abyssinialaw.com
abyssinialaw.com is an open source for Ethiopian Lawyers, Students, Lecturers, Judges, Prosecutors, Advocates, Draft person and Researchers. It is dedicated not only to making Ethiopian Laws freely available in an electronic format but also to provide the status of the laws. This site is not affiliated in any way with any government entity; it is an independent, an effort to foster the learning of
በግልግል ዳኝነት የፍርድ ቤቶች ሚና
ጸሐፊ፡ ፍቃዱ አንዳርጌ መኮንን (ጠበቃ እና የሕግ አማካሪ)
ይህ ጽሑፍ፣ ከፍርድ ቤት ውጪ በግልግል ዳኝነት በሚፈቱ አለመግባባቶች ውስጥ መደበኛ ፍርድ ቤቶች ያላቸውን ወሳኝ ሚና ይተነትናል። የግልግል ዳኝነት ራሱን የቻለ ሥርዓት ቢሆንም፣ የግልግል ጉባዔን በማቋቋም፣ ጊዜያዊ ትዕዛዞችን በመስጠት፣ በማስረጃ አሰባሰብ ላይ ድጋፍ በማድረግ፣ እንዲሁም በግልግል የተሰጡ ውሳኔዎችን በማስፈጸምና በይግባኝ በመመርመር ረገድ የፍርድ ቤቶች ድጋፍ የግድ አስፈላጊ መሆኑን ጽሑፉ በዝርዝር ያስረዳል።
https://www.abyssinialaw.com/blog/the-role-of-courts-in-arbitration
09/09/2025
A Legal Guide to Ethiopian Security Listings: A Roadmap for Banks | Legal Analysis | Liku Worku Law Office A legal analysis on 'A Legal Guide to Ethiopian Security Listings: A Roadmap for Banks.' Insight from Liku Worku Law Office, a premier law firm in Addis Ababa, Et…
https://t.me/abyssinialaw/411
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ገቢዎች ቢሮ የ2017 ዓ.ም የግብር ዘመን ግብር አወሳሰንና አሰባሰብ አሠራር መላክን ይመለከታል በሚል ርዕስ ጠበቆች ለ2017 በጀት ዓመት ከግብር ዓመቱ አጠቃላይ ገቢ 35% እንደ ወጪ 65% ግብር የሚከፈልበት ገቢ ሆኖ በሠንጠረዥ "ሐ" መሠረት ግብሩን በማስላት ተሰውኖ ገቢውን እንዲሰበሰብ በማለት ትዕዛዝ ሰጥቷል። ውሳኔውን ከዚህ ያግኙ
ደረጃ ሀ እና ለ የሒሳብ መዝገብ በለመያዛቸው ምክንያት የግብር ማስከፈያ የማትሪፈያ ህዳጉ እጥፍ ተወስዶ እና የታክስ ጉዳቱን 40 በመቶ እና የታክሱን እጥፍ በመቅጣት ሕጉን ተፈጻሚ እንዲደረግ ብሏል፤
የወንጀል ቅጣት አወሳሰን መመሪያ ቁጥር 3/2017
የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት የወንጀል ቅጣት አወሳሰን መመሪያ ቁጥር 3/2017 አውጥቷል።
ይህ መመሪያ ከጥቅምት 1 2006 ዓ.ም ጀምሮ ሥራ ላይ የነበረውን የወንጀል ቅጣት አወሳሰን መመሪያ በማሻሻል የወጣ ሲሆን ፍርድ ቤቱ መመሪያውን እና ማብራሪያውን ለተጠቃሚዎች ዛሬ አሰራጭቷል።
