Imam Tefera

Imam Tefera

Share

18/10/2022

ሚሽነሪዎች ኢየሱስ ብርሃን ተብሏል ስለዚህ በቁርአንና በኢየሱስ ንግግር ፈጣሪ የተባለው ኢየሱስ ነው ብለው አረፉት፦

ዮሐንስ 8፥12 ደግሞም ኢየሱስ፦ "እኔ የዓለም ብርሃን" ነኝ፤

እኛም ምግታችንን ሰፋ አድርገን ታዲያ ኢየሱስ የዓለም ብርሃን መባሉ አምላክ ያሰኘዋልን? ብለን ጥያቄ እናቀርባለን፤ መልሱ አዎ ከሆነ እንግዲያውስ ብዙ አምላኮች ሊኖሩ ነው፤ ምክንያቱም የዓለም ብርሃን የተባለው ኢየሱስ ብቻ ሳይሆን ሃዋርያትም ጭምር ናቸው፦
ማቴዎስ 5፥14 " " ናችሁ።

አይ ሃዋርያትን ብርሃን ያደረጋቸው እግዚአብሔር ስለሆነ የእነርሱ ብርሃንነት በመደረግ የተመሰረተ የፀጋ እንጂ የባህርይ አይደለም ከተባለ ኢየሱስንስ ብርሃን ያደረገው እግዚአብሔር አይደለምን? ስለዚህ የኢየሱስ ብርሃን መሆን እንደ ሃዋርያት በፀጋ እንጂ የባህርይ አይደለም፦
ኢሳይያስ 49፥6 እርሱም፦ የያዕቆብን ነገዶች እንድታስነሣ ከእስራኤልም የዳኑትን እንድትመስል ባሪያዬ ትሆን ዘንድ እጅግ ቀላል ነገር ነውና እስከ ምድር ዳር ድረስ መድኃኒት ትሆን ዘንድ ለአሕዛብ ""ብርሃን አድርጌ"" ሰጥቼሃለሁ ይላል።
ኢሳይያስ 42፥7 እኔ እግዚአብሔር በጽድቅ ጠርቼሃለሁ፥ እጅህንም እይዛለሁ እጠብቅህማለሁ፥ የዕውሩንም ዓይን ትከፍት ዘንድ የተጋዘውንም ከግዞት ቤት በጨለማም የተቀመጡትን ከወህኒ ቤት ታወጣ ዘንድ ለሕዝብ ቃል ኪዳን ለአሕዛብም ""ብርሃን አድርጌ"" እሰጥሃለሁ።

26/07/2022

ፈጣሪ(አምላክ)በሰራው (በወሰነው) ውሳኔ እንደሰው ልጅ ይፀፀታል? ወይስ አይፀፀትም?
➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖
1✅“ሐሰትን ይናገር ዘንድ እግዚአብሔር ሰው አይደለም፥ #ይጸጸትም ዘንድ የሰው ልጅ አይደለም።”
— ዘኍልቁ 23፥19

2✅“እግዚአብሔርም ሰውን በምድር ላይ በመፍጠሩ #ተጸጸተ፥ በልቡም #አዘነ።”
— ዘፍጥረት 6፥6
ዕውን አምላክ (ፈጣሪ) እንደ ሰው ልጅ ያዝናልን?

“እግዚአብሔርም ስለዚህ ነገር #ተጸጸተ፤ ይህ አይሆንም፥ ይላል እግዚአብሔር።”
— ትንቢተ አሞፅ 7:3
ዕውን አምላክ (ፈጣሪ) እንደ ሰው ልጅ ይፀፀታልን?

3✅“በፊቴ ክፉን ነገር ቢያደርግ ቃሌንም ባይሰማ፥ እኔ አደርግለት ዘንድ ስለ ተናገርሁት መልካም ነገር #እጸጸታለሁ።”
— ኤርምያስ 18፥10
ዕውን አምላክ (ፈጣሪ) እንደ ሰው ልጅ ይፀፀታልን?

