Ethio-Mereja
08/01/2021
❗️
⚡️የመከላከያ ሰራዊት ኃይል ስምሪት መምሪያ ኃላፊ ብርጋዴል ጀነራል ተስፋዬ አያሌው ለኢዜአ እንደገለፁት፣ የህወሐት አመራር ስብሃት ነጋ ከተደበቀበት ለሰው ልጅ እጅግ አስቸጋሪ የሆነ ሰርጥ ውስጥ በቁጥጥር ስር ውሏል።
በተጨማሪም በቁጥጥር ስር የዋሉ፣
1. የህወሐት አመራርና ስትራቴጂስት፣ ስብሃት ነጋ
2. ሌተናል ኮሎኔል ፀአዱ ሪች- የስብሃት ነጋ ባለቤትና ቀደም ሲል በጦር ሃይሎች ሆስፒተል ሃኪም የነበረች፣ በኋላም በጡረታ የተገለለች
3. ኮሎኔል ክንፈ ታደሰ- ከመከላከያ የከዳ
4. ኮሎኔል የማነ ካህሳይ- ከመለካከያ የከዳ
5. አስገደ ገ/ ክርስቶስ- ከመሃል ሀገር ተጉዞ ቡድኑን የተቀላቀለና ለጊዜው ሃላፊነቱ ያልታወቀ ግለሰብ በቁጥጥር ስር የዋሉ ሲሆን
6. የሜጀር ጀነራል ሃየሎም አርአያ ባለቤት የነበረችና ኑሮዋን በአሜሪካ አድርጋ የቆየች በኋላም ወደ አዲስ አበባ በመምጣት ወደ ህወሐት ተቀላቅላ የነበረች፣ ወይዘሮ አልጋነሽ መለስ ህወሕርትን በመያዝ ኦፕሬሽን ሂደት ውስጥ ለማምለጥ ስትሞክር ገደል በመግባት ህይወቷ ማለፉን ብርጋዴል ጀነራል ተስፋዬ አያሌው ገልፀዋል።
08/10/2020
ጭራሹኑ ሱሰኛ አንበጣ ነዉ የመጣብን!!!
04/10/2020
በህዳሴ ግድቡ አካባቢ ያለው የኢትዮጵያ የአየር ክልል ለበረራ ዝግ መደረጉ ተገለጸ!
የኢትዮጵያ ሲቪል አቪዬሽን ዋና ዳይሬክተር ወሰንየለህ ሁነኛው (ኮሎኔል) ለሪፖርተር እንዳረጋገጡት፣ የታላቁ ህዳሴ ግድብ በሚገነባበት ቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል ውስጥ ያለው የኢትዮጵያ የአየር ክልል ከማንኛውም ዓይነት የበረራ እንቅስቃሴ ዝግ እንዲሆን፣ ከሚመለከታቸው የደኅንነት አካላት ጋር በመወያየት ክልከላ ተጥሎበታል።
በመሆኑም የንግድ ወይም የመንገደኞች ማጓጓዣ አውሮፕላኖችም ሆኑ ሌሎች ዓይነት የበረራ እንቅስቃሴዎች፣ ግድቡ በሚገኝበት አካባቢ መከናወን እንደማይችሉ ገልጸዋል።
ይህ ቢሆንም የሚመለከተው አካል በሚሰጠው ልዩ ፈቃድ ብቻ በተከለከለው የአየር ክልል በረራ እንዲደረግ ሊፈቀድ እንደሚችል አስረድተዋል። የአገርን ደኅንነት ለማረጋገጥ እንዲህ ዓይነት ክልከላዎችን መጣል በዓለም አቀፍ አሠራር የተለመደ መሆኑን የገለጹት ዋና ዳይሬክተሩ፣ ኢትዮጵያም የግድቡን ደኅንነት ለማረጋገጥ ሰትል ይህንን ክልከላ መጣሏን ገልጸዋል።
Reporter Newspaper
ቀነኒሳ በቀለ ከለንደን ማራቶን ውጪ ሆኗል !!!
Click here to claim your Sponsored Listing.
Category
Website
Address
Addis Ababa