መመሪያው እና ማብራሪያውን ከዚህ ማግኘት ይችላሉ።
11/04/2025
በመጀመሪያ ደረጃ መቃወሚያዎች ላይ ትኩረት የሚሹ አወዛጋቢ ነጥቦችና መፍትሔዎቻቸው
በ፡ ካሴ መልካም
ይህ ጽሑፍ የተወሰደው በፍትሐብሔር ሥነ-ሥርዓት ሕግ የመጀመሪያ ደረጃ መቃዎሚያዎች በሚል ከታተመው በ2017 ዓ.ም ተሻሻሎ በቀረበው መጽሐፌ ላይ ሲሆን የግርጌ ማስታዎሻዎቹ እና ማጣቀሻዎቹ ለዚህ ጽሑፍ ሲባል ለንባብ በሚመች አግባብ እንደገና ተቀናጅተው ተሰርተዋል፡፡ በዚህ ጽሑፍ የተካተቱት አብዛኛዎቹ ነጥቦች አወዛጋቢ ሆኖም በሕግ ባለሙያው ብዥታ እና ልዩነት የሚፈጥሩ ነጥቦች በመጽሐፉ የመጀመሪያ ዕትም ያልነበሩ አሁን ላይ በችሎት በሚገጥሙ ክርክሮች ሰበር ጭምር መፍትሔ የሰጣቸውን እና ሰበር መፍትሔ ያልሰጠባቸውን ደግሞ የመጽሐፉ አዘጋጅም የራሱን ምልከታ እና መፍትሔ የሚላቸውን ሃሳቦች ያሰቀመጠባቸው ጉዳዮች ናቸው፡፡
በዚህ በተሻሻለው ዕትም ከ400 በላይ የመጀመሪያ ደረጃ መቃዎሚያን የሚመለከቱ በ5 እና በ7 ዳኞች የተሰጠ የሰበር ችሎቱ አስገዳጅ የሕግ ትርጉ እና በርካታ የፌዴራሽን ምክር ቤቶች የተካተቱበት ነው፡፡ ከዚህም በተጨማሪ በመጀመሪያ ደረጃ እና በከፍተኛ ፍርድ ቤት በችሎት አከራካሪ የሆኑ ጉዳዮች እና ፍ/ቤቶቹ የሰጡት ፍርድን መነሻ በማድረግ መፍትሔ የሚሆኑ ነጥቦችን ለማስቀመጥ ተሞክሯል፡፡
በዚህ ጽሑፍ የሚከተሉትን ያገኛሉ።
1. በጽሑፍ ያልቀረበን የመጀመሪያ ደረጃ መቃዎሚያን ከሳሹ በቃል ክርክር የማቅረብ መብት ያለው ስለመሆኑ
2. በመቃወሚያ ላይ ማስረጃ የመስማት አስፈላጊነት
3. በብዙ መቃወሚያዎች ላይ የውሳኔ አሰጣጥ ስነ-ስርዓት
4. በመቃወሚያዎች ላይ ከሳሽ በክሱ ያልዘረዘራቸውን ማስረጃዎች የማቅረብ መብት
5. በተጣመሩ ተከሳሾች አንዱ በሌላኛው ላይ መቃዎሚያዎችን የሚያነሱበት አግባብ
6. በመቃዎሚያዎች ላይ ይግባኝ የሚባልበት አግባብ
7. በመጀመሪያ ደረጃ መቃዎሚያ ላይ ውሳኔ ከተሰጠ በኋላ የክስ መሻሻል ውጤት
8. የመጀመሪያ ደረጃ መቃዎሚያና እሱን ለመወሰን መሰረት የሚሆነው ሕግ
9. በፍርድ ቤት በራሱ እና በተከራከሪዎች ብቻ የሚነሱ መቃዎሚያዎችን
10. በተከራካሪዎች ብቻ የሚነሱ የመጀመሪያ ደረጃ መቃዎሚያዎች
11. ፍርድ ቤቱ በራሱ ሊያነሳቸው የሚችሉ የመጀመሪያ ደረጃ መቃዎሚያዎች
https://www.abyssinialaw.com/blog/controversial-points-and-their-solutions-for-preliminary-objections
መልካም ንባብ!
Click here to claim your Sponsored Listing.
Category
Contact the practice
Telephone
Website
Address
Bole, Gulf Aziz Building
Addis Ababa
23113
Opening Hours
| Monday | 09:00 - 17:00 |
| Tuesday | 09:00 - 17:00 |
| Wednesday | 09:00 - 17:00 |
| Thursday | 09:00 - 17:00 |
| Friday | 09:00 - 17:00 |