Tegbareid Polytechnic College

Tegbareid Polytechnic College

Share

Addis Ababa Tegbare-id Poly Technique College was established in 1942 as a Technical School. Since then, the college has been offering vocational trainings mainly for technical occupations. Tegbare-id is currently regarded as one of the top polytechnic colleges. Currently, the college offers vocational trainings in twelve different occupational fields, including Information and Communication Techn

Photos from Tegbareid Polytechnic College's post 28/06/2026

“ከCOC ቅርንጫፍ ጽ/ቤት አመራሮች ጋር በብሔራዊ ምዘና (COC) አፈጻጸምና ቀጣይ እቅድ ዙሪያ የውይይት መድረክ ተካሄደ::”

ተግባረዕድ ሚዲያና ኮሚዩኒኬሽን ሰኔ 19/2018/ዓ.ም

የአዲስ አበባ ተግባረዕድ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ የ2017 ዓ.ም. ተመራቂ ሰልጣኞች የብሔራዊ ምዘና (COC) አፈጻጸም ሪፖርትን በመገምገምና የ2018 ዓ.ም. ተመራቂ ሰልጣኞች የምዘና ሂደትን በተሻለ ውጤት ለማስፈጸም ያለመ የውይይት መድረክ ተካሂዷል።

በመድረኩ የልደታ እና የቂርቆስ ማኑፋክቸሪንግ ኮሌጆች የስልጠናና አካዳሚክ ጉዳይች ም/ዲኖች፣ ከአራዳና ጉለሌ፣ ከልደታና ቂርቆስ እና ከኮልፌ የትምህርትና ስልጠና ቁጥጥር ባለስልጣን ቅርንጫፍ ጽ/ቤቶች የመጡ ባለሙያዎች እንዲሁም የኮሌጃችን ዲኖች እና የስልጠና ዘርፍ ኃላፊዎች ተሳትፈዋል።

የመድረኩን መክፈቻ ንግግር ያደረጉት የኮሌጁ ዋና ዲን አቶ ተስፋየ አድማሱ ሲሆኑ፣ ብሔራዊ ምዘና የሰልጣኞችን የሙያ ብቃት የሚያረጋግጥ ወሳኝ ሂደት መሆኑን በመግለጽ፣ በሂደቱ የሚሳተፉ ሁሉም አካላት በቅንጅት፣ በኃላፊነትና በተጠያቂነት በመስራት የ2018 ዓ.ም. የምዘና ውጤትን ከፍ ማድረግ እንደሚገባ አሳስበዋል።

የዉይይቱ ዋና ዓላማው የ2017 ዓ.ም. የብሔራዊ ምዘና አፈጻጸምን በጥልቀት በመገምገም ጠንካራ ጎኖችን ማጠናከር፣ የታዩ ክፍተቶችን በመለየት ለ2018 ዓ.ም. የምዘና ሂደት የተሻለ ዝግጅትና የጋራ የመፍትሔ አቅጣጫ ማስቀመጥ ነዉ።

ሰነዱን ያቀረቡት የኮሌጁ ሬጅስትራር ጽ/ቤት ኃላፊ የሁኑት አቶ ሀይረዲን ሙሳ ሲሆኑ፣ በሰነዱ ላይ የ2017 ዓ.ም. ተመራቂ ሰልጣኞች የብሔራዊ ምዘና (COC) አፈጻጸም ሪፖርት እና የ2018 ዓ.ም. ተመራቂ ሰልጣኞች የምዘና ሂደት በስፋት ቀርቧል።

በሪፖርቱ መሰረት በ2017 ዓ.ም. 1,815 ተመራቂ ሰልጣኞች ከነበሩት ውስጥ 1,165 ሰልጣኞች የብሔራዊ ምዘና የወሰዱ ሲሆን፣ 314 ሰልጣኞች ብቁ ሆነው ማለፋቸው ቀርቧል።

በተጨማሪም የመብቃት ምጣኔ፣ በሂደቱ የታዩ ጠንካራ ጎኖች (Strengths)፣ ከተመዛኞች ስነ-ልቦና አንፃር የታዩ ችግሮች፣ ከትምህርትና ስልጠና ቁጥጥር ባለስልጣን ቅርንጫፍ ጽ/ቤቶች አንፃር መሻሻል የሚገባቸው ጉዳዮች፣ ከመዛኞች አንፃር ያሉ ክፍተቶች እና ለ2018 ዓ.ም. ሰልጣኞችን በብቃት ለማዘጋጀት የተደረጉ ቅድመ ዝግጅቶች በዝርዝር ቀርበዋል።

በውይይቱ ተሳታፊዎች በቀረበው ሰነድ ላይ ሰፊ ሀሳብ በመስጠት፣ የምዘና ጥራትን ለማሻሻል፣ የሰልጣኞችን የስነ-ልቦና ዝግጅት ለማጠናከር፣ በኮሌጆች፣ በቅርንጫፍ ጽ/ቤቶች፣ በመዛኞችና በአሰልጣኞች መካከል ያለውን ቅንጅታዊ ስራ ለማጠናከር እና የ2018 ዓ.ም. የመብቃት ምጣኔን በከፍተኛ ደረጃ ለማሳደግ የሚያስችሉ ተጨባጭ የመፍትሔ አቅጣጫዎች ተቀምጠዋል።

በመጨረሻም ሁሉም ተሳታፊ አካላት በጋራ በመስራት የ2018 ዓ.ም. ብሔራዊ ምዘና ውጤትን በማሻሻል ብቁና ተወዳዳሪ የሰው ኃይል ለሀገር ለማፍራት ያላቸውን ቁርጠኝነት በማረጋገጥ መድረኩ ተጠናቋል፡፡

ተግባረዕድ ኮሚዩኒኬሽንና ህዝብ ግንኙነት

Want your school to be the top-listed School/college in Addis Ababa?
Click here to claim your Sponsored Listing.

Category

Telephone

Address


Mexico Square
Addis Ababa
251

Opening Hours

Monday 02:30 - 23:30
Tuesday 02:30 - 23:30
Wednesday 02:30 - 23:30
Thursday 02:30 - 23:30
Friday 02:30 - 23:30