LDI

LDI

Share

Livestock Development Institute is an Institute established by The Council of Ministers Regulation No. 506/2014 to conduct research, capacity building and counseling services on animal genetic improvement and product processing activities.

Photos from LDI's post 31/12/2024

የእንስሳት ልማት ኢንስቲትዩት ለ56ኛ ጊዜ ያሰለጠናቸውን የአዳቃይ ቴክኒሽያኖች አስመረቀ!
==========================================
የእንስሳት ልማት ኢንስቲትዩት ከምግብ ሥራዓት ማጠናከሪያ ፕሮግራም ጋር በመተባበር ለ56ኛ ጊዜ ያሰለጠናቸውን 141 (ወ 126፣ ሴ 15) ከተለያዩ ክልሎች የተውጣጡ የእንስሳት አዳቃይ ቴክኒሽያኖችን ዛሬ ታህሳስ 22 ቀን 2017 ዓ.ም የተከበሩ እንግዶች፣ ለሥልጠናው ልዩ አስተዋጽዎና ድጋፍ ያደረጉ እና የኢንስቲትዩቱ ማኔጅመንት እና ሠራተኞች በተገኙበት በይፋ አስመርቋል፡፡

በግብርና ሚኒስቴር የእንስሳት ዘርፍ ሚኒስተር ዴኤታ የሆኑት ክቡር ዶክተር ፍቅሩ ረጋሳ(ፒኤችዲ) እና የኢንስቲትዩቱ ዋና ዳይሬክተር የሆኑት ዶክተር አስራት ጤራ(ፒኤችዲ) ተመራቂዎቹን እንኳን ደስ አላችሁ በማለት ለተመራቂዎቹ መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡

ክቡር ዶክተር ፍቅሩ ረጋሳ(ፒኤችዲ) በምረቃው ሥነ ሥርዓት ላይ ባስተላለፉት መልዕክት በክቡር ጠቅላይ ሚኒስትራችን በተነደፈው የሌማት ትሩፋት ስኬት የእንስሳትን ምርትና ምርታማነትን ለማሳደግ በግንባር ቀደምትነት ዝርያ ማሻሻል ወሳኝ ሥራ መሆኑን በመጥቀስ ይህን የእንስሳት ዝርያና ለማሻሻል ደግሞ የአዳቃይ ቴክኒሽያኖች ከፍተኛ ሚና የሚጫወቱ መሆኑን በመጥቀስ መንግስት ከፍተኛ ኃላፊን የጣለባቸው መሆኑን በመጥቀስ ተመራቂ ሠልጣኞች ወደመጡበት ተመልሰው ይህን ሀገራዊ ኃላፊነት በብቃት እና ጥራት እንዲወጡ የሥራ መመሪያ ሰጥተዋቸዋል፡፡

