ALSA
የደቡብ ብ/ብ/ሕ/ክ/መንግስትየሰራተኛና ማህበራዊ ጉዳይ ኤጀንሲ ዋና ዳይሬክተር መልእክት
የሠራተኛና ማህበራዊ ጉዳይ ኤጀንሲ ከተሰጠው ተግባርና ኃላፊነት የለውጥ ሰራዊትን በመገንባትና በማሰማራት በመንግስት የተሰጠውን ተልዕኮ በመፈፀም የተገልጋይ እርካታን ማረጋገጥ ሲሆን ቁልፍ ተግባራትን ለመፈፀምና ተቋማዊ ለውጥን ለማረጋገጥ ሲባል በርካታ የተግባር እንቅስቃሴዎች ሲደረጉ ቆይተዋል፡፡ ከዚህ አንፃር በመስፋፋት ላይ የሚገኙ ኢንዱስትሪዎችና አገልግሎት ሰጪ ተቋማት ላይ የስራ ቦታዎች ለሥራ ምቹ እንዲሆኑና የስራ ላይ አደጋና በሽታ እንዳይከሰት የመከላከል የሙያ ጤንነትና ደህንነት በሚመለከት የግንዛቤ ማስጨበጫና የቁጥጥር ሥራዎች የማከናወን፣ሴክተሩን በሚመለከት የወጡ ፖሊሲዎች፣ አዋጆች ደንቦችና መመሪያዎች እንዲሁም ሀገራችን የተቀበለቻቸው አለም ዓቀፍ ኮንቬንሽኖችና ስምምነቶችን ተግባራዊ በማድረግ ችግር ፈቺ የሆኑ ጥናቶችና ምርምሮችን በማካሄድ የረጅም፣ የመካከለኛና አጭር ጊዜ ዕቅዶችን በመንደፍ ለአሰሪዎችና ለሰራተኞች በአጠቃላይ ለህብረተሰቡ ግንዛቤ የማስጨበጥ ስራዎችን በማከናወን የኢንዱስትሪ ሰላም እንዲሰፍን ለማድረግ ትኩረት ሰጥቶ በመስራት ላይ ይገኛል፡፡
በክልላችን በተፈጠረው ምቹ የኢንቨስትመንት ፖሊሲ አኳያ እየተስፋፋ ባለው የግሉ ዘርፍ እንዲሁም መንግስት በተለያዩ ዘርፎች በሚያካሂዳቸው መጠነ ሰፊ የልማት ስራዎች ለበርካታ ዜጎች ሰፊ ጊዜያዊና ቋሚ የስራ እድሎች እንዲፈጠርላቸው ኤጀንሲው የስራ ገበያ አደራጅቶ በመያዝ ሥራና ሰራተኛን በማገናኘት የስራ አጥነት ችግሮችን በመቅረፍ ላይ ይገኛል፡፡ ከዚህ አኳያ ለወቅታዊ የግብርና ልማት ስራዎች በክልላችንና ከክልላችን ውጭ ወደሚገኙ የልማት ድርጅቶች የሚሄዱትን ሰራተኞች በማስተባበር የልማት ድርጅቶችን የሰው ሀይል ፍላጎት ማሟላትና የቤተሰብ ጥሪት የመገንባት ስራዎችን ማገዝ ህገመንግስታችን የሰጠውን የመደራጀት መብት ተጠቅመው የተደራጁ የአሰሪም ሆነ የሰራተኛ ማህበራትን አግባብነት ባላቸው ህጎች ዙሪያ ግንዛቤ በማስጨበጥና በማጠናከር ለእንዱስትሪ ሰላም መስፈን እንዲሁም ለምርትና ምርታማነት መጎልበት የበኩላቸውን እንዲወጡ ማድረግ ትኩረት ሰጥቶ የሚተገብራቸው ስራ ናቸው፡፡
በክልላችንም ሆነ በአገራችን ማህበረዊና ኢኮኖሚያዊ ችግር ከመሆን አልፎ በሀገር ገጽታ ላይ አሉታዊ ጥላ እያሳረፈ የሚገኘውን ሕገ-ወጥ የሰዎች ዝውውር ለመከላከል ወጣቱ በሀገር ውስጥ ባሉና በተመቻቹ የስራ ዕድሎች እንዲጠቀም እንዲሁም ሕብረተሰቡ ስለ ህገ-ወጥ የሰዎች ዝውውር አስከፊነት ግንዛቤ ማስጨበጥና ህገ-ወጥ አዘዋዋሪዎችን ወደ ህግ ፊት እንዲቀርቡ ከማድረግ አንፃር ባለድርሻ አካላትን በማስተባበር ሰፊ ስራዎችን ይሰራል፡፡ በተጨማሪም የህፃናትን ጉልበት ብዝበዛና የህፃናት ህገ-ወጥ ዝውውር ከመከላከል አኳያ ኤጀንሲው ከሚመለከታቸው ጋር በመሆን ተግቶ በመስራት ላይ ይገኛል፡፡
በማህበራዊ ጥበቃ ዘርፍ በማህበራዊ ችግሮች ውስጥ የሚገኙትና ለማህበራዊ ኑሮ ጠንቆች ተጋላጭ የሆኑት የህብረተሰብ ክፍሎች ማለትም አካል ጉዳተኞች፣ አረጋውያን፣ ሴተኛ አዳሪዎች፣ ወላጅና አሳዳጊ ያጡ ህፃናትና ሌሎች ከድህነት ወለል በታች ያሉና ማህበራዊ መገለል የሚደርስባቸው የህብረተሰብ ክፍሎች ችግሮቻቸው የሚቀረፈው በማህበረሰብ አቀፍ አደረጃጀትና አሰራር መሆኑን በመገንዘብ ባለድርሻ አካላትን በማሳተፍ ስልት ቀይሶ እንቅስቃሴ በማድረግ ላይ ይገኛል፡፡
ሴክተሩ የተጣለበትን ኃላፊነት ለመወጣት በሚያደርገው ቀጣይ ጥረት ከጊዜ ወደ ጊዜ ለውጥ እያሳየ መምጣቱ እሙን ነው፡፡ ይህ ደግሞ ሀገራችን ለምታራምደው የሰላም፣ የልማትና ዲሞክራሲ ስርዓት ግንባታ መፋጠን ሁነኛ ድርሻ እያበረከተ መገኘቱን ለማየት የሚያስችል ነው፡፡ በዚህ መሠረት የለውጥ ሰራዊት ግንባታ ለሴክተሩ ተልዕኮ መሳካት ወሳኝ ድርሻ የሚያበረክት አቅም ስለሆነ በግባታው ሂደት ጠንካራ ቁመና ያለው የሰራተኛና ማህበራዊ ጉዳይ ሴክተር የልማት ሰራዊት በመገንባት ሴክተሩ በሚሰጠው ዘርፈ ብዙ አገልግሎት ተደራሽ፣ ፍታሃዊና የህዝብን ተጠቃሚነት በሚያረጋግጥ መልኩ ተፈፃሚ በማድረግ መልካም አስተዳደርን ለማስፈንና በተያዘው ንቅናቄ ውስጥ እምርታ የማሳያት ጥረት ይበልጥ ተጠናክሮ ይቀጥላል፡፡
Click here to claim your Sponsored Listing.
Category
Contact the organization
Website
Address
Addis Ababa