Ethiopian Human Rights Commission
13/07/2026
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ሰብአዊ መብቶች አማካሪ ምክር ቤት ተቋቋመ።
"የጅግጅጋ ዲክላሬሽን" (Jigjiga Declaration) በሚል ስያሜ ምክርቤቱን ለማቋቋም የተደረገው ስምምነት በሙሉ ድምፅ ጸደቋል።........
ጅግጅጋ — “የሰብአዊ መብቶች እና ሰላም” በሚል መሪ ቃል በጅግጅጋ ከተማ እየተካሄደ በሚገኘው ሀገራዊ መድረክ ላይ፣ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ሰብአዊ መብቶች አማካሪ ምክር ቤት ለማቋቋም የተደረገው ታሪካዊ ስምምነት በሙሉ ድምፅ መጽደቁ ተገለጠ።
በጉባኤው አስተናጋጅ ከተማ ስም “የጅግጅጋ መግለጫ” ተብሎ የተሰየመው ይህ ስምምነት፤ በሀገሪቱ የዴሞክራሲያዊ አስተዳደር ግንባታን ለማፋጠን፣ ሰላምን ለማስፈንና ዘላቂ ልማትን ለማረጋገጥ ከፍተኛ ሚና ይኖረዋል ተብሎ ታምኖበታል።
የመድረኩ ተሳታፊዎች እንደገለጹት፣ በሕገ መንግሥቱና በዓለም አቀፍ የሰብአዊ መብቶች ስምምነቶች የተረጋገጡ መብቶችን በተግባር ለመተርጎም የሁሉንም ባለድርሻ አካላት ትብብር ይጠይቃል።
በዚህም መሠረት አዲስ የሚቋቋመው የአማካሪ ምክር ቤት በፌዴራል መንግሥት ተቋማት፣ በገለልተኛ ሕገ መንግሥታዊ አካላት፣ በክልል መንግሥታት፣ በትምህርት ተቋማትና በሌሎች ባለድርሻ አካላት መካከል ጠንካራ ውይይትና ትብብር ለመፍጠር የሚያስችል መድረክ ሆኖ ያገለግላል።
ምክር ቤቱ በዋናነት፦
• የጋራ መረጃዎችን ለመለዋወጥ፣
• በሰብአዊ መብት አጠባበቅ ዙሪያ ያሉ ተግዳሮቶችን በጋራ ለመለየት፣ እና
• መብቶችን ከማስፋፋትና ከመጠበቅ ጋር በተያያዘ ተገቢና ወቅታዊ እርምጃዎችን በጋራ ለመውሰድ እንደሚያስችል በመግለጫው ላይ በግልጽ ተመላክቷል።
ይህ ስምምነት መጽደቁ በሀገሪቱ የሰብአዊ መብቶች አያያዝ ሥርዓት ላይ አዲስ ምዕራፍ ሊከፍት የሚችልና የባለድርሻ አካላትን ቅንጅታዊ አሠራር ይበልጥ የሚያጠናክር መሆኑን የጉባኤው ተሳታፊዎች ገልጸዋል።
ስምምነቱ የሶማሌ ክልል ፕሬዝደንት አቶ ሙስጠፌ መሀመድ ፣ የኢሰመኮ ዋና ኮሚሽነር ብርሃኑ አዴሎ፣ ምክትል ዋና ኮሚሽነር እና የየዘርፍ ኮሚሽነሮች የኢፌዴሪ ህዝብ ወና እምባ ጠባቂ ስመኝ ውቤ የተባበሩት መንግሥታት የሰብአዊ መብቶች ከፍተኛ ኮሚሽነር ጽሕፈት ቤት (OHCHR-ESARO) ተወካይ አቶ ጆሴፍ ኑጉያም እና ሁሉም ባለድርሻዎች በተገኙበት ነው የጸደቀው።
🔗 https://ehrc.org
🇪🇹
በነጻ የስልክ መስመራችን 7307 ላይ በመደወል የሰብአዊ መብቶች ጥሰት አቤቱታ ማቅረብ ወይም ጥቆማ መስጠት ይችላሉ።
04/07/2026
ትግራይ፡- በትግራይ ክልል ያለውን አሳሳቢ የሰብአዊ መብቶች ሁኔታ በተመለከተ..
በክልሉ ወጣቶችን ከፈቃዳቸው ውጪ ወደ ወታደራዊ ሥልጠና የማሰማራትና ሐሳብን በነጻነት የመግለጽ መብትን የመገደብ ተግባራት ከሰብአዊ መብቶች መርሆዎች እና ከሕገ መንግሥቱ ጋር የሚጣረሱ በመሆናቸው በአፋጣኝ ሊቆሙ ይገባል
🔗 https://ehrc.org/?p=38519
🇪🇹
በነጻ የስልክ መስመራችን 7307 ላይ በመደወል የሰብአዊ መብቶች ጥሰት አቤቱታ ማቅረብ ወይም ጥቆማ መስጠት ይችላሉ።
ትግራይ፡- በትግራይ ክልል ያለውን አሳሳቢ የሰብአዊ መብቶች ሁኔታ በተመለከተ - Ethiopian Human Rights Commission - EHRC The Ethiopian Human Rights Commission (EHRC) is an independent federal state body established by Parliament as the national human rights institution with the mandate for the promotion and protection of human rights.
Click here to claim your Sponsored Listing.
Category
Contact the organization
Telephone
Website
Address
Headquarters: Meskel Square, On Bole Airport Road Next To Hyatt Regency Hotel
Addis Ababa