በመቀጠልም የክብር እንግዳው ክቡር ዶክተር ፍቅሩ ረጋሳ (ፒኤችዲ) አጭር የሥራ ጉብኝት አድርገው የዕለቱ ፕሮግራም ተጠቃሏል፡፡

እልኢ ታህሳስ 22 ቀን 2017 ዓ.ም

Photos from LDI's post 11/12/2024

የእንስሳት ልማት እንስቲትዩት፤ሆለታ ማዕከል(ሆ/እ/ል/ማ) ከ 40.000-45.000 የድርቆሽ ሳር ቦንዳ ለማገኘት እየሰራ ይገኛል
በ2017 ዓ.ም ማዕከሉ ከ40-45 ሺህ የድርቆሽ ሳር ቦንዳ ለማገኘት አቅዶ እየሰራ እንደሚገኝ የማዕከሉ ስራ አስኪያጅ ሙሉጌታ ተስፋዬ ገልጸዋል።
ለሳሩ ማከማቻ የሚሆን ሃያ(20) ሃያ(20) ሽህ የሚይዙ ሁለት መጋዝኖች ተዘጋጅቷል።
ስራዉ በአጠቃላይ ከ 80 በላይ ዜጎች ግዜያዊ የስራ እድል መፍጠር እንደተቻለም አክለዋል፡፡
በ2016 ዓ.ም 58,409 የድርቆሽ ሳር ቦንዳ ተሰብስቦ እንደ ነበርም ጠቅሰው የዘንድሮ ምርት ግን የከብቶች ብዛት መጨመርን ተከትሎ ይመረት ከነበረዉ ምርት እንደቀነሰ ጠቅሷል።
የሳር አጨዳ እና መሰብሰቡ ስራ በአጠቃላይ ከ 80 በላይ ለሚሆኑ ዜጎች ግዜያዊ የስራ እድል መፍጠር ተችሏል፡፡
ማዕከሉ በተጨማሪም የድርቆሽ ሳር ከማምረት ባሻገር የተቀነባበረ የእንስሳት መኖ እንደ አስፈላጊነቱ ለጥጃ፤ ለኮርማ እና ለወተት ላሞች በ ራሱ መኖ ማቀነባበሪያ ፋብሪካ እያመረተ ለዋና መስሪያ ቤት ኮርማዎች ፤ ለቢሾፍቱ እንስሳት ልማት ማዕከል የወተት ላሞች እና ክልሎች እንደሚያከፋፍል እና ፋብሪካዉ በቀን እስከ 150 ኩንታል የማምረት አቅም አለው።

Photos from LDI's post 10/12/2024

ኢትዮ-ቻይና የኢኮኖሚ ንግድ ወደ ላቀ እድገት የሚያሸጋግር ልምድ ልውውጥ ተደረገ
በእንስሳት ልማት እንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር አሥራት ጤራ(ፒኤችዲ)ና አመራሮች እንድሁም የመካከለኛ አፍሪካ ቀጠና ስራ ሀላፊ ው ሊያዓንቢን(Ms Wu Lianbin) እና ሊዩ ያጅናን(Mr Liu Yajnan) ጋር የሁለቱ ሀገራት የንግድ ልውውጥ(import-export) ያሉት እድሎችና እንቅፋቶች በተለይ በተቋማችን እየተሰራ ባለው የቄራዎች ጥራት እና ደረጃ የማሳደግ ፡እንዲሁም ወደ ቻይና የሚላኩ ምርቶች ብዛታቸውና ጥራታቸውን ጠብቆ በተለይ የስጋ ምርት ወደ ቻይና ተልኮ ለሀገሪቱ የዉጭ ምንዛሬውን ማሳደግ በሚቻልበት ዙሪያ ተዋያይቷል።
በዚህ አመት ብቻ ኢትዮጵያ ከቻይና ወደ 435.95ሚ ዶላር በላይ ስጋን ጨምሮ ከተለያዩ ሸቀጣ ሸቀጦች አግኝታለች። የሀገሪቱ የስጋ መላክ ሙሉ አቅሟ 200,000 ስጋ ቶን ብሆንም በአሁኑ ወቅት ግን 22,000ስጋ ቶን ስጋ ብቻ መላክ እንደተቻለ ስሆን የመላክ አቅሟን ለማሳደግ እየተሰራ ይገኛል።

06/12/2024

የእንስሳት ልማት ኢንስቲትዩት አመራሮች እና ሠራተኞች ለ19ኛ ጊዜ "አገራዊ መግባባት ለኅብረ ብሔራዊ አንድነት' በሚል መሪ ቃል የብሔር ብሔረሰቦችእና ሕዝቦች በዓል በደማቅ ሁኔታ አክብሯል።

በበዓሉ ለዕለቱ በተዘጋጀው ሰነድ ላይ የግንዛቤ ማሰጨበጫና ውይይት ተካሂዷል።

Want your school to be the top-listed School/college in Addis Ababa?
Click here to claim your Sponsored Listing.

Telephone

Website

Address


Addis Ababa

Opening Hours

Monday 09:00 - 17:00
Tuesday 09:00 - 17:00
Wednesday 09:00 - 17:00
Thursday 09:00 - 17:00
Friday 09:00 - 17:00