EAS

EAS

Share

31/05/2026

373

ኢኳዶሪያዊያኖቹ
ዊሊያን ፓቾ እና ፒየሮ ሂንካፒ!

ዕለተ እሁድ ግንቦት 23 /2018 ዓም የኢትዮ-አዲስ ስፖርት መሰናዶ ከቀኑ 6:00-7:00 በተወዳጁ ብስራት FM 101.1 ላይ አየር ላይ ይውላል።

የክለቦች ውድድር ቁንጮ የሆነው የአውሮፓ ቻምፕየንስ ሊግ በሀንጋሪ ቡዳፔስት በፑሽካሽ አሬና ስታድየም ተጠናቋል።

ፔዤ በድጋሜ የአውሮፓ ሀያልነቱን ክብር ያስጠበቀበት ድል ተጎናፅፏል።

መድፈኞቹ በታሪካቸው ለመጀመሪያ ጊዜ አሸናፊ የሚሆኑበትን እድል ማሳካት አልቻሉም።

በዚህ የፍፃሜ ጨዋታ ላይ በታሪክ ለመጀመሪያ ጊዜ በአውሮፓ ቻምፕየንስ ሊግ ፍፃሜ ሁለት ኢኳዶራዊያን በተቃራኒ ሆነው ተፋልመዋል።

ከፓሪስ በመቀጠል አሸናፊዋ ኢኳዶር ነበረች።

ዊልያን ፓቾ እና ፒየሮ ሂንካፒ

በትናንቱ ጨዋታ ላይ ኢኳዶርን ባኮሩት ወርቃማ ልጆቿ ዙሪያ ቆይታ እናደርጋለን።

እናንተስ የምሽቱ ጨዋታ እንዴት አያችሁት?

👉 የአርቴታ የጨዋታ አቀራረብ፣ ፣የተጨዋች ምርጫ እና ቅያሪ?

👉 የማጋሌሽ መለያ ምት ጉዳይ?

👉 ኤነሪኬ ለ 3ኛ ጊዜ የአውሮፓ ቻምፕየንስ ሊግ ዋንጫ አንስቷል።ታዲያ በታሪክ ከሰፈሩት ከቁንጮ አሰልጣኞች ዝርዝር እንዲገባ አያደርገውም?

በነዚህ እና በሌሎች ስፖርታዊ ጉዳዮች ላይ ሀሳባችሁን ፃፉልን።

- የሚሳተፉበትና የሚዝናኑበት

26/04/2026

365

Al Ahly - AFC Champion

ዕለተ እሁድ መጋቢት 18/2018 ዓም የኢትዮ-አዲስ ስፖርት መሰናዶ ከቀኑ 6:00-7:00 በተወዳጁ ብስራት FM 101.1 ላይ አየር ላይ ይውላል።

የሳውዲው አል አህሊ በድጋሚ የኤሺያ ቻምፕየንስ ሊግ አሸናፊ በመሆን አጠናቋል።

ሪያድ ማህሬዝ ሁለት እና ጓደኞቹ በሁለት ተከታታይ አመታት አሸናፊ በመሆን የወቅቱ የኤሺያ ንጉስ ሆነዋል።

በተለይ ማህሬዝ ከማን ሲቲ ጋር የአውሮፓ ቻምፕየንስ ሊግ አሸናፊ የነበረ ሲሆን አሁን ደግሞ ከሳውዲው ክለብ ጋር የኤሺያውን አምሳያ እያጣጣመው ይገኛል።

ዛሬ በቆይታችን ከሌሎች አጫጭር ጉዳዮች ጋር አድርገን የምናነሳው ጉዳይ ነው።

ትናንት በአውሮፓ የሊግ ጨዋታዎች ተደርገዋል

👉 አርሰናል ወደ መሪነት ተመልሷል።

👉 ሊቨርፑል ፓላስን ባሸነፈበት ጨዋታ የሞ ሳላህ ጉዳት በሊፐርፑል ማሊያ የመጨረሻው ያደርገው ይሆን?

👉 ቶተንሀም እና ዌስትሀም ላለመውረድ ተፋጠዋል

👉 ሲቲ በድጋሚ ለ FA cup ፍፃሜ መብቃት ችሏል።

ዛሬ(FA Cup)

ቼልሲ ከ ሊድስ?

ነገ(ፕሪምየርሊግ)

ማን ዩናይትድ ከ ብሬንትፎርድ

ማን ያሸንፋል?በኮሜንት ሳጥን ሀሳባችሁን አካፍሉን

- የሚሳተፉበትና የሚዝናኑበት

Want your business to be the top-listed Gym/sports Facility in Addis Ababa?
Click here to claim your Sponsored Listing.

Telephone

Address


Lideta
Addis Ababa