተዋል።
ፖፑላር ኤሌክትሮኒክስ የገባውን ቃል በተግባር በማሳየቱ እና አርቲስቱን በመሸለሙ በብዙዎች ዘንድ አድናቆትን አትርፏል። አርቲስት ሱራፌልም ለዚህ ስኬት በመብቃቱ እንኳን ደስ አለህ እንላለን!
እንኳን ደስ አለህ ሱራፌል ተካ!
ትልቅ ምስጋና ለቲክቶከር አዶናይ!
ክብር ለPopular Electronics!
ፎቶግራፍ Naomi 📸 studio
ጋዘጤኛ : ሲሳይ መንግስቴ
ℹ️ ለበለጠ መረጃ
▤▤▤▤▤▤▤▤
Youtube ገፃችንን subscribe ያድርጉ
👉 https://www.youtube.com/
Facebook ገፃችንን follow ያድርጉ
👉https://www.facebook.com/ecntv
01/02/2026
የሁለቱ ባለሐብቶች ልጆች በመቄዶንያ የአረጋውያን መርጃ ማዕከል ተዳሩ!! የሁለቱ ባለሐብቶች ልጆች በመቄዶንያ የአረጋውያን መርጃ ማዕከል ተዳሩ!!ኢትዮጵያዊቷ የሴት ባለሀብት ወ/ሮ ትልቅሰው ገዳሙ ወንድ ልጃቸውን አቶ ሁንልኝ አምደወርቅን መኪና በማስመጣት ከ....
Click here to claim your Sponsored Listing.
Category
Contact the business
Telephone
Website
Address
Addis Ababa