4✅“የእግዚአብሔርም ቃል፦ ሳኦል እኔን ከመከተል ተመልሶአልና፥ ትእዛዜንም አልፈጸመምና ስላነገሥሁት #ተጸጸትሁ ብሎ ወደ ሳሙኤል መጣ።”
— 1ኛ ሳሙኤል 15፥10-11
ዕውን አምላክ (ፈጣሪ) እንደ ሰው ልጅ ይፀፀታልን?

5✅“እግዚአብሔርም ያጠፋት ዘንድ ወደ ኢየሩሳሌም መልአክን ሰደደ፤ ሊያጠፋትም በቀረበ ጊዜ እግዚአብሔር አይቶ ስለ ክፉው ነገር #ተፀጸተ።”
— 1 ዜና 21፥15
ዕውን አምላክ (ፈጣሪ) እንደ ሰው ልጅ ይፀፀታልን?


6✅“እግዚአብሔርም በሕዝቡ ላይ ሊያደርግ ስላሰበው ክፋት #ራራ።”
— ዘጸአት 32፥14
ዕውን አምላክ (ፈጣሪ) እንደ ሰው ልጅ ይፀፀታልን?

7✅“የእግዚአብሔርም መልአክ ኢየሩሳሌምን ያጠፋት ዘንድ እጁን በዘረጋ ጊዜ እግዚአብሔር ስለ ክፉው ነገር #አዘነ፥”
— 2ኛ ሳሙኤል 24፥16
ዕውን አምላክ (ፈጣሪ) እንደ ሰው ልጅ ይፀፀታልን?

8✅“እግዚአብሔርም፦ የፈጠርሁትን ሰው ከምድር ላይ አጠፋለሁ፥ ከሰው እስከ እንስሳ እስከ ተንቀሳቃሽም እስከ ሰማይ ወፍም ድረስ ስለ ፈጠርኋቸው #ተጸጽቼአለሁና አለ።”
— ዘፍጥረት 6፥7
ዕውን አምላክ (ፈጣሪ) እንደ ሰው ልጅ ይፀፀታልን?

9✅“እግዚአብሔርም በእስራኤል ላይ ሳኦልን ስላነገሠ #ተፀፀተ።”
— 1ኛ ሳሙኤል 15፥35
ዕውን አምላክ (ፈጣሪ) እንደ ሰው ልጅ ይፀፀታልን?

10✅“ይህ ስለ እርሱ የተናገርሁበት ሕዝብ ከክፋቱ ቢመለስ፥ እኔ አደርግበት ዘንድ ካሰብሁት ክፉ ነገር #እጸጸታለሁ።”
— ኤርምያስ 18፥8
ዕውን አምላክ (ፈጣሪ) እንደ ሰው ልጅ ይፀፀታልን?

‼Note:–
ከላይ በጥቂቱ በተመለከትናቸው 10 ያህል የመፅሀፍ ቅዱስ ጥቅሶች (አንቀፆች) መሰረት "ፈጣሪ ወዶና ፈቅዶ ከሰራ (ከወሰነ) በኋላ ፈጣሪ በስራው እንደ ሰው ልጅ ይፀፀታል?

❓ወይስ ፈጣሪ (አምላክ) አይፀፀትም?❓

የመፅሀፍ ቅዱስ የርስ በርስ ግጭቶችን አስታርቁልን እስኪ

06/01/2022

መቼ ነው ?

ኡስታዝ አብዱልመጅድ ሁሴን አላህ ይዘንለት የዛሬ 4 ዓመት ፖስት ባደረገው ፅሁፉ መቼ ነው ? ሲል ይጠይቀናል:: ራሳችንን እንጠይቅበት :: ይሄን የጠየቀን ሰው ወደ እውነተኛ ቤቱ ሂዷል :: ራሳችንን እንጠይቅ እስኪ

