Beta ICT
our vision is provide safe,affordable and timely solutions through technology.
🤳0953902828
24/10/2024
ለሞባይል ቀፎ መንታፊዎች መላ ተገኘላቸው!
• ጉግል የተሰረቁ ሞባይል ቀፎዎች ዳግም እንዳይሰሩ የሚያደርግ ፈጠራ መተግበሩን አስታውቋል
ጎግል የተሰረቁ ሞባይል ቀፎዎች ዳግም እንዳይሰሩ የሚያደርግ ፈጠራ መተግበሩን ገለጸ፡፡ የስልክ ንጥቂያ ወንጀል ኢትዮጵያን ጨምሮ በበርካታ ሀገራት እየተስፋፋ የመጣ ወንጀል መሆኑ ይታወቃል፡፡
ጎግል በሰው ሰራሽ አስተውሎት የታገዘ ቴክኖሎጂ ይፋ ማድረጉን አስታውቋል፡፡ ይህ ቴክኖሎጂ ሰዎች ስልካቸውን በስርቆት ሲያጡ፣ ለስልክ ቀፎ አምራች ድርጅት ወዲያውኑ ማመልከት የሚችሉበትን ስርዓት ዘርግቷል ተብሏል፡፡
ከዚህ በፊት ሰዎች ስልካቸውን ሲሰረቁ ቀፎው እንዳይሰራ ለማድረግ ማዘጋት የሚችሉት የይለፍ ቃላቸውን ካስታወሱ ብቻ ነበር የተባለ ሲሆን፤ አሁን ግን ስልክ ቁጥራቸውን መናገር ከቻሉ የተሰረቀው ስልክ እንዳይሰራ ማድረግ የሚያስችል ቴክኖሎጂ መተግበሩን ቢቢሲ ዘግቧል፡፡
ሌቦች የስልክ ቀፎን ከወሰዱ በኋላ ለመደበቅ ቢሞክሩና ዳግም ጥቅም ላይ ለማዋል ሲሞክሩ ኤአይን በመጠቀም ለዘለቄታው ከአገልግሎት ውጪ እንዲሆን የሚያደርግም ነው፡፡
ለአንድሮይድ ስልክ የተገጠመለት ኤአይ ቴክኖሎጂ፤ ቀፎው ላይ በተገጠመለት ሴንሰር አማካኝነት እንዳይከፈት አድርጎ መዝጋት ይችላልም ተብሏል፡፡
ከዚህ በተጨማሪም ስልካቸውን የተሰረቁ ሰዎች የጠፋባቸውን መረጃዎች ወደ ሦስተኛ አካል ከመተላለፋቸው በፊት ያለምንም መቆራረጥ ዳግም መልሰው እንዲያገኙ እንደሚያደርግ ተገልጿል፡፡
(አል-ዐይን)

Android’s theft protection features keep your device and data safe Android rolls out theft protection features to safeguard your data before, during and after a theft incident.
03/07/2022
"የአማርኛ መፃፊያ ኪቦርድ የፈለሰፈው"
የአማርኛ ቋንቋ መተየቢያ መኪና (Type writer) የተፈለሰፈው በ1925 ዓ.ም በኢንጂነርር አያና ብሩ ሲሆን ይህም ለአማርኛ ቋንቋ እድገት ትልቅ አስተዋጽኦ አድርጓል ። በሆሮ ጉዱሩ ወለጋ የተወለደው ኢንጂነር አያና ብሩ የአማሪኛ ኪቦርድ ፈጣሪ ብቻ ሳይሆን በ1920ዎቹ ፋሺስት ጣሊያንን የተዋጋ ብርቅዬ የኦሮሞ ልጅ ነው። ይህ ብቻም ሳይሆን ልጁ ጀነራል አበራ አያና ብሩም እንዲሁ በውትድረና ህይወት ያሳለፈ ጀግና ነበት።
Click here to claim your Sponsored Listing.
Category
Contact the business
Telephone
Website
Address
Piassa
Addis Ababa