Alem TV

Alem TV

Share

መረጃ ለአንድ ሀገርና ህዝብ ማህበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊና ፖለቲካዊ እድገት እጅግ ከፍተኛ ሚና ይጫወታል፡፡ “የመረጃ ዘመን” በመባል በሚታወቀው የ21ኛው ክፍለ ዘመን መረጃ የህይወት አንዱና ዋነኛው አካል ሆኗል፡፡ ዘመናዊ የመረጃና የኮሚኒኬሽን ቴክኖሎጂ መስፋፋት ለመረጃ ዝውውር ከፍተኛ እገዛ አድርጓል፡፡ የድረ-ገጽ /ኢንተርኔት/ ቴክኖሎጂ ጥቅም ላይ ከዋለበት የ1990ዎቹ መጀመሪያ ጀምሮ የዓለማችን የኢኮኖሚ፣ ማህበራዊና ፖለቲካዊ ለውጦች ዋነኛ ማዕከል ሆኖ በማገልገል ላይ ይገኛል-መረጃ፡፡

አፍሪካ እንደ ቀሪው የዓለም ክፍል ሁሉ ከዚህ ዘርፍ ተጠቃሚ ሆናለች፡፡ በርካታ የአፍሪካ ሀገራት ኢንተርኔትን ጨምሮ የሌሎች የመረጃ ቴክኖሎጂዎች

26/01/2020

ዓለም ቲቪ በአዲስ መልክ እንቅስቃሴ ጀመረ!!
ዓለም ቲቪ ላለፉት ጥቂት ዓመታት አንድ ጠንካራ እና ተጽኖ ፈጣሪ የቴሌቪዥን ጣቢያ ሆኖ ለመውጣት ሲያደርገው የነበረው ጥረት በፋይናንስ እና ሌሎች ተግዳሮቶች ምክንያት የተስተጓጎለ ቢሆንም፣ ድርጅቱ ያጋጠሙትን መሰናክሎች አልፎ ራእዩን እውን ለማድረግ ስራውን ለአፍታም ሳያቋረጥ ቀጥሏል፡፡

ዓለም ቲቪ ዛሬም ጥረቱን አጠናክሮ በመቀጠል እና ወሳኝ የአደረጃጀት ለውጥ በማድረግ ለሀገራችን አንድ ተጨማሪ የቴሌቪዥን አገልግሎት ለመፍጠር በአዲስ ኃይል እና አደረጃጀት እንቅስቃሴ ጀምሯል፡፡

ዓለም ቲቪ በተለይ ባለፉት ሁለት አመታት በሀገራችን የተፈጠረውን የፖለቲካ ለውጥ ታሳቢ ያደረገ የፕሮግራም እና የኮንሴፕት ሽግሽግ ያደረገ ሲሆን፣ በሀገራችን የብሮድካስቲንግ ህግ መሰረት የአሰራር ለውጥ ለማካሄድ የሚያሰፈልጉ የህግ ማሻሻያዎችንም በማድረግ ላይ ይገኛል፡፡

በተለያዩ የፖሊሲ፣ አስተዳደራዊ፣ የቴክኖሎጂ፣ የሰው ኃይል እና ሌሎች ተያያዥ ችግሮች የታጠረውን የሀገራችን የፕሮድካስቲግ ሴክተር፣ በአንድ እርምጃ ወደፊት ለማራመድ አስተዋጾ ይኖረዋል ተብሎ የሚጠበቀው የዓለም ቲቪ እውን ሆኖ ለማየት የቴሌቪዥኑ አደራጆች በአዲስ አስተሳሰብ እና አመራር እንቅስቃሴ ጀምረዋል፡፡
የዓለም ቲቪ ፕሮግራሞችን በቴሌቪዥን መስኮት የምናይበትን ግዜ ሩቅ አይሆንም፡፡

ከዓለም ቲቪ ፕሮግራሞች አንዱ የሆነውን “ለውጥ” የተሰኘ ፕሮግራም ለቅምሻ ጀባ ብለናል፡፡

ዓለም ቲቪ፡ የመረጃ አለም፡፡

#EBC በአዲስ አበባ መስቀል አደባባይ በምስጋናው ሰልፍ ላይ በደረሰው ጉዳት ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዓቢይ አህመድ መግለጫ 24/06/2018

#EBC በአዲስ አበባ መስቀል አደባባይ በምስጋናው ሰልፍ ላይ በደረሰው ጉዳት ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዓቢይ አህመድ መግለጫ Ethiopian Broadcasting Corporation is a national media which disseminates its news and programs world wide via Television,Radio and Website

ሰበር ዜና 23/06/2018
Untitled album 23/06/2018
Want your business to be the top-listed Media Company in Addis Ababa?
Click here to claim your Sponsored Listing.

Website

Address


Addis Ababa