Selam

Selam

Share

Photos from Addis Ababa Prosperity Party - ብልፅግና's post 06/12/2024
27/11/2024

👉 ጓርዲዮላን-Pep Gardiola ምን ነካቸው?
ስፔናዊው የእግር ኳስ ሊቅ አሰልጣኝ ፔፕ ጓርዲዮላ ከትናንቱ ጨዋታ በኋላ ጭንቅላታቸውን እና አፍንጫቸውን በጥፍራቸው መቦጫጨራቸው አነጋጋሪ ሆኗል፡፡

በውድድር ዓመቱ ማንቼስተር ሲቲ እያሳየ ባለው ደካማ እንቅስቃሴ ምክንያት ከተጫዋቹ ጋር እሰጣገባ ውስጥ የገቡት አሰልጣኙ÷ በተከታታይ ነጥብ መጣላቸውን ተከትሎ የሥነ ልቦና ጫና ውስጥ መግባታቸው እየተነገረ ነው፡፡

በተለይም ቶተንሃም ሆትስፐር በኢትሃድ 4 ለ 0 ከረታቸው በኋላ መልበሻ ክፍል ውስጥ ለተጫዋቾቻቸው ስሜት ያመዘነበት ንግግር ሲያደርጉ ተደምጠዋል፡፡

ከኢቲሃዱ ሽንፈት በአግባቡ ያላገገሙት አሰልጣኙ÷ ትናንት ምሽት በአውሮፓ ሻምፒየንስ ሊግ ክለባቸው ፌይኖርድን 3 ለ 0 ሲመራ ቢቆይም በተከታታይ በተቆጠሩበት ጎሎች 3 አቻ ተለያይቷል፡፡

በውጤቱ በተከፉ የውኃ ሰማያዊዮቹ ደጋፊዎች የተተቹት ጓርዲዮላ÷ ከጨዋታው በኋላ አስተያየት በሚሰጡበት ወቅት ጭንቅላታቸውን እና አፍንጫቸውን በጥፍራቸው ቦጫጭረው መታየታቸው እያነጋገረ ነው፡፡

በወቅቱም ጋዜጠኛው የአካል ክፍላቸውን ለምን በጥፍራቸው እንደቦጫጨሩ ሲጠይቃቸው÷ “ራሴን መጉዳት እፈልጋለሁ” የሚል ምላሽ ሰጥተዋል፡፡

ተንታኞች እንደሚሉትም “ጓርዲዮላ ያጋጠማቸውን ተደጋጋሚ ሽንፈት ተከትሎ እየደረሰባቸው ባለው የደጋፊዎች ትችት ምክንያት የሥነ-ልቦና ጫና ውስጥ ገብተዋል፡፡”

በቅርቡ በማንቼስተር ሲቲ ቤት ለመቆየት የሁለት ዓመት ተጨማሪ ኮንትራት የፈረሙት አሰልጣኙ÷ በውድድር ዓመቱ በፕሪሚየር ሊግ፣ ኤፍ ኤ ካፕ እና ሻምፒየንስ ሊግ ባደረጓቸው ጨዋታዎች አራቱን ሲሸነፉ አንዱን አቻ ተለያይተዋል፡፡

በፕሪሚየር ሊጉ በቶተንሃም ሆስትስፐር ያጋጠማቸው ሽንፈት ከ52 ጨዋታዎች በሜዳ ያለመሽነፍ ጉዞ በኋላ የአሰልጣኙ አስከፊው ሽንፈት ሆኖ ተመዝግቧል፡፡

አሰለልጠኝ ፔፕ ጓርዲዮላ በባርሴሎና፣ ባየርን ሙኒክ እና ማንቼስተር ሲቲ በአሰልጣኝነት ባገለገሉባቸው ዓመታት በሁሉም ውድድሮች 38 ዋንጫዎችን አንስተዋል፡፡

26/11/2024
23/11/2024

“የትንሳኤው ዐሻራ” ዛሬ ምሽት ይጠብቁን!!

!!

30/10/2024

የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በተገኙበት ነገ መደበኛ ስብሰባውን ያካሂዳል

የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በተገኙበት ነገ መደበኛ ስብሰባውን ያደርጋል።

በመደበኛ ስብሰባው የኢፌዲሪ ፕሬዝዳንት ታዬ አጽቀስላሴ መስከረም 27 ቀን 2017 ለሕዝብ ተወካዮች እና ለፌዴሬሽን ምክር ቤቶች የጋራ ስብሰባ ያደረጉትን የመክፈቻ ንግግር አስመልክቶ ከምክር ቤቱ አባላት በሚቀርቡ ጥያቄዎች ላይ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ምላሽና ማብራሪያ ይሰጣሉ።

ይህን ተከትሎም ምክር ቤቱ የመንግስትን አቋም በማዳመጥ የድጋፍ ሞሽኑን ያፀድቃል ተብሎ ይጠበቃል።

በስብሰባው ላይ በአዲስ አበባ የሚገኙ የተለያዩ ሀገራት አምባሳደሮችና የዓለም አቀፍ ተቋማት ተጠሪዎች፣ የሃይማኖት አባቶች፣ ከፍተኛ የመንግስት የስራ ኃላፊዎች እና ሌሎች ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች እንደሚገኙ ከምክር ቤቱ የተገኘው መረጃ ያመለክታል።

Photos from Selam's post 02/10/2024

Want your practice to be the top-listed Clinic in Addis Ababa?
Click here to claim your Sponsored Listing.

Category

Website

Address


Addis Ababa