*መቼ ነው* እውነተኛ ሙስሊሞች የምንሆነው?
*መቼ ነው* አላህ በፈጠራቸው ነግሮች የምንማረከው?
*መቼ ነው* አሏህ ለምን እንደፈጠርን የምንረዳው?
*መቼ ነው* አሏህ እንደሚፈልገው መኖር የምንጀምረው?
*መቼ ነው* ስለ ሀይማኖታችን በሙሉ ልብ እምንናገረው?
*መቼ ነው* እማይጠቅም ንግግር ከመናገር የምንቆጠበው?
*መቼ ነው* ሀዲስና ቁርአን ስንሰማ የምንደነግጠው?
*መቼ ነው* ለመልካም ስራ ሰበብ የምንሆነው?
*መቼ ነው* በሰላታችን የምንጠቀመው?
*መቼ ነው* ዱአችን ተሰሚነት የሚያገኝው?
*መቼ ነው* ዲናችንን የምንረዳው?
*መቼ ነው* ውሎና አዳራችን በሱና የሚሆነው?
*መቼ ነው* ሙሉ በሙሉ በአሏህ ላይ የምንመካው?
*መቼ ነው* የዱንያን ትልቅነት ከልባችን የምናወጣው?
*መቼ ነው* ቤታችን ውስጥ ያለው የተበላሸ ሂዎት የሚስተካከለው?
*መቼ ነው* ቤታችን ውስጥ ቁርአንና ሀዲስ የሚቀራው የሚወራው?
*መቼ ነው* ውሽት እምናቆመው?
*መቼ ነው* የአሏህን ውሳኔ መቃውም እምናቆመው?
*መቼ ነው* እኔ እኔ ማለት ትተን ውንደሜ እህቴ ማለት እምንጀምረው?
*መቼ ነው* ለሰዎች ከአላህ ውጪ ጌታ እንደሌለ እምንናገረው?
*መቼ ነው* በኛ ዘመን በዲናችን የበላይነት ምናገኝው?
*መቼ ነው* የኢስላም ዘቦች የምንሆነው?
*መቼ ነው* ኢስላምን የምናስተዋውቀው?
*መቼ ነው* ለድሃ እምናዝነው?.
*መቼ ነው* ትዳራችን ስላም ሚያገኝው?
*መቼ ነው* የጋብቻን ጥቅም ተገንዝበት ለትዳር የምንቻኮለው?
*መቼ ነው* ዱአቶቻችን ለገጠሩ የሚጨነቁት?
*መቼ ነው* ከሀሜት; ስውን ከመበድል; ክማስቀየምና ከማማት እምንላቀቀው?
*መቼ ነው* ወላጆቻችንን እምናስደስተውና እምንታዝዝው?
*መቼ ነው* ያልተጣራ ውሬ ካማውራት እምንቆጠበው?
*መቼ ነው* ለአሏህ ብለን እምንዋደደው?
*መቼ ነው* አሏህ በወሰነልን ነገር ደስተኞች የምንሆነው?
*መቼ ነው* የሌሊት ሰላትንና ዚክርን የምንላመደው?
*መቼ ነው* የበድለንን ይቅር የመንለው?
*መቼ ነው* ከራስ ወዳድነት እምንላቀቀው?
*መቼ ነው* ከሞት ቡኃላ ላለው ሂወት ስንቅ እምናዘጋጀው?
*መቼ ነው* ኡለማዎቻችንን እምናከብረው?
*መቼ ነው* ለእውቅት ጊዜ የምንሰጠው?
*መቼ ነው* ባወቅነው የምንሰራው?
*መቼ ነው* የ ምንሞትበትን ቀንም ይሁን ስፍራ እንደማናውቅ ተገንዝበን በተጠንቀቅ የምንቆመው?
*መቼ እረ መቼ ነው* ኢስላምን የምንኖረው?
*መቼ ነው* ለእነዚህ ተግባራዊ መልስ የምንመልሰው?
*አሏህ ያግራልን*
አብዱረሂም አህመድ

Want your public figure to be the top-listed Public Figure in Addis Ababa?
Click here to claim your Sponsored Listing.

Category

Telephone

Website

Address


Addis Ababa

Opening Hours

09:00 - 17:00