Deju
19/12/2025
"The contribution we Ethiopians have made to world peace—to mention just a few: the Korean War, the Rwandan Civil War, Somalia, and the Abyei region of South Sudan—is a legacy written in blood that will endure forever."
19/12/2025
በመደመር መንግስት አሻጋሪ እይታ ህልሞቻችንን በማሳካት የታፈረች እና የተከበረች ሀገር እንገነባለን!
ሀገራችን ከለውጡ በፊት የነበረችበት ነባራዊ ሁኔታ ወደፊት ለመጓዝ ምንም አይነት አስቻይ ሁኔታዎች ያልነበሩት ሲሆን የመደመር መንግስት በተደመረ እሳቤ ሀገራችንን ለማበልፀግ በያዘው ግልፅ እና ብቁ አቋም ፈተናዎችን ወደ ዕድል ቀይሯል።
የለውጡ መንግስት በፓርቲያችን አሻጋሪ እሳቤዎች እና በመደመር መንግስት ጥልቅ ፍልስፍና እየተመራ መስቀለኛ መንገድ ላይ የነበረችዋን ሀገራችንን ስብራቶች የሚጠግን ፣ ወደ ልዕልናዋ የሚወስድ ፅኑ መሰረት መገንባት ችሏል።
እራሳቸውን ከሀገር እና ከህዝብ ያስቀደው ፅንፈኛ ግለሰቦች እና ቡድኖች እንዲሁም ኢትዮጵያ የተፈጥሮ ሀብቶቿን አልምታ ለመበልፀግ የጀመረችው የለውጥ ጉዞ ያልተመቻቸው ሀገራት ፣ ተለዋዋጩ ዓለም አቀፋዊ ሁኔታ እንዲሁም ሌሎች ሰው ሰራሽ እና የተፈጥሮ አደጋዎች የደቀኑትን የሀገራችንን ለውጥ ሊቀለብሱ የሚችሉ አደጋዎች ሁሉ ከጉዟችን አልገቱንም ፤ ወደፊት አስፈነጠሩን እንጅ።
እንድንፈጥን ሳይሆን እንድናዘግም ፣ እንድንዘል ሳይሆን እንድንዝል ፣ ተስፋችን እንድናለመልም ሳይሆን እንድንተክዝ ፣ የተደራረቡ መሰናክሎችን ወደ እድል በመቀየር እንደ ወርቅ ነጥሮ የወጣው ብልፅግና ፓርቲ እና በእሱ የሚመራው የለውጡ መንግስት ኢትዮጵያን ከነበረችበት የቁልቁለት ምዕራፍ በማውጣት ሁለንተናዊ ብልፅግናን ማረጋገጥ የሚያስችል መሰረትን አፅንተዋል።
የሀገራትን ተወዳዳሪነት ስለሚወስነው የቴክኖሎጂ አቅም ሲወራ ቅንጦት የሚመስላቸው ፣ ግብርናችንን አዘምነን የምግብ ዋስትናችን እና የምግብ ሉዓላዊነታችንን ለማረጋገጥ የምናደረገውን ርብርብ በስጋት የሚመለከቱ ፣ የተፈጥሮ ፀጋዎቻችንን ለማልማት የያዝነውን ቁርጠኛ አቋም ሌሎችን እንደመጉዳት ፣ ከተሞቻችን ከጥልቅ ጉስቁልና ለማውጣት የሚተገበሩ የኮሪደር ልማትን የመሳሰሉ ውጤታማ ኢኒሸቲቮችን ጭምር በማጥላላት የተጠመዱ ባዳ እና ባንዳዎች ለጥፋት ቢተባበሩም የመደመርን ትውልድ ታሪካዊ ግስጋሴ ማስቆም አልቻሉም።
ፅንፈኛ አካላት እና ታሪካዊ ጠላቶቻችን ከእኩይ ዓላማቸው ጋር ተቸንክረው ይኖሩ ይሆናል እንጅ ዛሬም ነገም የከፍታ ጉዞአችንን ሊቀለብሱ አይችሉም።
የመደመር መንግስት ሀገርን የማበልፀግ ጉዞ አይደለም ዛሬ ከፈተናዎቻችን በላይ መስፈንጠር ችለን ይቅርና ትላንት በጅምር ላይ እያለም እንደ ንስር ከፈተናዎች በላይ በመብረር አንፀባራቂ ድሎችን አስመዝግቧል።
ተፈጥሮ አብዝታ የቸርችንን እምቅ ሀብት ተጠቅመን ፣ ህዝባችንን አስተባብረን እርዳታን ታሪክ አድርገን ዜጎቿ በምቾት የሚኖሩባት ለሌሎችም የምትተርፍ ሀገር የመገንባት ህልማችንን በመደመር መንግስት አሻጋሪ እይታዎቻችን ዕውን እናደርጋለን።
በብልፅግና ፓርቲ የአዲስ አበባ ቅ/ፅ/ቤት
Click here to claim your Sponsored Listing.
Category
Contact the public figure
Telephone
Website
Address
Addis Ababa
Opening Hours
| Monday | 09:00 - 17:00 |
| Tuesday | 09:00 - 17:00 |
| Wednesday | 09:00 - 17:00 |
| Thursday | 09:00 - 17:00 |
| Friday | 09:00 - 17:00 |
| Saturday | 09:00 - 17:00 |
| Sunday | 09:00 - 17:00 |