Finfinne Press

Finfinne Press

Share

22/06/2026

#ኢትዮጵያን ጨምሮ የአፍሪካ የዘር ሀረግ ያላቸው #የእስራኤል ወታደሮች #በሶማሊላንድ መሰማራታቸው ተዘገበ

የእስራኤል መንግስት በተለይ የዘር ሀረጋቸው ከኢትዮጵያ የሆኑ እስራኤላውያን ወታደሮችን ያካተተ የጦር ኃይል ወደ ሶማሊላንድ ማሰማራቱን ሚድል ኢስት አይ አንድ ከፍተኛ የ #ሶማሊያ መንግሥት ባለሥልጣንን ዋቢ በማድረግ ዘገበ።

ስማቸው ያልተጠቀሰው ባለሥልጣኑ ለሚዲያው እንደገለጹት፥ እስራኤል በታኅሣሥ ወር 2018 ዓ.ም. ለሶማሊላንድ የሀገርነት እውቅና ከሰጠች ከጥቂት ጊዜ በኋላ ወደ 50 የሚጠጉ የእስራኤል ወታደሮች ወደ ሀገሪቱ ተልከዋል።

ባለሥልጣኑ፥ ወታደሮቹ አፍሪካዊ መነሻ ካላቸው እስራኤላውያን በተለይም የዘር ሀረጋቸው ኢትዮጵያ ከሆኑት መካከል ተመርጠው መሰማራታቸውን ጠቅሰው፤ ይህም የሰዎችን ትኩረት ሳይስቡ ከአካባቢው ማኅበረሰብ ጋር በቀላሉ ተቀላቅለው ለመንቀሳቀስ እንዲችሉ ታስቦ የተደረገ ነው ብለዋል።

የእስራኤል ጦር ኃይል በዚህ ጉዳይ ላይ አስተያየት ለመስጠት ፈቃደኛ ሳይሆን መቅረቱን ዘገባው ገልጿል። የሶማሊላንድ ባለሥልጣናትም ማብራሪያ እንዲሰጡ ለቀረበላቸው ጥያቄ ምላሽ አለመስጠታቸውን ሪፖርቱ አክሎ ገልጿል።

ይህ መረጃ የወጣው በእስራኤል እና በሶማሊላንድ መካከል እያደገ የመጣውን ከፍተኛ የጸጥታ ትብብር ተከትሎ ነው።

ባለፈው ሳምንት የእስራኤል መከላከያ ሚኒስትር እስራኤል ካትስ ከሶማሊላንድ ፕሬዚዳንት አብዲራህማን መሐመድ አብዱላሂ ጋር በተገናኙበት ወቅት ሁለቱ ወገኖች «ከሕዝብ ዕይታ ውጭ በምስጢር» ለዓመታት በትብብር ሲሠሩ መቆየታቸውንና ሂደቱም እስካሁን ሚስጢራዊነቱ ተጠብቆ የቆየ መሆኑን ጠቁመዋል።

ከቅርብ ጊዜ ወዲህ እስራኤል በሶማሊላንድ ውስጥ ወታደራዊ መሠረተ ልማት ሊኖራት ይችላል የሚሉ ግምቶች በከፍተኛ ሁኔታ እየጨመሩ ቢመጡም፥ የሶማሊላንድ መከላከያ ሚኒስትር መሐመድ ዩሱፍ አሊ እስራኤል በሀገሪቱ ውስጥ ምንም ዓይነት ወታደራዊ የጦር ሰፈር እንደሌላት በይፋ አስተባብለዋል።

ዘገበው አዲስ ስታንዳርድ ነው

ቴሌግራም፦
📌 t.me/Brics4ethiopia

•════••Reminder ••••════•
(⚠️ This content is only for educational, information, and historical awareness purposes.)

22/06/2026

የፓኪስታኑ ጠቅላይ ሚኒስትር ሼህባዝ ሻሪፍ በስዊዘርላንድ የተካሄደው የኢስላማባድ የመግባቢያ ስምምነት ከፍተኛ የልዑካን ኮሚቴ ስብሰባ በአዎንታዊ እና ገንቢ መንፈስ ተጠናቆ አበረታች ውጤቶችን ማስገኘቱን አስታውቀዋል። በዚህም መሰረት በ60 ቀናት ውስጥ የመጨረሻ ስምምነት ላይ ለመድረስ የሚያስችል የጊዜ ሰሌዳ (roadmap) ተዘጋጅቷል፤ የፖለቲካ ቁጥጥር የሚያደርግ ኮሚቴ ተቋቁሟል እንዲሁም ተጨማሪ የቴክኒክ ንግግሮች መጀመራቸው ተገልጿል።🤝

ቴሌግራም፦
📌 t.me/Fastsinfo99

22/06/2026

"አስፈላጊ ከሆነ አሜሪካ የሆርሙዝ ሰርጥን (Strait of Hormuz) ቁጥጥር ስር ልታውለው ትችላለች።"

~ዶናልድ ትራምፕ (የአሜሪካ ፕሬዝዳንት)

" . . . ወሬ ብቻ! እስቲ ሞክሩ! ወሬ ተዉና አድርጉት!. . . "

~መሐመድ ባጌር ጋሊባፍ (የኢራን ዋና ተደራዳሪ)

Want your public figure to be the top-listed Public Figure in Addis Ababa?
Click here to claim your Sponsored Listing.

Category

Telephone

Address


Addis Ababa
1000